Wednesday, July 24, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የንግድ ሚኒስቴር የዘጠኝ ወራት ሪፖርት ዛሬ ይፋ ይደረጋል

ተዛማጅ ፅሁፎች

  • ቡና በዘጠኝ ወራት ውስጥ ከ560 ሚሊዮን ዶላር በላይ አስገኝቷል

ንግድ ሚኒስቴር የአገሪቱን አጠቃላይ የዘጠኝ ወራት የወጪና ገቢ ንግድ አፈጻጸም ሪፖርት ለማሳወቅ ለረቡዕ ግንቦት 1 ቀን 2010 ዓ.ም. ቀጠሮ ቢይዝም፣ ከቡና ወጪ ንግድ የተመዘገበው የዘጠኝ ወራት አፈጻጸም ይፋ ተደርጓል፡፡ 

2010 በጀት ዓመት ከሐምሌ እስከ መጋቢት ወራት ውስጥ የታየው የቡና የወጪ ንግድ አፈጻጸምን በማስመልከት የቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ግብይትና ልማት ባለሥልጣን ይፋ ያደረገው መረጃ እንደሚያሳየው ለውጭ ገበያ ከቀረበው ቡና የተገኘው የውጭ ምንዛሪ ገቢ 560.24 ሚሊዮን ዶላር ነው፡፡  

ከሐምሌ እስከ መጋቢት 2010 ዓ.ም. የተመዘገበው የቡና ክንውን በመጠንና በገንዘብ ያሳየውን አፈጻጸም ባለሥልጣኑ ባስቀመጠው አኃዛዊ መረጃ መሠረት፣ በመጠን 159,652.78 ቶን ጥሬ ቡና ወደ ውጭ ተልኮ 560.24 ሚሊዮን ዶላር አስገኝቷል፡፡ ይህ አፈጻጸም ከባለሥጣኑ ዕቅድ አኳያ ሲነፃፀር በመጠን 95.19 በመቶ፣ በገቢ ረገድም 78.31 በመቶ አፈጻጸም የታየበት ስለመሆኑ ተጠቅሷል፡

በዚህ በጀት ዓመት እስከ መጋቢት ወር በነበረው የቡና አፈጻጸም ከ2009 ዓ.ም. ተመሳሳይ ወቅት ሲነፃፀርም በመጠን የ19,594.21 ቶን ወይም የ14 በመቶ እንዲሁም በገቢ በኩል የ14.4 ሚሊዮን ዶላር ወይም የ2.64 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን የባለሥልጣኑ መረጃ ይጠቁማል፡፡ ቡና ወደ ውጭ በብዛት ከተላከባቸው ወራት ውስጥ በኅዳር ወር የተመዘገበው ከዕቅዱም አኳያ በዘጠኝ ወራት ውስጥ በመጠን ከፍተኛ ውጤት በማሳየት የ115 በመቶ አፈጻጸም እንደተመዘገበ ተመልክቷል፡፡ በአንፃሩ በመጋቢት ወር የ69 በመቶ ዝቅተኛ  አፈጻጸም ሲመዘገብ፣ በገቢ ረገድ በነሐሴና በመስከረም ወራት የ92 በመቶ ከፍተኛ ውጤት መዘግቧል፡፡ በአንበመጋቢት ወር የ56 በመቶ ዝቅተኛ አፈጻጸም መመዝገቡን ባለሥልጣኑ ያሰራጨው መረጃ ይጠቁማል፡፡

ባለሥልጣኑ ይህን መረጃ ቢያቀርብም ዘንድሮ ከፍተኛ መጠን ያለው ቡና ለውጭ ገበያ እንዳልወጣ የሚናገሩ ላኪዎች አልታጡም፡፡ ይህ በመሆኑም ለዘንድሮ የታቀውን ገቢ ዝቅተኛ ሊያደርገው እንደሚችል ከወዲሁ አሥግቷል፡፡ ይህም ሆኖ ባለሥልጣኑ አነስተኛ አምራቾችን ጨምሮ ሁለት ሔክታርና ከዚያ በላይ የቡና እርሻ ላላቸው 248 ቡና አብቃዮች የላኪነት ፈቃድ መስጠቱ የሚታወስ ነው፡፡ ይህም የቡና የወጪ ንግዱን ለማስፋፋት ያለመ ዕርምጃ እንደሆነ መገለጹም አይዘነጋም፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች