Saturday, September 30, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ሥነ ፍጥረትዐዞ እና መንጋጋው

ዐዞ እና መንጋጋው

ቀን:

ዐዞ የባሕር አውሬ ሆደ መጋዝ ጋድሚያ እንቅልፋም፤ ያገኘውን ሰውና እንስሳ በዥራቱ እየጠለፈ ወደ ባሕር ይዞ የሚገባ ብሎ የሚፈታው የአለቃ ደስታ ተክለወልድ ዐዲስ ያማርኛ መዝገበ ቃላት ነው፡፡ ልጇን ዐዞ የበላባት እናት ‹‹ግባተ መሬቱን አትድገሙ እናንተ፤ ታዞ ሂዷል እንጂ ልጄ መቼ ሞተ›› ስትል እህት ደግሞ ‹‹ላንድ ቀን ትእዛዝ ሰዉ ይመረራል፤ የኔ ወንድም ታዞ ዓባይ ላይ ይኖራል፤›› ብላ አንጎራጉራለች፡፡

በንቁ! ድረ ገጽ  የ2015 ዕትም እንደተጻፈው፣ የዐዞ መንጋጋ በአሁኑ ጊዜ በምድር ላይ ከሚኖሩ አራዊት ሁሉ ይበልጥ ከፍተኛ የመቀርጠፍ ኃይል አለው። ለምሳሌ ያህል፣ አውስትራሊያ አቅራቢያ በጨዋማ ውኃ ውስጥ የሚኖረው ዐዞ የመንከስ ኃይሉ ከአንበሳ ወይም ከነብር ጋር ሲወዳደር ሦስት እጥፍ ያህል ከፍ ያለ ነው።

 የዐዞ መንጋጋ ትንሽ ነገር እንኳ ሲነካው የሚሰማው ወዲያውኑ ነው፤ ሌላው ቀርቶ ከጣታችን ጫፍ ይበልጥ ቶሎ ይሰማዋል። የዐዞ መንጋጋ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ የስሜት ሕዋሳት አሉት። ዳንከን ሊች የተባሉ ተመራማሪ በዚህ ላይ ጥናት ካደረጉ በኋላእያንዳንዱ የነርቭ ጫፍ የሚወጣው በጭንቅላቱ ውስጥ ከሚገኝ ቀዳዳእንደሆነ አስተውለዋል። በመንጋጋው ውስጥ ያሉት ነርቮች በዚህ መንገድ መቀመጣቸው ምንም ነገር እንዳይጎዳቸው የሚያደርግ ከመሆኑም ሌላ የነርቭ ሴሎቹ አንድ ነገር ሲነካቸው ቶሎ እንዲሰማቸው ያስችላል፡፡

እንዲያውም በመንጋጋው ላይ ያሉ አንዳንድ ነርቮች አንድ ነገር ሲነካቸው የሚሰጡት ምላሽ በጣም ፈጣን ከመሆኑ የተነሳ በመሣሪያ እንኳ መለካት አይቻልም። በዚህም የተነሳ ዐዞ አፉ ውስጥ ያለ አንድ ነገር ምግብ ይሁን አይሁን በቀላሉ መለየት ይችላል። ይህም አንዲት ዐዞ ጫጩቶቿን በአፏ ይዛ ስትሄድ ተሳስታ እንኳ እንዳትጨፈልቃቸው ይረዳታል። የሚያስገርመው፣ የዐዞ መንጋጋ እጅግ ኃይለኛ የመቀርጠፍ ብቃትና ትንሽ ነገር ሲነካው ቶሎ የመለየት ችሎታን አጣምሮ የያዘ ነው።

spot_img
Previous article
Next article
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ

እሑድ ጠዋት መስከረም 13 ቀን 2016 ዓ.ም. የፋኖ ታጣቂዎች...

ብሔራዊ ባንክ ለተመረጡ አልሚዎች የውጭ አካውንት እንዲከፍቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈቀደበት መመርያና ዝርዝሮቹ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀምንና ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮችን...

እነ ሰበብ ደርዳሪዎች!

ከሜክሲኮ ወደ ዓለም ባንክ ልንጓዝ ነው። ሾፌርና ወያላ ጎማ...