Wednesday, June 12, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ስፖርትካፍ የኢትዮጵያን የቻን መሰናዶ መገምገም ጀመረ

ካፍ የኢትዮጵያን የቻን መሰናዶ መገምገም ጀመረ

ቀን:

  • ግብረ መልሱ ከአምስት ወራት በኋላ ለፌዴሬሽኑ ይቀርባል

እ.ኤ.አ. በ2020 የሚካሔደውን የአፍሪካ አገሮች ዋንጫን (ቻን) ለማስተናገድ ዕድሉን ያገኘችው ኢትዮጵያ፣ የምታካሒዳቸውን መሰናዶዎች የሚገመግም የካፍ ልዑካን ቡድን ሥራውን ጀመረ፡፡ በሞሮኮ አትናጋጅነት ተሰናድቶ በነበረው የዘንድሮ ቻን የእግር ኳስ ውድድር ላይ ኃላፊነቷን የተረከበችው ኢትዮጵያ፣ ያካሔደቻቸውንና የምታካሒደቸውን የስታዲየሞች ግንባታ ሒደትና ወቅታዊ ጉዳዮች የሚገመግሙ ልዑካን መሆናቸው ታውቋል፡፡

ሰኞ፣ ሚያዝያ 8 ቀን 2010 ዓ.ም. ግምገማውን የጀመረው የካፍ ልዑካን ቡድን፣ የአዲሱን የአደይ አበባ ስታዲየም በመጎብኘት ቀዳሚ ያደረገ ሲሆን፣ የግንባታው ሒደት 72 በመቶ ደረጃ ላይ መድረሱን በመመልከት መሠረታዊ ግንባታዎች ግን እስከ ውድድሩ መቃረቢያ ወቅት መጠናቀቅ እንዳለበት ማሳሰቡ ተሰምቷል፡፡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ጁነይዲ ባሻም ይህንኑ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ በመሠረተ ልማት፣ በመለማመጃ ሜዳ፣ በሆቴል፣ በሆስፒታል፣ በውኃ፣ በኤሌክትሪክ ኃይል፣ በኢንተርኔት ኔትወርክና በመሳሰሉት ላይ ያተኮረ ግምገማ ልዑኩ ማካሔዱን አቶ ጁነይዲ አብራርተዋል፡፡

ከካፍ የተወኩሉት ስድስት የልዑኩ አባላት ካለፈው ሰኞ ጀምሮ በሐዋሳ፣ በባህርዳርና በመቀሌ ጉብኝት አድርገዋል፡፡ በስቴዲየሞቹ ጉብኝት ወቅት የደኅንነት ጉዳይ፣ የስቴዲየሞቹ መውጫና መግቢያ በሮች ምቹነት፣ የስብሰባ አዳሽ፣ የመፀዳጃ ቤት ጥራት፣ የሚዲያ ክፍሎች፣ የሻወር ቤቶችና መልበሻ ክፍሎች እንዲሁም የዳኞች ክፍሎች ላይ ግምገማ አድርገዋል፡፡ በግምገማው ወቅትም የተለያዩ አስተያየቶች መሰንዘራቸው ተገልጾ፣ ግብረ መልሱ ከአምስት ወራት በኋላ ለፌዴሬሽኑ እንደሚቀርብ ፕሬዚዳንቱ አስታውሰዋል፡፡

- Advertisement -

ከአምስት ወራት በኋላም የነቀምትና የወልድያ ስቴዲየሞችም ለግምገማ እንደሚቀርቡ ጠቅሰዋል፡፡ አምስተኛውን የአፍሪካ አገሮች ዋንጫ ኬንያ እንድታሰናዳ ዕድል የተሰጣት ቢሆንም፣ በቂ ዝግጅት ባለማድረጓ በካፍ ውሳኔ ለሞሮኮ እንዲሰጣት መደረጉ አይዘነጋም፡፡ ኢትዮጵያ ስድስተኛውን የአፍሪካ አገሮች ዋንጫ ለማሰናዳት ኃላፊነቱን ተረክባለች፡፡

አሁን ባለው የኢትዮጵያ ስቴዲየሞች የግንባታና መሰናዶ አካሔድ በተለይ በክልሎች የሚገኙና ግንባታቸው የተጀመሩ ስታዲየሞች መጓተት ኢትዮጵያም የኬንያ  ዕጣ ፋንታ እንዳይደርሳት የሚሰጉ አሉ፡፡ የአፍሪካ የእግር ኳስ ውድድሮችን ለማሰናዳት ጥያቄ ስታቀርብ የነበረችው ኢትዮጵያ፣ እንደ አፍሪካ ዋንጫ ያሉ ውድድሮችን ለማሰናዳት ቻንን በአግባቡ መጠቀም እንዳለበትና አቅሟን ማሳየት እንደሚገባትም ይታመናል፡፡ በተለይ በሁሉም ክልል ከተሞች ውስጥ ግንባታቸው ተጀምሮ ግን ደግሞ የተረሱ ስቴዲየሞችና ሙሉ በሙሉ ያልተጠናቀቁትን የማጠናቀቅ፣ ስፖርቱን ከማነቃቃት ባሻገር የከተሞችን የገበያና የቢዝነስ እንቅስቃሴ ለማስፋፋት እንዲህ ያለው የስፖርት ውድድር ትልቅ ጥቅም እንደሚያስኝ ይገመታል፡፡

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የአመራሮች የምርጫ ማስፈጸሚያ መመሪያ ከዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) የተላከ ሲሆን፣ ይህንን መመሪያ ለማጽደቅና የምርጫ አስፈጻሚ ኮሚቴ ለመምረጥ፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔውን ሚያዝያ 27 ቀን 210 ዓ.ም. በአዲስ አበባ እንደሚያካሂድ ተገልጿል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...