Sunday, June 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየኦሮሚያ ክልል መንግሥትና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዳዲስ አመራሮችን ሾሙ

የኦሮሚያ ክልል መንግሥትና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዳዲስ አመራሮችን ሾሙ

ቀን:

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ተደርገው በተሾሙት አቶ አሰግድ ጌታቸው ምትክ የፐብሊክ ሰርቪስ፣ የሰው ሀብት ልማት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ አዳሙ አያና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽሕፈት ቤትና የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ ተደርገው ተሾሙ፡፡

የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ፕሬዚዳንት አቶ ለማ መገርሳ ከፌዴራል፣ ከአዲስ አበባ ከተማና ከክልሉ ውስጥ በተለያዩ ኃላፊነቶች ላይ የነበሩ የኦሕዴድ አባላትን በማሰባሰብ አዲስ ካቢኔ መሥርተዋል፡፡

ከፌዴራል የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር)፣ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር)፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) እና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሲሳይ ገመቹ ኦሮሚያ ውስጥ አዲስ ሹመት ተሰጥቷቸዋል፡፡

ከአዲስ አበባ ደግሞ ላለፉት አምስት ዓመታት የከንቲባ ጽሕፈት ቤትን የመሩት አቶ አሰግድ፣ የክልሉን ፕሬዚዳንት ቢሮ እንዲመሩ ተደርጓል፡፡

አቶ አሰግድ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ሥራ አስኪያጅ፣ የአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው ሠርተዋል፡፡ ኢትዮ ቴሌኮምን ጨምሮ በሰባት ተቋማት የቦርድ አባል በመሆንም አገልግለዋል፡፡

አቶ ለማ ከፌዴራልና ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በተለይ ለሦስቱ ውጤታማ ለተባሉ ሴት ከንቲባዎች ከፍተኛ ሥልጣን ሰጥተዋል፡፡

የሻሸመኔ ከንቲባ የነበሩት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት፣ የለገጣፎ ለገዳዲ ከንቲባ የነበሩት ወ/ሮ ጫልቱ ሰኚ የኦሮሚያ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ተደርገው የተሾሙ ሲሆን፣ የአዳማ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የኦሕዴድ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ተደርገው ተሹመዋል፡፡

ወ/ሮ አዳነች የተኩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ይዘውት የነበረውን ቦታ ነው፡፡ የክልሉ ፕሬዚዳንት በአጠቃላይ ለ23 ሰዎች ሹመት በመስጠት አዲስ ካቢኔ መሥርተዋል፡፡

የኦሮሚያ ፕሬዚዳንት በወሰዷቸው ምትክ የፌዴራል መንግሥት ተተኪዎችን እያዘጋጀ ሲሆን፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግን ከፌዴራል መንግሥት አቶ አዳሙን ወስዷል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አወዛጋቢው የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ጉዳይ

በኢትዮጵያ የሕገ መንግሥት ማሻሻል ጉዳይ ከፍተኛ የፖለቲካ ውዝግብ የሚቀሰቀስበት...

 መፍትሔ  ያላዘለው  የጎዳና  መደብሮችን  ማፍረስ

በአበበ ፍቅር ያለፉት ስድስት ዓመታት በርካቶች በግጭቶችና በመፈናቀሎች በከፍተኛ ሁኔታ...

የተናደው ከቀደምቱ አንዱ የነበረው የአዲስ አበባ ታሪካዊ ሕንፃ

ዳግማዊ አፄ ምኒልክ በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ መናገሻ ከተማቸውን...

የአከርካሪ አጥንት ሕክምናን ከፍ ያደረገው ‘ካይሮፕራክቲክ’

በአፍሪካ ከጀርባ ሕመም ጋር በተያያዘ በርካታ ሰዎች ለከፍተኛ የአካል...