Friday, December 8, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅየፓርላማው ውሎ

የፓርላማው ውሎ

ቀን:

ሐሙስ ሚያዝያ 11 ቀን 2010 ዓ.ም. ረፋድ ላይ በፓርላማ በነበረ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) የካቢኔ አባላት ሹመት አፀድቀዋል፡፡ ተሿሚዎቹም ቃለ መሃላ ፈጽመዋል፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ከቀረቡ ተሿሚዎች መካከል አሥሩ አዳዲስ ሲሆኑ፣ ስድስቱ ደግሞ ከአንዱ ወደ ሌላው የሚኒስትርነት ኃላፊነት የተዘዋወሩ ናቸው፡፡ ከካቢኔ አባላቱ በተጨማሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ አባዱላ ገመዳ ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት ተሰናብተው፣ በምትካቸው ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ተጠቁመው ለመጪዎቹ ሁለት ዓመታት አፈ ጉባዔነቱን ተረክበዋል፡፡ ቃለ መሃላም ፈጽመዋል፡፡ አቶ አባዱላ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደኅንነት አማካሪ ተደርገዋል፡፡ በዕለቱ የግብርና እና የእንስሳት ሀብት ሚኒስቴርን እንደ አዲስ ለማደራጀት የቀረበው ረቂቅ አዋጅም በሦስት ተቃውሞና በአንድ ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል፡፡ ይህ አዋጅ በምክር ቤቱ አባላት ጥያቄዎችና ተቋውሞዎች ቀርበውበት ነበር፡፡ ከፓርላማው ውሎ በኋላ የተለያዩ ሹመቶችም ተሰጥተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ታዋቂው የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አይቴል የስትራቴጂ ለውጥ አካል የሆነውን አዲስ አርማ እና መለዮ ይፋ አደረገ።

በአለማችን ታዋቂ ከሆኑት የኤሌክትሮኒክስ ብራንዶች መካከል አንዱ የሆነው እና...

የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]

አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው? ጠፋሁ አይደል? ጠፋሁ ብቻ?! ምን ላድርግ ብለሽ...

በሱዳን ላይ ያጠላው የመከፋፈል ዕጣና ቀጣናዊ ተፅዕኖው

የሱዳን ጦርነት ስምንተኛ ወሩን እያገባደደ ይገኛል፡፡ ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን...