Friday, December 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትፌዴሬሽኑ ለአምስት የአፍሪካ አገሮች የወዳጅነት ጨዋታ ጥሪ አቀረበ

ፌዴሬሽኑ ለአምስት የአፍሪካ አገሮች የወዳጅነት ጨዋታ ጥሪ አቀረበ

ቀን:

– በኬንያውያን ኤጀንቶች የተገኘውን የኒጀር የወዳጅነት ጨዋታ ውድቅ አድርጓል

ኢትዮጵያን ጨምሮ በአፍሪካ አገሮች የውስጥ ሊግ የሚጫወቱ ተጫዋቾች ብቻ የሚሳተፉበት አራተኛው የአፍሪካ አገሮች ዋንጫ ጥር 7 ቀን 2008 ዓ.ም. በሩዋንዳ ኪጋሊ ይጀመራል፡፡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ብሔራዊ ቡድኑ ወቅታዊ አቋሙን ይፈትሽበት ዘንድ ለአምስት የምዕራብና ሰሜን አፍሪካ አገሮች የወዳጅነት ጨዋታ ጥሪ አቅርቧል፡፡ በኬንያውያን ኤጄንቶች ተመቻችቶ ኬንያ ናይሮቢ ላይ ሊደረግ የታቀደው የኢትዮጵያና የኒጀር ብሔራዊ ቡድኖች የወዳጅነት ጨዋታ በፌዴሬሽኑ ውድቅ መደረጉም ታውቋል፡፡

አሥራ ስድስት የአፍሪካ አገሮች በአራት ምድብ ተከፋፍለው ከጥር 7 እስከ 29 ቀን 2008 ዓ.ም. ድረስ በሩዋንዳ የሚያከናውኑት የአፍሪካ አገሮች ዋንጫ (ቻን)፣ ሁሉም ተሳታፊ አገሮች ከዋናው ውድድር አስቀድሞ የተለያዩ የአቋም መፈተሽያ ውድድሮችን በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ ዘንድሮ ለሁለተኛ ጊዜ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በኬንያውያን ኤጀንቶች አማካይነት የተመቻቸለትን የወዳጅነት ጨዋታ ወደ ኬንያ ናይሮቢ አምርቶ ከኒጀር አቻው ጋር ሊያደርገው የነበረው ጨዋታ በፌዴሬሽኑ ውድቅ መደረጉ የሳምንቱ መነጋገሪያ ሆኗል፡፡ ጉዳዩን አስመልክቶ የተለያዩ ማኅበራዊና መሰል ሚዲያዎች ፌዴሬሽኑ እንደነዚህ ዓይነት ዕድሎችን መጠቀም ሲገባው ውድቅ ማድረግ ‹‹ለምን?›› በማለት የፌዴሬሽኑን ውሳኔ ማብጠልጠል ጀምረዋል፡፡

ይህንኑ አስመልክቶ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ ጁነዲን ባሻ፣ ‹‹በኬንያውያን ኤጀንቶች አማካይነት የሁለቱ አገሮች ብሔራዊ ቡድኖች ኬንያ ናይሮቢ ላይ የወዳጅነት ጨዋታ እንዲያደርጉ ጥያቄ ለፌዴሬሽኑ ቀርቧል፡፡ ነገር ግን ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ በሌለው አቅም ይህንን ጨዋታ ለማድረግ ጥያቄውን አልተቀበለም፡፡ ምክንያቱም የኒጀር ብሔራዊ ቡድን ከኢትዮጵያ አቻው ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ለማድረግ ፍላጎት ካለው ከናይሮቢ ይልቅ አዲስ አበባን በመረጠ ነበር፡፡ ይህ ደግሞ በዋናነት ኬንያውያኑ ኤጀንቶች ከኢትዮጵያ ፌዴሬሽን ኮሚሽን ለማግኘት ሲሉ ያደረጉት ነው፡፡ ለዚህም ነው ኬንያ ላይ የተዘጋጀውን የወዳጅነት ጨዋታ ላለመቀበል ድምዳሜ ላይ የደረስነው፡፡ ሆኖም የኒጀር ፌዴሬሽን ከኢትዮጵያ ጋር ለመጫወት ፍላጎቱ ካለው ኤጀንቶች ሳይገቡበት ፌዴሬሽኑ ግንኙነት በመፍጠር ጨዋታውን ለማከናወን ጥረት እያደረግን ነው፤›› ብለዋል፡፡  

አቶ ጁነዲን አስተያየታቸውን ሲቀጥሉ ብሔራዊ ቡድናችን ወቅታዊ አቋሙን ይፈትሽብት ዘንድ ኒጀርን ጨምሮ ለሌሎች አምስት የምዕራብና የሰሜን አፍሪካ አገሮች ጥሪ ማድረጋቸውንና ይህን አስተያየት እስከሰጡበት ድረስ ግን ፍላጎት ያሳዩ አገሮች ባለመኖራቸው ምክንያት የአገሮቹን ስምና ማንነት መግለጽ እንደማይፈልጉ ጭምር አስረድተዋል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...