Friday, September 22, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የመንግሥት የልማት ድርጅቶች በዘጠኝ ወራት ከ26 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰባቸው

ተዛማጅ ፅሁፎች

ለመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር ቀጥታ ተጠሪ የሆኑ 17 የልማት በዘጠኝ ወራት 26.7 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰባቸው ተገለጸ፡፡

ሰኞ ሚያዝያ 29 ቀን 2010 ዓ.ም. ሁሉም ተጠሪ ድርጅቶችና ኮርፖሬሽኖች የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸምና ግምገማ በግዮን ሆቴል ተደርጓል፡፡

የግምገማውን መድረክ የመሩት በቅርቡ በተካሄደው የከፍተኛ አመራሮች ምደባ፣ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት ተሾመ ቶጋ (አምባሳደር) ናቸው፡፡

የልማት ድርጅቶቹ በኦፕሬሽን ዕቅድ አፈጻጸም ረገድ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 38.3 ቢሊዮን ብርምርትናአገልግሎት ሽያጭ ለማከናወን አቅደው፣ 26.7 ቢሊዮን ብር ወይም የዕቅዳቸውን 70 በመቶ ማከናወን ችለዋል ተብሏል፡፡

ከምርትናአገልግሎት ሽያጭ 2.5 ቢሊዮን ብር ለማትረፍ አቅደው ሁለት ቢሊዮን ብር ወይም የዕቅዳቸውን 75 በመቶ ማከናወን እንደቻሉ በግምገማው ወቅት ተገልጿል፡፡

ከልማት ኮርፖሬሽኖችና ድርጅቶች መካከል የተወሰኑት ምርትና አገልግሎቶቻቸውን ለውጭ ገበያ ጭምር የሚያቀርቡ አሉ፡፡ እነዚህ የልማት ድርጅቶች ባለፉት ዘጠኝ ወራት 19 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ገቢ ለማግኘት አቅደው፣ 15 ሚሊዮን ዶላር ወይም የዕቅዳቸውን 78 በመቶ ማከናወናቸው በግምገማው ወቅት ተገልጿል፡፡

ከምርትናአገልግሎት ሽያጭ ገቢ ከዕቅዳቸው 95 በመቶ በላይ አፈጻጸም ያስመዘገቡት የሕንፃ ዕቃዎች አቅራቢ ድርጅት፣ ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካና የኢትዮጵያ ቱሪስት ንግድ ሥራ ድርጅት ናቸው፡፡ ከትርፍ ገቢ አንፃር ደግሞ የኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን፣ ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ፣ የሕንፃ ዕቃዎች አቅራቢ ድርጅትና ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ከዕቅዳቸው 95 በመቶ በላይ ማከናወናቸው ተጠቁሟል፡፡ 

ከላይ ከተጠቀሰው አጠቃላይ ከልማት ኮርፖሬሽኖችና ድርጅቶች የምርትናአገልግሎት ሽያጭ ገቢ 26.7 ቢሊዮን ብር ውስጥ 13.5 በመቶ አስተዋፅኦ በማድረግ ከፍተኛውን ድርሻ የያዘው፣ የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ነው ተብሏል፡፡ የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽንና የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን እንደ ቅደም ተከተላቸው 5.1 በመቶና 2.8 በመቶ  ከአጠቃላዩ ገቢ ድርሻ እንደያዙ በግምገማው ወቅት ተገልጿል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች