ፋሺስት ጣሊያን በኢትዮጵያ ድል የተመታበት 77ኛ ዓመት ሚያዝያ 27 ቀን 2010 ዓ.ም. ተከብሯል፡፡ በዓሉ በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ አራት ኪሎ በሚገኘው ሚያዝያ 27 አደባባይ ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ (ዶ/ር) በተገኙበት በአርበኞች ሰልፍና በወጣቶች ትርዒት ተከብሯል፡፡ ፋሺስት ጣሊያን አዲስ አበባን በያዘበት ሚያዝያ 27 ቀን (1928 ዓ.ም.) በሕዝቡና በአርበኞች ተጋድሎ የኢትዮጵያ የድልን ቀን ሚያዝያ 27 ቀን (1933 ዓ.ም.) በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መበሰሩ ይታወቃል፡፡ ፎቶዎቹ የክብረ በዓሉን ልዩ ልዩ ገጽታ ያሳያሉ፡፡