Wednesday, February 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየኢንቨስትመንት ኮሚሽነሩ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሆነው ተሾሙ

የኢንቨስትመንት ኮሚሽነሩ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሆነው ተሾሙ

ቀን:

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር በመሆን ላለፉት አምስት ዓመታት ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ ፍጹም አረጋ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ተደርገው ተሾሙ፡፡

አቶ ፍጹም በአዲሱ ሥልጣናቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ጽሕፈት ቤት ኃላፊ በመሆን፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩን እንቅስቃሴዎች የመምራትና የማደራጀት ሥራዎችን የመወጣት ኃላፊነት እንደሚይዙ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ሹመቱን በተመለከተ አቶ ፍጹም ለሪፖርተር ሹመቱን አረጋግጠው፣ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡ አቶ ፍጹም የተሾሙበትን ኃላፊነት በበላይነት የሚመሩት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤትና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት ወ/ሮ ደሚቱ ሐምቢሳ ናቸው፡፡

አቶ ፍጹም ቀደም ብሎ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ይሠሩ የነበረ ሲሆን፣ በኋላም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ፣ በተጨማሪም የአዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ኤጀንሲ ኃላፊ በመሆን አገልግለዋል፡፡ ላለፉት አምስት ዓመታት ደግሞ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽንን በኮሚሽነርነት ሲመሩ ቆይተዋል፡፡

ሌላዋ ተደራቢ ኃላፊነት የተሰጣቸው ደግሞ ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረ እግዚአብሔር ናቸው፡፡ ወ/ሮ ፈትለወርቅ ባለፈው ሳምንት በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ዋና አስተባባሪነት በተጨማሪ፣ የኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሆነው የድርጅቱን የዕለት ተዕለት ተግባር የማስፈጸም ኃላፊነት እንደተሰጣቸው የሪፖርተር ምንጮች ገልጸዋል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የገጠር መሬት ማሻሻያና የመሬት ባለቤትነት ጥያቄ በኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ ከቅርብ ወራት ወዲህ መሬትን በተመለከተ ጠንከር ያሉ የለውጥ...

በፖለቲከኞች እጅ ያለው ቁልፍ

ኢትዮጵያ በተለይ ካለፉት አምስት ዓመታት ወዲህ ሰላሟ መረጋጋት አቅቶታል፡፡...

የኤክሳይስ ታክስ ረቂቅ አዋጅ ፓርላማው ያፀደቀውን አዋጅ የሚጥሱ ድንጋጌዎችን በማካተቱ እንዳይፀድቅ ተጠየቀ

ሰሞኑን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የኤክሳይስ ታክስ ማሻሻያ...

በፀጥታ ችግር ሳቢያ ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው አማራ ክልል የገቡ ዜጎች ቁጥር 800 ሺሕ መድረሱ ተነገረ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 112 ሺሕ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ...