Thursday, September 21, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔውን አሰናብቶ በምትካቸው መረጠ

ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔውን አሰናብቶ በምትካቸው መረጠ

ቀን:

ላለፉት ሦስት ዓመታት በፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔነት ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ ያለው አባተ ያቀረቡትን መልቀቂያ የተቀበለው የፌዴሬሽን ምክር ቤት፣ በምትካቸው ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂምን አፈ ጉባዔ አድርጎ መርጧል፡፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሰኞ ሚያዝያ 22 ቀን 2010 ባካሄደው መደበኛ ጉባዔው፣ ላለፉት ዓመታት ሲያገለግሉ የነበሩት አፈ ጉባዔ ያለው አባተ፣ ከአፈ ጉባዔነታቸው መነሳት እንደሚፈልጉ ያቀረቡትን ጥያቄ ተቀብሏል፡፡

አቶ ያለው ለምክር ቤቱ ባቀረቡት ጥያቄ ከአፈ ጉባዔነት ኃላፊነታቸው መነሳት እንደሚፈልጉ፣ ይህንንም ለፖለቲካ ፓርቲያቸው (ብአዴንና ኢሕአዴግ) አሳውቀው ተቀባይነት ያገኙ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ በመሆኑም ምክር ቤቱም እንዲቀበላቸው ጠይቀዋል፡፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤትም ጥያቄውን ወዲያው ተቀብሎ በምትካቸው እንዲሰየሙ የታጩት፣ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም ለምክር ቤቱ እንዲተዋወቁ አድርጓል፡፡

በዚህም መሠረት ወ/ሮ ኬሪያ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ሆነው ተመርጠዋል፡፡ ወ/ሮ ኬሪያ ትግራይ ክልልንና ሕወሓትን የሚወክሉ ሲሆኑ፣ ወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ከመምጣታቸው አስቀድሞ የትግራይ ክልል ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊ ነበሩ፡፡

ወ/ሮ ኬሪያ ከቀድሞዋ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ወ/ሮ አልማዝ መኮ ቀጥሎ ሁለተኛዋ የምክር ቤቱ ሴት አፈ ጉባዔ ሆነዋል፡፡ ከሁለት ሳምንት በፊት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአቶ አባዱላ ገመዳ ምትክ ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚልን በአፈ ጉባዔነት መምረጡ የሚታወስ ሲሆን፣ ሁለቱም የአገሪቱ ምክር ቤቶች በሴት አፈ ጉባዔ የሚመሩበት የታሪክ አጋጣሚም ተከስቷል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ሪፖርት ምን ይዟል?

ለአሜሪካ ድምፅ አማርኛ ዝግጅት የስልክ አስተያየት የሰጡ አንድ የደንበጫ...

መንግሥት በአማራ ክልል ለወደሙ የአበባ እርሻዎች ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት በቢዝነስ...

አምናና ዘንድሮ!

እነሆ መስከረም ጠብቶ በአዲስ መንፈስ ተሞልተን መንገድ ጀምረናል። ‹‹አዲስ...