Thursday, May 30, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናበሞያሌ ከተማ በተከሰተ ግጭት በሰው ሕይወት ላይ ጉዳት ደረሰ

በሞያሌ ከተማ በተከሰተ ግጭት በሰው ሕይወት ላይ ጉዳት ደረሰ

ቀን:

ከወራት በኋላ እንደገና ባገረሸው የሞያሌ የሰላም መደፍረስ መጠነ ሰፊ የሆነ ግጭት ተከስቶ፣ በሰው ሕይወት ላይ ጉዳት መድረሱን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስቱ አስታወቀ፡፡

ከዚህ ቀደም በየካቲት ወር በተመሳሳይ በዚሁ የድንበር ከተማ ተከስቶ በነበረው ግጭት፣ ዘጠኝ ንፁኃን ተገድለው ሌሎችም መቁሰላቸው ይታወሳል፡፡

እሑድ ሚያዝያ 28 ቀን 2010 ዓ.ም. እንደተከሰተ በተገለጸው በዚህ የሰላም መደፍረስ፣ ቁጥራቸው ይፋ ያልተደረገ ነገር ግን ከዚህ ቀደም ከነበረው ሊጨምር ይችላል ተብሎ በተገመተ ንፁኃን ዜጎች ላይ ሞትና የአካል ጉዳት ሳይደርስ አይቀርም ተብሏል፡፡

- Advertisement -

የኮማንድ ፖስቱ ሴክሬታሪያት ባወጣው መግለጫ፣ ‹‹በሞያሌ ከተማ ሚያዝያ 28 ቀን 2010 ዓ.ም. በተደራጀና በህቡዕ ዝግጅት በተደረገበት የጥፋት ተልዕኮ፣ በሁለት ጎራዎች የታጠቁ ኃይሎች መካከል ማኅበረሰቡን ዒላማ ያደረገ፣ በመጠኑም ሰፋ ያለ ግጭት ተከስቶ በሰው ሕይወት ላይ ጉዳት ደርሷል፤›› ብሏል፡፡

‹‹በዚህ ግጭት የዜጎች ሕይወት ጠፍቷል፣ የመቁሰል አደጋ ደርሷል፤›› ያለው ኮማንድ ፖስቱ፣ በምን ያህል ዜጎች ላይ የሞትና የመቁሰል አደጋ እንደደረሰ ይፋ ከማድረግ ተቆጥቧል፡፡

በተጨማሪም ጽሕፈት ቤቱ በህቡዕ የተደራጁ ሲል የገለጻቸውን የታጠቁ ኃይሎች ማንነት በመግለጫው ይፋ አላደረገም፡፡

በዚህ ድርጊት የተሳተፉና ከጀርባ ሆነው ድርጊቱን ሲመሩ የነበሩ ኃይሎችን የመለየትና የማጣራት ሥራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል፡፡

በአሁኑ ጊዜ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሕገወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውር በስፋት እየተካሄደ መሆኑን በመግለጽ፣ በሚያዝያ ወር ብቻ 142 ክላሽኒኮቭ ጠመንጃዎች፣ 88 ሽጉጦች፣ ኋላ ቀር መሣሪያዎች ከበርካታ ተተኳሾች ጋር፣ እንዲሁም 11 የእጅ ቦምቦች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ኮማንድ ፖስቱ አስታውቋል፡፡

በሞያሌ ከተማ ለተከሰተው ግጭትም ሕገወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውር አስተዋጽኦ እንደነበር በመግለጫው ተጠቁሟል፡፡ ለዚህም ሲባል ከመንግሥት በተሰጠ ትዕዛዝ የትጥቅ ማስፈታት እየተከናወነ ነው ሲል ኮማንድ ፖስቱ በመግለጫው አስታውቋል፡፡

በኦሮሚያ ክልል በጉጂ ዞን በሞያሌ ወረዳ በመከላከያ ሠራዊት አባላት በስህተት ተፈጽሟል ተብሎ በነበረው ጥቃት ምክንያት ከሞቱትና ከተጎዱት በተጨማሪ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ወደ ኬንያ መሰደዳቸው ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[የክቡር ሚኒስትሩ ባለቤት የኬንያው ፕሬዚዳንት ያስተላለፉትን መልዕክት ተመልክተው ባለቤታቸውን በነገር ይዘዋቸዋል]

የኬንያው ፕሬዚዳንት ከሕዝባቸው ለቀረበባቸው ቅሬታ የሰጡትን ምላሽ ሰማህ? እንኳን ምላሻቸውን...

የኢትዮ ኤርትራ ሰሞነኛ ሁኔታና ቀጣናዊ ሥጋቱ

“ግንቡን እናፍርስ ድልድዩን እንገንባ” የሚል ፖለቲካዊ መፈክር ጎልቶ በሚሰማበት፣...

ኦሮሚያ ባንክ ከተበዳሪ ደንበኞቼ ውስጥ 92 በመቶ የሚሆኑት አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ናቸው አለ

ኦሮሚያ ባንክ ለደንበኞቹ ከሰጠው ብድር ውስጥ ለአነስተኛና ለመካከለኛ ኢንተርፕራይዞች...

ሽቅብና ቁልቁል!

ጉዞ ከመገናኛ ወደ ሲኤምሲ ጀምረናል። ተሳፋሪዎች የዕለት ጉርሳቸውን መሸፈን...