Wednesday, December 7, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊቤቶች ኮርፖሬሽን ለመንግሥት ሠራተኞች የሚገነባውን አፓርታማዎች ዲዛይን ይፋ አደረገ

  ቤቶች ኮርፖሬሽን ለመንግሥት ሠራተኞች የሚገነባውን አፓርታማዎች ዲዛይን ይፋ አደረገ

  ቀን:

  ባለፈው ዓመት አጋማሽ በድጋሚ የተቋቋመው የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ለፌዴራል መንግሥት ተሿሚዎችና ሠራተኞች አፓርታማዎች ለመገንባት የተለያዩ ዲዛይኖችን ይፋ አደረገ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ለራሱ ሠራተኞች ብቻ በኪራይ የሚተላለፉ አፓርታማዎች ግንባታ በይፋ አስጀምሯል፡፡

  በተለያዩ የመዋቅር ለውጦች አልፎ ጥር 26 ቀን 2009 ዓ.ም. በድጋሚ የተቋቋመው የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን፣ በአዲስ አበባ ከተማ 16 ሺሕ ቤቶችን ለመገንባት ዕቅድ ይዟል፡፡

  ኮርፖሬሽኑ ጥር 4 ቀን 2010 ዓ.ም. የአፓርታማዎቹን ዲዛይን ክለሳ፣ የአዳዲስ ዲዛይኖችና የአፈር ምርመራ ሥራዎችን ከሚሠሩለት ኖሚ ኢንጂነሪንግና ጂአይ አማካሪ ድርጅቶች ጋር ስምምነት ተፈራርሞ ወደ ሥራ ገብቷል፡፡

  በዚህ መሠረትም ከስምንት እስከ 21 ወለል ያላቸው አፓርታማዎች ዲዛይን የተሠራ ሲሆን፣ የግንባታ ቦታ ዝግጅትም እየተገባደደ መሆኑ ተገልጿል፡፡ ቤቶች ኮርፖሬሽን የሚገነባቸውን አፓርታማዎችን በተለይ ለፌዴራል መንግሥት ሠራተኞችና ተሿሚዎች በኪራይ የሚተላለፉ ቤቶችን የመገንባት ዕቅድ የያዘ ሲሆን፣ ከዚህ በተጨማሪ በመንግሥት ውሳኔ ለሽያጭ የሚያቀርባቸው ቤቶችም እንደሚኖሩም ታውቋል፡፡

  ይህ ተቋም የኪራይ ቤቶች አስተዳደር በሚባልበት ወቅት ከአሥር ሺሕ ቤቶች በላይ የገነባ ሲሆን፣ ከመንግሥት ለውጥ በኋላ ወደ መኖርያ ቤት ግንባታ ለመግባት ተደጋጋሚ ሙከራዎች ቢያደርግም ከመንግሥት ፈቃድ ሳያገኝ ቀርቷል፡፡

  በቅርቡ እንደገና ሲቋቋም ወደ ቤቶች ግንባታ እንዲገባ የተፈቀደለት ሲሆን፣ ሰፋፊ ቦታዎች ላይ ያረፉ ቪላዎችን በማፍረስ ግንባታ ለመጀመር የመጨረሻ ደረጃ ላይ መድረሱ ተመልክቷል፡፡

  ከፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በተጨማሪ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ ለራሱ ሠራተኞች ብቻ በኪራይ የሚተላለፉ ቤቶችን መገንባት ጀምሯል፡፡ ከንቲባ ድሪባ ኩማ ቅዳሜ ሚያዝያ 13 ቀን 2010 ዓ.ም. አራት ኪሎ ባሻ ወልዴ ችሎት በመገንባት ላይ ያሉትን አፓርትመንቶች ከመጎብኘታቸው በተጨማሪ፣ ለአዳዲስ አፓርታማዎች ግንባታ የመሠረት ድንጋይ አኑረዋል፡፡

  በ335 ሚሊዮን ብር ወጪ በአራት ኪሎና በገላን ሳይቶች በሁለት ምዕራፍ 1,718 ቤቶች ይገነባሉ ተብሏል፡፡ በአሁኑ ወቅት በአራት ኪሎ የተጀመሩት አፓርታማዎች የግንባታ አፈጻጸም 22 በመቶ መድረሱን ከንቲባ ድሪባ በጉብኝቱ ወቅት ገልጸዋል፡፡

  ሁለቱም መንግሥታዊ ተቋማት ትኩረት ያደረጉት ለመንግሥት ሠራተኞች መኖርያ ቤት ማቅረብ ላይ ሲሆን፣ ይህ ሊሆን የቻለውም የመንግሥት ሠራተኞች ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው በመሆኑ ተረጋግተው ሥራቸው ላይ ማተኮር ተስኗቸዋል በሚል መሆኑ ሲገለጽ ቆይቷል፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  የኢትዮጵያና የሩሲያ የንግድ ልውውጥ በጦርነቱ ምክንያት ማሽቆልቆሉ ተገለጸ

  ባለፉት አሥር ወራት በኢትዮጵያና በሩሲያ መካካል የነበረው የንግድ ልውውጥ...

  ዳግም ነፍስ የዘራው የተማሪዎች ማርች ባንድ

  የሙያው ፍቅር ያደረባቸው ገና በልጅነታቸው ነው፡፡ በ1970ዎቹ መጀመርያ፣ ለቀለም...

  በስንደዶና ሰበዝ የተቃኘው ጥበብ

  በአንዋር አባቢ ተወልዳ ያደገችው መሀል አዲስ አበባ አራት ኪሎ ነው፡፡...

  አዲስ ጥረት የሚጠይቀው  ኤችአይቪ  ኤድስን  የመግታት  ንቅናቄ

  ‹‹ኤችአይቪ በመላው ዓለም  በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን የሚያጠቃ ዋነኛ የሕዝብ...