Monday, March 4, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊማይንድሴት የተሰኘ ድርጅት ከሰባት ሺሕ በላይ ሰዎች የሚሳተፉበት ፕሮግራም አዘጋጀ

ማይንድሴት የተሰኘ ድርጅት ከሰባት ሺሕ በላይ ሰዎች የሚሳተፉበት ፕሮግራም አዘጋጀ

ቀን:

በአዕምሮ ጤና አማካሪውና ሐኪሙ ምሕረት ደበበ (ዶ/ር) የተቋቋመው ማይንድሴት ኮንሰልት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ፣ በኢትዮጵያ የመጀመርያው የሆነ የማነቃቂያ መርሐ ግብር በሚሊኒየም አዳራሽ አዘጋጀ፡፡ ከሰባት ሺሕ በላይ የሚሳተፉበት ዝግጅቱ ግንቦት 11 ቀን 2010 ዓ.ም. እንደሚካሄድ ታውቋል፡፡

‹‹እኔ ነኝ አዲሲቷ ኢትዮጵያ›› በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው ዝግጅት ከ7,000 እስከ 8,000 ተሳታፊዎች እንደሚኖሩት የሚጠበቅ ሲሆን፣ ከዚህ ቀደም ድርጅቱ ያዘጋጃቸው ከነበሩት ዝግጅቶች በተለየ ይኼኛው በነፃ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡

በማይንድሴት ኮንሰልትና በኢቴል ኢቨንት ኦርጋናይዘርስ ትብብር የሚዘጋጀው ይህ ፕሮግራም ሁለት ዓይነት የምዝገባ ሒደቶች ይኖሩታል፡፡ አንደኛው ተመዝጋቢዎች በኢንተርኔት www.registrationmindsetconsult.com ድረ ገጽን በመጎብኘት የሚመዘገቡበት፣ ሁለተኛው ደግሞ በተንቀሳቃሽ ስልካቸው ወደ 8845 ስማቸውን በመጻፍ በሚልኩት አጭር የጽሑፍ መልዕክት ይሆናል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ምዝገባውን የፈጸሙ ተሳታፊዎች በሚሊኒየም አዳራሽ ከሰባት ሰዓት እስከ ዘጠኝ ሰዓት መገኘት ሲኖርባቸው፣ ከዘጠኝ ሰዓት በኋላ የሚመጡ ዝግጅቱ ስለሚጀመር መግባት እንደማይችሉም ተገልጿል፡፡

‹‹ዝግጅቱ ዘጠኝ ሰዓት ላይ ስለሚጀመር መግባት አይቻልም፣›› ሲሉ የድርጅቱ የሰብዓዊ ልህቀትና የአስተሳሰብ ለውጥ ፕሮግራም አስተባባሪ ወ/ሮ ሕይወት ዓለማየሁ ተናግረዋል፡፡

ይህ በዓይነቱ ልዩ የሆነው ዝግጅት ‹‹እኔ ነኝ አዲሲቷ ኢትዮጵያ›› በሚል መሪ ቃል  ሲሆን፣ ከዘጠኝ ሰዓት እስከ 12 ሰዓት የሚቆይ እንደሆነም  ምሕረት (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

በዚህም መሪ ቃል፣ አዲስ አገር አዲስ ራዕይ፣ አዲስ አገር አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አገር አዲስ አስተሳሰብ በሚሉ ርዕሶች ዙሪያ እሳቸውን ጨምሮ አራት ወይም አምስት ተናጋሪዎች እንደሚኖሩ ተገልጿል፡፡

እስካሁን እንደሚገኙ የተረጋገጠ ተናጋሪዎች፣ ‹የማማ በሰማይ› ደራሲ ሕይወት ተፈራና የታሪክ ተመራማሪው ኢብራሂም ሙሉሸዋ ይገኙበታል ሲሉ፣ ዶ/ር ምሕረት አስታውቀዋል፡፡ አንድ ስማቸው ያልተገለጸ ተናጋሪም እንደሚኖሩ ተጠቁሟል፡፡

ካሁን ቀደሞቹ የማይንድሴት ዝግጅቶች በተለየ ይህኛው ለምን በነፃ እንደሆነ የተጠየቁት ዶ/ር ምሕረት ድርጅታቸው ምንም እንኳን ለትርፍ የተቋቋመ ቢሆንም፣ ሁልጊዜ ትርፍ እያሰቡ መሥራት ብቻ በቂ እንዳልሆነ፣ ድርጅታቸው አዲስ እንደ መሆኑ መጠን አሁን መነሻ መዋዕለ ንዋይ የሚያፈስበት ጊዜ ላይ እደሆነና በቆይታ ትርፋማ ሊደርጋቸው የሚችል ሥራ እየሠሩ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

‹‹እያስከፈልን ስናካሂዳቸው የነበሩ ሥልጠናዎች እንኳን ይህን ያክል ትርፋማ አልነበሩም፡፡ ከ70 በመቶ በላይ የሚሆነውን ገቢያችንን የምናውለው ለሆቴል ኪራይ ክፍያ ነው፤›› ብለዋል፡፡

ይህኛው ዝግጅት በነፃ እዲሆን ያስቻለው አንዱ ምክንያት የሚሊኒየም አዳራሽን በነፃ ለመጠቀም ስለተፈቀደላቸው መሆኑንም አክለዋል፡፡

 የድርጅቱ አስተሳሰብ ልህቀትና የማኅበራዊ ለውጥ አማካሪ የሆኑት ሰላም አክሊሉ (ዶ/ር)፣ እኔ ነኝ አዲሲቷ ኢትዮጵያ የሚል አስተሳሰብን ለመፍጠር ያለመ ዝግጅት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ማይንድሴት ከሦስት ዓመታት በፊት የተቋቋመ አማካሪ ድርጅት ሲሆን፣ በአዕምሮ ጤና ላይ የማማከርና የሕክምና አገልግሎቶችን ይሰጣል፡፡

ማይንድሴት ላለፉት አራት ወራት ሲያደርጋቸው የነበሩ ተከታታይ የክፍያ ሥልጠናዎችን ማጠናቀቁንና ሁለተኛውን ዙር በብሔራዊ ቴአትር አዳራሽ ለመጀመር ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ዶ/ር ምሕረት ተናግረዋል፡፡

‹‹ሐሳብን እንደ ሸቀጥ ለመሸጥ ቀላል አይደለም፡፡ ሸቀጥ ለመሸጥ ቀላል ነው፤›› ሲሉም ዶ/ር ምሕረት ሥራው ተቀባይነት እንዲያገኝ ጊዜ እንደሚወስድ አስረድተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቁጥር ሲጨምር የሚኒባስ ታክሲዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ሊታሰብበት ይገባል

በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ከፍተኛ የሚባለውን ድርሻ...

ሃምሳ ዓመታት ያስቆጠረው አብዮትና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውጣ ውረድ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች የዴሞክራሲ ለውጥ ጥያቄ የሚነሳው ከፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የተፈጸመው ሕገወጥ ተግባር ምንድነው?

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ፣...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ላይ ምርመራ እንዲደረግ ውሳኔ ተላለፈ

ፕሬዚዳንቷና ዋና ጸሐፊው ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሏል ከአዲስ አበባ ንግድና...