6 ፍሬ ተልጦ በአራት መአዘን የተከተፈ ድንች
1 ራስ የተከተፈ ሽንኩርት
4 ፍሬ ነጭ ሽንኩርት
1 የሾርባ ማንኪያ የደቀቀ ባሮ
1 የሾርባ ማንኪያ የደቀቀ ሲለሪ
1 የሾርባ ማንኪያ የአትክልት ዘይት
½ የሻይ ማንኪያ ቁንዶ በርበሬ
½ የሻይ ማንኪያ ጨው
1 የቡና ሲኒ ክሬም
4 ዳቦ
ግማሽ ሌትር ውሃ
አዘገጃጀት
- ባዘጋጀነው ድስት ውስጥ ዘይት በመጨመር ዘይቱ ከጋለ በኋላ ከተከተፈው ድንች እስከ ደቀቀው ሲለሪ ድረስ ለአምስት ደቂቃ ማቁላላት፡፡ በመቀጠልም ግማሽ ሊትር ውሃ በመጨመር ለ25 ደቂቃ ማፍላት
- ለአምስት ደቂቃ ከቀዘቀዘ በኋላ በጁስ መፍጫ እስኪልም ድረስ መፍጨት
- ጨው ቁንዶ በርበሬ እና ከሙን በመጨመር በድጋሚ በድስት ውስጥ ለአምስት ደቂቃ ማንተክተክ
- በመጨረሻ ባዘጋጀነው መመገቢያ ሳህን ላይ በመጨመር በላዩ ላይ የደቀቀ ፐርሲል ማድረግና ከዳቦ ጋር መመገብ
- ሱ ሼፍ ጌታዋ በሪሁን