Tuesday, July 16, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየመድኃኒቶች የመረጃ ሥርዓት ክፍተት

የመድኃኒቶች የመረጃ ሥርዓት ክፍተት

ቀን:

የመድኃኒቶች አመራረትና የተመረተበት አገር፣ እንዲሁም ተመርተው የመጨረሻው ተጠቃሚ ኅብረተሰቡ ዘንድ እስኪደርሱ ድረስ ያለው የመረጃ ልውውጥ እጅግ የተበጣጠሰ፣ ተመጋጋቢ ለመሆን የሚያስችለው ሥርዓት ያልተበጀለት መሆኑን በጤናው ዘርፍ ችግር እየፈጠረ እንደሚገኝ ታወቀ፡፡

አንድ መድኃኒት የት መመረቱን? እንዴት መጓጓዙን? አገር ውስጥ መቼ እንደ ገባ? ወደ የትኞቹ ተቋማት መሠራጨቱን፣ የትኛው ተቋም ለየትኛው ታካሚ መድኃኒቱን መቅረቡንና የመሳሰሉትን ጥያቄ በአግባቡ ለመመለስ  የሚያስችለው መረጃ የተሟላ አይደለም፡፡ ይህም ሁኔታ የመድኃኒቶቹን ደኅንነትና ጥራት ከማረጋገጥ አኳያ እጅግ ማነቆ ሆኖ እስከዛሬ ቆይቷል፡፡

እነዚህ ችግሮች በይበልጥ የሚጎዱት ኅብረተሰቡን ሲሆን፣ ደኅንነቱና ጥራቱ እንደዚሁም ምንጩ ያልታወቀ መድኃኒትን የኅብረተሰቡን ጤና እና ደኅንነት አደጋ ላይ እየጣለ እንደሚገኝ የምግብ፣ የመድኃኒት ጤና ነክ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን አስታውቋል፡፡ አንዳንድ አገሮች ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂን በመጠቀም አንድ መድኃኒት የት እንደተመረተ፣ የአገልግሎት ማብቂያ ጊዜው መቼ እንደሆነ፣ ሕጋዊ መዝገብ ቁጥሩ ምን እንደሆነ ለማወቅ የሚያስችል ሥርዓት ዘርግተው ስለሚሠሩ በዚህ ረገድ ሥጋት የለባቸውም፡፡ ይህም የኅብረተሰባቸውንም ጤናና ደኅንነት ለመጠበቅም እጅጉን ረድቷቸዋል፡፡

ኢትዮጵያም ይህ ዓይነቱን የተቀናጀ የመረጃ ሥርዓት ለመጠቀም የሚያስችላት ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት አዋቅራ፣ ለተግባራዊነቱም ክትትል የሚያደርግ አገር አቀፍ ኮሚቴ አቋቁማ ወደ ሥራ መግባቷን የኢትዮጵያ የምግብ፣ የመድኃኒትና ጤና ነክ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ የሁሉ ደነቀው ተናግረዋል፡፡

እንደ ዋና ዳይሬክተሩ ገለጻ፣ ኢትዮጵያ ይህንን ስትሠራ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ እንዲሆን መሥራት ያስፈልጋል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ሥርዓት የመዘርጋቷ ጉዳይ የኢትዮጵያ ብቻ ሆኖ ይቀራል፡፡ ከዚህ አኳያ በጉዳዩ ዙሪያ ተወያይቶ መፍትሔ መፍጠር እንደሚረዳ የታመነበት፣ በዋነኛነት አፍሪካ አገሮች የሚሳተፉበት የአፍሪካ የመድኃኒትና የሕክምና መሣሪያዎች ክትትልና ቁጥጥር ኮንፈረንስ አዲስ አበባ ውስጥ ለማካሄድ ዝግጅት ተጠናቋል፡፡

ከሚያዝያ 30 እስከ ግንቦት 3 ቀን 2010 ዓ.ም. ድረስ በሸራተን አዲስ በሚካሄደው አህጉራዊ ኮንፈረንስ ላይ 350 የሚሆኑ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ መድኃኒት አምራቾች፣ አስመጪዎችና ላኪዎች፣ የቴክኖሎጂ አቅራቢ ድርጅቶች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል፡፡

የኮንፈረንሱ ዓላማ የኢትዮጵያ መድኃኒት አስመጪዎች፣ የጤና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የሚገዙትን መድኃኒት ከመነሻ እስከ መድረሻቸው መከታተል የሚያስችላቸውን ሁኔታ መፍጠር ነው፡፡ የጤና አገልግሎት ግብዓቶችን የተመለከተ ዓለም አቀፍ ስታንዳርዶች ላይ ውይይት ይደረጋል፡፡

የመድኃኒት አስተዳደር ውጤታማነትና የሕሙማን ደኅንነት የሚያረጋግጡ ወጥነት ያላቸውን ደረጃዎች ለመቅረፅና ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያስችል ሥርዓት ከሌሎች አቻዎቻቸው ልምድ እንዲቀስሙ ያደርጋል፡፡  

ኮንፈረንሱ በጤና አገልግሎት፣ የመድኃኒትና የሕክምና መሣሪያዎች ክትትልና ቁጥጥር ላይ ወጥነት ያለው አሠራር መፍጠር የሚቻልበትን አማራጭ መፍትሔ የሚቀርብበት፣ አንዱ ከሌላው የሚማርበትና የልምድ ለውውጥ የሚደረግበት ይሆናል፡፡ የአገር ውስጥ የመድኃኒትና የሕክምና መሣሪያ አምራቾች ዓለም አቀፍ ስታንዳርዶችን ተከትለው የሚያመርቷቸውን መድኃኒቶች ወደ ሌሎች አገሮች በመላክ ተጠቃሚ እንዲሆኑም የራሱን ሚና ይጫወታል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሚዲያው በሕዝብ የህሊና ችሎት ከተዳኘ በቂ ነው!

መሰንበቻውን ድንገት ሳይታሰብ ያለ ማስጠንቀቂያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ...

የባህር በር ጉዳይ

በታምሩ ወንድም አገኘሁ ድሮ ድሮ ገና ልጅ ሆኜ ፊደል እንደቆጠርኩ...

አገሩ ፖለቲካዊ ስክነትና መደማማጥ ያስፈልገዋል

በንጉሥ ወዳጀነው    ኢትዮጵያ የሁላችንም የጋራ ቤት ነች፡፡ ‹‹ጥያቄዬ ተመለሰልኝ››፣...

የመንግሥት የሰብዓዊ መብት ተቋም ለምን የመንግሥት ሚዲያን ማስተማር አቃተው

በገነት ዓለሙ የአገራችን የ2016 የበጀት ዓመት መሰናበቻና የአዲሱ የ2017 በጀት...