Sunday, April 21, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበ18 ወራት ይጠናቀቃል የተባለው የሽሮሜዳ - ኪዳነ ምሕረት መንገድ ግንባታ በነዋሪዎች ላይ...

በ18 ወራት ይጠናቀቃል የተባለው የሽሮሜዳ – ኪዳነ ምሕረት መንገድ ግንባታ በነዋሪዎች ላይ ሥጋት ፈጥሯል

ቀን:

‹‹በሁለት ወራት ውስጥ ለመጨረስ በትጋት እየሠራን ነው››

የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን 

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በመገንባት ላይ የሚገኘው ከሽሮሜዳ እስከ ሃመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ያለው 2.1 ኪሎ ሜትር መንገድ ግንባታ በ18 ወራት ውስጥ ይጠናቀቃል ቢባልም፣ ከሁለት ዓመታት በላይ መፍጀቱንና ለአካባቢው ነዋሪዎች ሥጋት መፍጠሩ ተገለጸ፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ከሁለት ዓመታት በፊት በየማነ ግርማይ የመንገድ ሥራ ተቋራጭ በ208 ሚሊዮን ብር ወጪ ለማስገንባት የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን ውል የገባ ቢሆንም፣ የሥራ ተቋራጩ ባለቤት በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው እስከታሰሩበት ነሐሴ ወር 2009 ዓ.ም. ድረስ፣ ነባር መተላለፊያ መንገዱንና ግራ ቀኙን ከማረስ ባለፈ ግንባታው በበቂ ሁኔታ አለመከናወኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

አቶ በቀለ ደጀኔና አቶ ማናየ ናደው የተባሉ የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት፣ መንገዱ መቆፋፈሩንና በተቀመጠለት ጊዜ አለመጠናቀቁ ችግር ፈጥሮባቸው ከርሟል፡፡ መንገዱ በጣም ጠባብ ስለነበር መስፋፋቱንና ልማቱን ደግፈው፣ በአካባቢው የነበሩ ቤቶች በፍጥነት እንዲነሱና ሥራው እንዲጀመር የራሳቸውን አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡

ነገር ግን ላለፉት ሁለት ዓመታት በተለይ ዝናብ ባካፋ ቁጥር ልጆቻቸው የትምህርት ቤት መግቢያና መውጫ አጥተው ሲሰቃዩ መክረማቸን አስረድተዋል፡፡ የአካባቢው አፈር ትንሽ ዝናብ ሲነካው ቶሎ ስለሚቀልጥ፣ በተለይ ለአቅመ ደካሞችና ለሕፃናት ከፍተኛ ችግር መፍጠሩን ጠቁመዋል፡፡ በርካታ ምዕመናን ለጠበልና ቤተ ክርስቲያኗን ለመሳለም እንደ ልብ መሄድ እንዳልቻሉ ገልጸው፣ በተለይ በአሁኑ ጊዜ እጅግ ከፍተኛ ጥልቀት ያለው ጉድጓድ ተቆፍሮ ሳይሞላ በመቅረቱ፣ ክረምቱ በዚሁ ከገባ በጎርፍ ተንዶ ነዋሪዎችን ይጨርሳል የሚል ሥጋት እንዳደረባቸው አስረድተዋል፡፡ በሕዝብና በመንግሥት ወጪ የተገዙ ብረቶችና የተለያዩ የግንባታ ግብዓቶችም በየመንገዱ ዳርና ዳር ተጥለው እየተበላሹ በመሆኑ የሚመለከተው አካል አፋጣኝ ዕርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል፡፡

ነዋሪዎቹ ያነሱትን ጥያቄ በሚመለከት ማብራሪያ እንዲሰጡ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ አዲስ ይርጉ (ኢንጂነር) እንደገለጹት፣ መንገዱ ለየማነ ግርማይ ሥራ ተቋራጭ በ208 ሚሊዮን ብር ተሰጥቶ ነበር፡፡ ኮንትራክተሩ በገጠመው ችግር ምክንያት ፕሮጀክቱ በተያዘለት ጊዜ ሊጠናቀቅ አልቻለም፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ከኮንትራክተሩ ከተረከበው ገና ሦስት ወሩ መሆኑን፣ ባለፉት ሦስት ወራት የግንባታ ዕቃዎችን ለማቅረብና የተለያዩ ግዥዎችን ለመፈጸም ሲንቀሳቀስ እንደነበር፣ አሁን ግን ሁሉም ነገር ተጠናቆ ወደ ሥራ በመገባቱ፣ በቀጣይ ሁለት ወራት ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ለማጠናቀቅ እየተሠራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በቀጣይ ሁለት ወራት ውስጥ ከፊል አስፋልትና ሙሉ በሙሉ የኮንክሪት ሙሌት ሥራ ለማጠናቀቅ የተቻለውን ሁሉ እያደረጉ በመሆኑ፣ የአካባቢው ነዋሪዎችም ሆኑ የመንገዱ ተገልጋይ ኅብረተሰብ ሥጋት እንዳይገባቸው ጠይቀዋል፡፡ ከተቋራጩ የተረከቡት የ163 ሚሊዮን ብር ሥራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡   

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰው መሆን ምንድን ነው? ቅርስና ማኅበራዊ ፍትሕ

በሱራፌል ወንድሙ (ዶ/ር) ዳራ ከጎራዎች፣ ከመፈራረጅ፣ ነገሮችን ከማቅለልና ከጊዜያዊ ማለባበስ ወጥተን...

ኢኮኖሚው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሳት ያሠጋል

በጌታቸው አስፋው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሱ የሚያሠጉኝ አንድ ሁለት ብዬ ልቆጥራቸው የምችላቸው...

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ትግል በሕግ አምላክ ይላል

በገነት ዓለሙ የአገራችንን ሰላም፣ የመላውን ዓለም ሰላም ጭምር የሚፈታተነውና አደጋ...

በሽግግር ፍትሕ እንዲታዩ የታሰቡ የወንጀል ጉዳዮች በልዩ ፍርድ ቤት ሳይሆን በልዩ ችሎት እንዲታዩ ተወሰነ

የኤርትራ ወታደሮች በሌሉበትም ቢሆን ይዳኛሉ ተብሏል በፅዮን ታደሰ የሽግግር ፍትሕ የባለሙያዎች...