Thursday, June 13, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ስፖርትጣዕም ያጣው የ‹‹ሸገር ደርቢ›› ፉክክር

ጣዕም ያጣው የ‹‹ሸገር ደርቢ›› ፉክክር

ቀን:

የኢትዮጵያ እግር ኳስ የሜዳ ውሎዎችና ክንውኖች ሥርዓት አልበኝነት ከነገሠባቸው ሰነባብተዋል፡፡ ለመካሪም ለዘካሪም የሚረቱ አልሆኑም፡፡ ሊጉን በበላይነት የሚያስተዳድረው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን፣ በሜዳ ላይ በሚታዩ የስፖርታዊ ጨዋነት ጥሰቶችና የዲሲፕሊን ግድፈቶች ላይ ቆንጠጥ ያሉ ዕርምጃዎችን መውሰድ ቢጀምርም፣ ድርጊቶቹ ሊገቱ ወይም አደብ ሊገዙ አልቻሉም፡፡

‹‹አበጃችሁ›› የተባሉ ይመስል ደጋፊዎች ጎራ ለይተው በየመንገዱ መተናነቃቸውን አልተውም፡፡ ከሰሞኑ የታየውም ይኼው ነው፡፡ ለዚህ ማሳያው ደግሞ ለአራት አሥርታት ያህል በተቀናቃኝነታቸው የ‹‹ሸገር ደርቢ›› በመባል በሚታወቁት፣ የቅዱስ ጊዮርጊስና የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለቦች ጨዋታ ወቅት የታየው ይጠቀሳል፡፡ ከሜዳ ላይ ትንቅንቃቸው ባሻገር በደጋፊዎቻቸው መካከል ሰሞኑን የታየው የደጋፊዎች የስፖርታዊ ጨዋነት ችግር፣ አንጋፋ ተመልካቾችን ያሳዘነ ነበር፡፡ ድርጊቱ በዋናነት የተከሰተው የሁለቱ ቡድኖች ደጋፊዎች፣ ለወትሮው ሜዳ ውስጥ ያበቃ የነበረው የቃላት ልውውጥና የስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል፣ ከሜዳ ውጪም ተደግሞ የአደባባይ ትዕይንት መሆን በመጀመሩ ነው፡፡  

ሰኞ ሚያዝያ 15 ቀን 2010 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ስቴዲዮም የተካሄደው የቅዱስ ጊዮርጊስና የኢትዮጵያ ቡና ጨዋታ ተጀምሮ እስኪያልቅ ውኃ፣ ውኃ የሚል ጣዕም አልባና ለደጋፊው የማይመጥን እንደነበር የሁለቱም ቡድኖች ደጋፊዎች ያምናሉ፡፡ ይህንኑ ተከትሎም ይመስላል በርካቶች ከጨዋታው ይልቅ ትኩረታቸው ወደ መበሻሸቁና መናቆሩ ያዘነበለው በማለት፣ አስተያየታቸውን የገለጹት ደጋፊዎች ሁኔታውን የገለጹት፡፡

- Advertisement -

በብሔራዊ ፌዴሬሽኑ አማካይነት ከሁለት አሥርታት በላይ በዳኝነትና በጨዋታ ታዛቢነት ሲያገለግሉ መቆየታቸውን የገለጹትና ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ ባለሙያ፣ ‹‹የሁለቱን ክለቦች ጨዋታ በተለይም ፕሪሚየር ሊጉ ከተጀመረ ከ1990 ዓ.ም. ጀምሮ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እያለሁ እንኳ አምልጦኝ አያውቅም፤›› በማለት አስተያየታቸውን ይጀምራሉ፡፡ ‹‹እስከ 1990ዎቹ መጨረሻ ድረስ የነበረው የተቀናቃኝነት ስሜት አጓጊና የማይሰለች ከመሆኑ ጎን ለጎን፣ ሜዳ ላይ የሚታዩ ክህሎቶችም ልዩ ነበሩ፡፡ በዚያን ወቅት የነበረው የአልሸነፍ ባይነት፣ የሜዳ ውስጥ ታክቲክና ቴክኒክ አሁን እንዲህ መውረዱ ሳያንስ፣ በደጋፊ ስም ለሰላማዊ ሰዎች እንቅስቃሴ እንቅፋት መሆኑ ያሳዝናል፤›› ይላሉ፡፡

ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ከስፖርታዊ ጨዋነት ጋር በተያያዘ ለሚፈጠሩ ችግሮች የዲሲፕሊን ዕርምጃዎች እየወሰደ እንደሚገኝ የሚናገሩት አስተያየት ሰጪው፣ ‹‹ውሳኔዎቹ ግን የእግር ኳሱን የዲሲፕሊን መመርያና ደንብ መነሻ ከማድረግ ይልቅ፣ በሰዎች ተፅዕኖ በመሆኑ ወጥነት የሌላቸው፣ በተመሳሳይ የዲሲፕሊን ጥሰቶች አንዱን እንደ ልጅ ሌላውን ደግሞ የእንጀራ ልጅ በሚያስመስል አኳኋን ውሳኔዎችን ማሳለፍ፣ ይህም ሳያንስ አንዳንዶቹ ውሳኔዎች በየትኛው የዲሲፕሊን መመርያ እንደተወሰኑ እንኳ ሳይታወቅ ውሳኔን በውሳኔ መሻርና ክለቦችን ማበላለጥ የተቋሙ መለያ መሆኑ፣ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ተዓማኒነት እንዳይኖረው አድርገዋል፤›› በማለት የተቋሙን የፍትሕ ሥርዓት ክፍተት ይተቻሉ፡፡ በቅርቡ በሜዳ ውስጥ ተጫዋቾችና አሠልጣኞች በፈጸሟቸው የስፖርታዊ ጨዋነት ግድፈቶች እንደ ወልድያ ያሉት ክለቦች ላይ ጠበቅ ያሉ ዕርምጃዎችን ፌዴሬሽኑ መውሰዱ ይታወሳል፡፡ ዕርምጃዎቹ ግን የዲሲፕሊን ግድፈቶቹን ለመቀነስ ጉልበት ያገኙ አልመሰሉም፡፡ ከሜዳ ውጪም ግጭቶችና አምባጓሮዎች መዛመታቸውን እንደቀጠሉ እየታየ ነው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...