Tuesday, July 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናምስክሮች ለመስማት የቀጠሩትን መዝገብ ሳይሰሙ ውሳኔ ሰጥተዋል የተባሉ ዳኛ ከሥራቸው ተሰናበቱ

ምስክሮች ለመስማት የቀጠሩትን መዝገብ ሳይሰሙ ውሳኔ ሰጥተዋል የተባሉ ዳኛ ከሥራቸው ተሰናበቱ

ቀን:

ከሳሽና ተከሳሽ የሚከራከሩበትን የክስ መዝገብ በመመርመር ላይ የነበሩ የአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤት ዳኛ፣ የግራ ቀኙን ተከራካሪ ወገኖች ምስክሮች ለመስማት የሰጡትን ቀጠሮ ምስክሮች እንደተሰሙ አድርገው ውሳኔ መስጠታቸው በመረጋገጡ ከዳኝነት ሥራቸው ተሰናበቱ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ሐሙስ ሚያዝያ 18 ቀን 2010 ዓ.ም. ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ባቀረበው የውሳኔ ሐሳብ እንዳብራራው፣ በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ምድብ ችሎት ዳኛ አቶ በሪሁ ታረቀኝ፣ የዲሲፕሊን ክስ ቀርቦባቸዋል፡፡ የቀረበባቸውም ክስ በወ/ሮ እታጉ ፍሬውና በአቶ ተስፋዬ ገብረ ፃዲቅ መካከል በሚደረገው ክርክር የግራ ቀኝ ምስክሮች ለመስማት ቀጠሮ የያዙ ቢሆንም፣ ምስክሮችን ከመስማታቸው በፊት ውሳኔ መስጠታቸውን ጉባዔው አስታውቋል፡፡ ዳኛው ያላግባብ ተደጋጋሚ ረዥም ቀጠሮ በመስጠት፣ ጉዳዩ እንዲጓተት በማድረግና በባለጉዳዮችም ላይ በደል ማድረሳቸውን አክሏል፡፡

ጉባዔው በአዋጅ ቁጥር 4/95 አንቀጽ 8(2) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት፣ በዳኛው ላይ የቀረበባቸውን የዲሲፕሊን ክስ ከዳኝነት የሙያ አፈጻጸምና ሥነ ምግባር አንፃር ሲመረምረው የሚያስከስስ ሆኖ ስላገኘው፣ ክሱ እንዲደርሳቸውና ማስረጃቸውን ንዲያቀርቡ ማድረጉን ገልጿል፡፡ ዳኛውም የክስ ሰነዱ ከእነ ማስረጃው ከደረሳቸው በኋላ፣ ምላሻቸውን ከእነ ማስረጃቸው ማቅረባቸውን አክሏል፡፡ በጽሑፍ ካቀረቡት መልስና ማስረጃ በተጨማሪ፣ በአካል በጉባዔው ፊት ቀርበው ክርክራቸውን ማሰማታቸውን ጠቁሟል፡፡ ከጉባዔው አባላት ለቀረቡላቸውም ጥያቄዎች ማብራሪያ መስጠታቸውን አስረድቷል፡፡  

ጉባዔው ዳኛው ከሰጡት መልስና ካቀረቡት ማስረጃ በተጨማሪ ክርክር የተካሄደበትን መዝገብ በማስቀረብ ባደረገው ምርመራ፣ ዳኛው ምስክሮች እንደተሰሙ አድርገው በሰጡት ውሳኔ የተሰሙት ምስክሮች የተከሳሽ አቶ ተስፋዬ ገብረ ፃዲቅ እንጂ፣ ወ/ሮ እታጉ ፍሬው የቆጠሯቸው ምስክሮች እንዳልተሰሙ ማረጋገጡን ጠቁሟል፡፡ ምስክሮቹ ያልተሰሙበትን ምክንያትም በመዝገቡ ላይ አለማስፈራቸውን አክሏል፡፡ ነገር ግን ዳኛው የሰጡት ውሳኔ በሰበር ሰሚ ችሎት ተሽሮ፣ የሥር ፍርድ ቤት ምስክሮቹን በመስማት እንዲወስን ትዕዛዝ በመስጠት፣ መዝገቡን ተመላሽ ማድረጉንም ጉባዔው ማረጋገጡን በውሳኔ ሐሳቡ አስፍሯል፡፡

ጉባዔው ዳኛው ለባለጉዳዮች አላስፈላጊ ቀጠሮ በተደጋጋሚ በመስጠት እንግልት ስለመፍጠራቸው ባደረገው ምርመራ፣ ዳኛው ያለ በቂ ምክንያትና በቢፒአር ጥናት ከተቀመጠው አሠራር ውጪ እስከ አንድ ወር የሚደርስ ረዥም ቀጠሮ መስጠታቸውን፣ ‹‹መዝገቡ አልተመረመረም›› በማለት መዝገቦች ውሳኔ ሳያገኙ ረዥም ጊዜ በተገልጋዮች ላይ እንግልትና መጉላላት ማድረሳቸውን ማረጋገጡን ገልጿል፡፡

ዳኛ የሚሰጠው ፍርድ፣ ውሳኔ፣ ትዕዛዝና ብይን ሕጎችን በትክክል በሥራ ላይ ማዋል ተቀዳሚ ተግባሩ መሆኑን የጠቆመው ጉባዔው፣ በተጨማሪም ዳኞች የሚቀርብላቸውን ጉዳይ ቀጠሮ ሳያበዙ በተቻለ ፍጥነት መቁረጥና ሳይጓተት ውሳኔ መስጠት እንዳለባቸው፣ ጉባዔው ባወጣው የሥነ ምግባር ደንብ ላይ መቀመጡን አብራርቷል፡፡ ዳኛው በደንብ ቁጥር 32(5) ተጨማሪ የዲሲፕሊን ክስ የቀረበባቸው መሆኑንና ከሌሎቹ ክሶች ጋር ተደማምሮ በሥነ ምግባር ደንቡ ቁጥር 32(6) መሠረት የዲሲፕሊን ጥፋት መፈጸማቸው መረጋገጡን ገልጿል፡፡

የተጠቀሱትን የሥነ ምግባር ደንብ ቁጥር 32(5 እና 6) በመተላለፋቸው ከባድ የዲሲፕሊን ጥፋት መፈጸማቸው በመረጋገጡ፣ ጉባዔው በሙሉ ድምፅ ጥፋተኛ መሆናቸውን ወስኖ ምክር ቤቱ እንዲያፀድቅለት አቅርቧል፡፡ በመሆኑም በሕገ መንግሥቱ ዳኞች ነፃነታቸው የተረጋገጠ ቢሆንም፣ የዲሲፕሊን ጥፋት መፈጸማቸው ሲረጋገጥ ተጠያቂ እንደሚሆኑ በመደንገጉ፣ ዳኛው አቶ በሪሁ ታረቀኝ በፈጸሙት ከባድ የዲሲፕሊን ጥፋት ምክንያት ከዳኝነት ሥራቸው እንዲሰናበቱ፣ ጉባዔው በአዋጅ ቁጥር 4/95 አንቀጽ፣ 8(2) መሠረት ያቀረበውን ውሳኔ ምክር ቤቱ በሙሉ ድምፅ ደግፎ በማፅደቁ ከሥራቸው ተሰናብተዋል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...