Sunday, June 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊእስረኞችን በኃይል ለማስፈታት ተንቀሳቅሰዋል የተባሉ ተከሳሾች ጥፋተኛ ተባሉ

እስረኞችን በኃይል ለማስፈታት ተንቀሳቅሰዋል የተባሉ ተከሳሾች ጥፋተኛ ተባሉ

ቀን:

በአዲስ አበባና በወልቂጤ ከተሞች በህቡዕ በመደራጀት፣ በተከሰሱበት የሽብር ወንጀል ድርጊት ከሰባት እስከ 22 ዓመታት በሚደርስ ጽኑ እስራት የተወሰነባቸውን ‹‹የሙስሊሙ ማኅበረሰብ መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ›› በሚባል መጠሪያ የሚታወቁትን ፍርደኞች፣ በኃይል ለማስለቀቅ ሲንቀሳቀሱ ተገኝተዋል ተብለው የተከሰሱ 16 ግለሰቦች ታኅሳስ 19 ቀን 2008 ዓ.ም. ጥፋተኛ ተባሉ፡፡

በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 14ኛ ወንጀል ችሎት ጥፋተኛ የተባሉት ተከሳሾች በእነ ኤልያስ ከድር የክስ መዝገብ የሚጠሩ ናቸው፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ በህቡዕ ተደራጅተው በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ከሚኖሩ አጋሮቻቸው ጋር በመሆን በህቡዕ እየተገናኙ፣ ጉዳያቸው በሕግ ተይዞ በፍርድ ቤት በመታየት ላይ የነበሩትን እነ አቡበከር አህመድን (18 ሰዎች) በኃይል ለማስለቀቅ፣ የተለያዩ ድርጊቶችን መፈጸማቸውን ከሳሽ ዓቃቤ ሕግ በክሱ አካቷል፡፡

የተለያዩ አባላትን በመመልመልና ‹‹ድምፃችን ይሰማ፣ የሙስሊሙ ማኅበረሰብ መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴን በኃይል እናስፈታለን›› የሚል ጽሑፍ የያዙ በራሪ ወረቀቶችን በማዘጋጀት፣ በየመስጊዱ መበተናቸውም በክሱ ተገልጿል፡፡

በተለይ ሙስሊሙ ማኅበረሰብ ተሰባስቦ በሚያከብራቸው በዓላት ላይ አመፅና የቅስቀሳ ጥሪ ወረቀቶችን መበተናቸውንና በየክልሉ በህቡዕ ከተደራጁ ቡድኖች ጋር ግንኙነት ፈጥረው ሲንቀሳቀሱ እንደነበርም በክሱ ተመልክቷል፡፡

‹‹የሙስሊሙ ማኅበረሰብ መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ ቢታሰርም እኛ ተክተን እንሠራለን፤›› በማለት የተለያዩ ቅስቀሳዎችን ማድረጋቸውን ዓቃቤ ሕግ በክሱ ጠቅሶ፣ እንደ ክሱ ያስረዱልኛል ያላቸውን ከ50 በላይ ምስክሮች አቅርቦ አሰምቷል፡፡

ተከሳሾቹም እንዲከላከሉ በተሰጠው ውሳኔ መሠረት መከላከያ ምስክሮቻቸውን አሰምተዋል፡፡ የግራ ቀኙን ክርክር የሰማውና የቀረበለትን የሰነድ ማስረጃ የመረመረው ፍርድ ቤቱ ዓቃቤ ሕግ እንደ ክሱ ማስረዳቱን ገልጾ፣ ተከሳሾቹን ጥፋተኛ ብሏቸዋል፡፡ የቅጣት ውሳኔ ለመስጠትም ለጥር 2 ቀን 2008 ዓ.ም. ቀጥሯቸዋል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አወዛጋቢው የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ጉዳይ

በኢትዮጵያ የሕገ መንግሥት ማሻሻል ጉዳይ ከፍተኛ የፖለቲካ ውዝግብ የሚቀሰቀስበት...

 መፍትሔ  ያላዘለው  የጎዳና  መደብሮችን  ማፍረስ

በአበበ ፍቅር ያለፉት ስድስት ዓመታት በርካቶች በግጭቶችና በመፈናቀሎች በከፍተኛ ሁኔታ...

የተናደው ከቀደምቱ አንዱ የነበረው የአዲስ አበባ ታሪካዊ ሕንፃ

ዳግማዊ አፄ ምኒልክ በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ መናገሻ ከተማቸውን...

የአከርካሪ አጥንት ሕክምናን ከፍ ያደረገው ‘ካይሮፕራክቲክ’

በአፍሪካ ከጀርባ ሕመም ጋር በተያያዘ በርካታ ሰዎች ለከፍተኛ የአካል...