Tuesday, November 29, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ስፖርትኢትዮጵያ ቡናና የእግር ኳስ ዳኞች እሰጣ ገባ

  ኢትዮጵያ ቡናና የእግር ኳስ ዳኞች እሰጣ ገባ

  ቀን:

  ታህሳስ 17 ቀን 2008 ዓ.ም. የደደቢት እግር ኳስ ክለብና የኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለብ ያደረጉት ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ የዕለቱ ኢንተርናሽናል ዳኛ የሠሩትን ስህተት በተመለከተ የኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለብ ታህሳስ 19 ቀን 2008 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

  በጋዜጣዊ መግለጫው የኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለብ በዳኝነቱ ዙሪያ መስተካከል ያለባቸው ነገሮች ካልተስተካከሉ ክለቡን ኪሳራ ላይ እንዳይወድቅ ስጋት እንዳለበት ጭምር ተነግሯል፡፡

  በተለይ የኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለብ በጨዋታ ደንብ መሠረት የሚመራ መሆኑን የክለቡ ሥራ አስኪያጅ አቶ ገዛኸኝ ወልዴ ተናግረዋል፡፡

  በዚሁ መሠረት ክለቡ አንድ ጨዋታ ለማድረግ አንድ ሚሊዮን ብር ወጪ እንደሚያደርግ፣ በአንጻሩ ጨዋታውን የሚመሩት ዳኞች በሚሠሩት ግልጽ ስህተት ክለቡ ማግኘት የሚችለውን ገቢም ሊያሳጣው የሚችልበት ደረጃ ላይ ስለመድረሱ አክለዋል፡፡

  እንደ ክለቡ ሥራ አስኪያጅ ከሆነ፣ ኢትዮጵያ ቡና ለረጅም ጊዜ በተለይ ልምድ ባላቸው ዳኞች ሳይቀር ተከታታይ በደል ይፈጸመበታል፡፡ በጉዳዩ ላይ ደብዳቤ ለፌዴሬሽኑ ቢያስገባም ሰሚ ማግኘት እንዳልቻለ ገልጸው ዳኞች የሚፈጽሙት ውሳኔ ትክክለኛ ባለመሆኑ ምክንያት በስታዲየም የተገኘውን ደጋፊዎችን ከፀጥታ ኃይሎች ጋር የማጋጨት ደረጃ መደረሱን ተናግረዋል፡፡

  ታህሳስ 4 2008 ዓ.ም. ከአዳማ ከነማ ጋር በተደረገው ጨዋታ የተፈጸመው የዳኝነት በደል እንዲሁም ቀደም ብሎ ሚያዝያ 28 ቀን 2005 ዓ.ም. ከመከላከያ ጋር በተደረገ ጨዋታ አስመልክቶ ለፌዴሬሽኑ ያስገባው ደብዳቤ ምላሽ እንዳልተሰጠው በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ አስታውቀዋል፡፡

  ባለፈው እሑድ በተደረገው የደደቢትና የኢትዮጵያ ቡና ጨዋታ ላይ የተካሄደው ኢንተርናሽናል ዳኛው ከዚህ ቀደም በብሔራዊ ሊግና በተለያዩ ጨዋታዎች ላይ ስህተት ሠርተው መታገዳቸውን ገልጸው፣ ኢትዮጵያ ቡናና ደደቢት በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ካሉ ክለቦች ተፎካካሪ መሆናቸው ከግምት ውስጥ በማስገባት ብቁ የሆነ ዳኛ ፌዴሬሽኑ መመደብ ክለቡ ሦስት ነጥብ እንዲያጣ ምክንያት ስለመሆኑ ጭምር ተናግረዋል፡፡

  ፌዴሬሽኑ ዳኛውን ከጨዋታው በኋላ ለአንድ ዓመት ከዳኝነት ያገዳቸው ሲሆን፣ እንደ ኢትዮጵያ ቡና ክለብ ውሳኔው ከጥፋቱ ጋር የሚጣጣም አይደለም፡፡ ሆኖ፣ ‹‹ፌዴሬሽኑ ወዲያው የወሰነውን ቅጣት ብናሞግስም በአንጻሩ የውሳኔው አካሄድ ላይ ግን ጥናት አልተደረገበትም ብለን እናምናለን፡፡ ስለዚህ በክለባችን ተቀባይነት የለውም፤›› በማለት የክለቡ ፕሬዚዳንት መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ በጋዜጣዊ መግለጫው ገልጸዋል፡፡

  እንደ መቶ አለቃው ገለጻ፣ እግር ኳስ የራሱ የሆነ ሥርዓትና ደንብ ያለው በመሆኑ ዳኞች ለእግር ኳስ ማደግ ትልቅ ሚና አላቸው፡፡

  በዚህም ምክንያት በደደቢትና ኢትዮጵያ ቡና መካከል የተደረገው ጨዋታ በተመለከተ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የወሰነው ውሳኔ ረዳት ዳኛዎችንም ማካተት ነበረበት፡፡

  ፕሬዚዳንቱ ተጨዋቾች ሜዳ ውስጥ ሰዓት ለመፍጀት አውቀው በመተኛት ጥፋት ቢሠሩም ዳኛው እርምጃ ባለመውሰዱ ምክንያት ሦስት ነጥብ ለማጣት እንደተገደዱ ተናግረዋል፡፡ ፌዴሬሽኑ በተጫዋቾች ላይም እርምጃ መወሰድ እንደነበረበት ጭምር አክለዋል፡፡

  በዓመቱ መጀመሪያ ላይ ከ500 ሺሕ ብር እስከ 800 ሺሕ ብር ገቢ ከተለያዩ የገቢ ምንጭ እንደሚያገኙ የተገለጸ ሲሆን ቲሸርት፣ የተለያዩ ፕሮግራሞችን በማዘጋጀትና በስፖንሰር ገቢን ለማግኘት የክለቡ ውጤት ወሳኝ መሆኑ በዳኝነት ምክንያት የሚጠፋው 3 ነጥብ ክለቡን ወደ ኪሳራ እንደሚከተውም ተገልጿል፡፡

  የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣትና ክለቡ በተደጋጋሚ በዳኞች የአግባብ ውሳኔ ከፖሊስና ከተመልካች ጋር ተደጋጋሚ ግጭት እንዲፈጠር መነሻ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡     

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  በችግር የተተበተበው የሲሚንቶ አቅርቦት

  ሲሚንቶን እንደ ግብዓት ተጠቅሞ ቤት ማደስ፣ መገንባት፣ የመቃብር ሐውልት...

  ‹‹የናይል ዓባይ መንፈስ›› በሜልቦርን

  አውስትራሊያ ስሟ ሲነሳ ቀድሞ የሚመጣው በተለይ በቀደመው ዘመን የባህር...

  ‹‹ልብሴን ለእህቴ››

  ለሰው ልጅ መኖር መሠረታዊ ፍላጎት ተብለው ከተዘረዘሩት ውስጥ ልብስ...

  የአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች የምርመራ ውጤት እስከምን?

  በፍቅር አበበ የትምህርት ጥራትን፣ ውጤታማነትንና ሥነ ምግባርን ማረጋገጥ ዓላማ አድርጎ...