Saturday, September 24, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናየማዳበሪያ ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች በአስቸኳይ ወደ ሥራ እንዲገቡ ማሳሰቢያ ተሰጠ

  የማዳበሪያ ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች በአስቸኳይ ወደ ሥራ እንዲገቡ ማሳሰቢያ ተሰጠ

  ቀን:

  የማዳበሪያ ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች ያሉባቸው ዘርፈ ብዙ ችግሮች ተቀርፈው በአስቸኳይ ወደ ሥራ መግባት እንዳለባቸው፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አሳሰበ፡፡

  ቋሚ ኮሚቴው በግብርና ግብዓት አቅርቦትና ተግዳሮቶች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሂዷል፡፡

  የግብርና እናእንስሳት ሀብት ሚኒስቴር የምጥን ማዳበሪያ ፋብሪካዎችን ችግር ለመፍታት እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ አስመልክቶ፣ ለቋሚ ኮሚቴው ዝርዝር ሪፖርት አቅርቧል፡፡

  በቀረበው ሪፖርትም በማዳበሪያ ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎችና በግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ተከማችቶ የሚገኘው ፈርቲኮት ኬሚካል ጥናት ተደርጎበት ጥቅም ላይ እንዲውል፣ አገልግሎት ላይ የማይውለውን የፖታሽ ማዳበሪያ ለማስወገድ እንደታሰበም ተገልጿል፡፡   

  ነገር ግን ቋሚ ኮሚቴው የሚኒስቴሩን ሪፖርት ከችግሩ ግዝፈትና ካለው አሳሳቢነት አንፃር ‹‹ችግር ፈቺ አይደለም›› ሲል አጣጥሎታል፡፡

  እንዲሁም በበጀት ዓመቱ ሁሉም የማዳበሪያ ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች ሥራ ለቆሙበት ጊዜ ለመጋዘን ኪራይ፣ ለባንክ ወለድ፣ ለሠራተኛ ደመወዝ ክፍያና ለሌሎች አላስፈላጊ ወጪዎች በመጋለጣቸው ከፍተኛ ኪሳራ እየደረሰባቸው እንደሚገኙ የቋሚ ኮሚቴው አባላት ገልጸው፣ ችግሮችን በአስቸኳይ ለመቅረፍ ርብርብ ሊደረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

  በሌላ በኩል የግብርናውን ዘርፍ ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር በሚስተዋሉ ችግሮች ላይ በሰፊው መወያየት እንዳለባቸው፣ አላስፈላጊ ወጪዎች ሊቆሙ እንደሚገባና ለተፈጠረው ችግር ተጠያቂ የሆኑ አካላት በሕግ ተጠያቂ መሆን እንዳለባቸው የቋሚ ኮሚቴው አባላት አሳስበዋል፡፡

  የግብርና እና እንስሳት ሀብት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ካባ ኡርጌሳ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ ለችግሮቹ ዩኒየኖች ጠያቂ ብቻ ሳይሆኑ የመፍትሔ አካል ሆነው እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ ገልጸው፣ በቀጣይ ጥቅም የሚሰጠው ማዳበሪያ ተለይቶ ለአርሶ አደሩ ለማሠራጨት እንደታሰበ  አስረድተዋል፡፡

  የግብርና እና እንስሳት ሀብት ሚኒስትር ዴኤታ ኢያሱ አብርሃ (ዶ/ር)፣ የሚስተዋሉ ውስብስብ ችግሮች በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲቀረፉ የኦዲት ክፍሉ ሥራውን በተገቢው መንገድ እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጸው፣ በቀጣይ በሕግ ተጠያቂ የሚሆኑ አካላት እንደሚኖሩም ጠቁመዋል፡፡

  ተፅዕኖ ማድረሱና አላስፈላጊ ንብረቶችን በማስወገዱ ረገድ ክፍተቶች መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡

  የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ በየደረጃው ያሉ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት የተጣለባቸውን ተልዕኮ በአግባቡ ለመወጣት ከፍተኛ ርብርብ ማድረግ እንዳለባቸው፣ የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ / አልማዝ አሳስበዋል፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ወ/ሮ መሰንበት ሸንቁጤ የአዲስ አበባን ንግድና ዘርፍ ምክር ቤትን በፕሬዚደንትነት ለመምራት በተደረገው ምርጫ አሸነፉ

  የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤትን በፕሬዚደንትነት ለመምራት፣...

  ለቻይናው ፖሊጂሲኤል ኩባንያ የተሰጠው ውል ተቋረጠ

  የማዕድንና ሚኒስቴር በሶማሌ ክልል የተገኘውን የተፈጥሮ ጋዝ አልምቶ ኤክስፖርት...

  የሕግ ክልከላዎችና የሚያስነሱት ቅሬታ

  በኢትዮጵያ የአገርና የዜጎችን ደኅንነት ለመጠበቅ ተብለው የሚወጡ አንዳንድ ሕጎች፣...