Wednesday, February 21, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናጠቅላይ ሚኒስትሩ ሹም ሽር በማድረግ ለ43 አመራሮች ሹመት ሰጡ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሹም ሽር በማድረግ ለ43 አመራሮች ሹመት ሰጡ

ቀን:

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በ23 በፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶች የሥልጣን ሹም ሹር በማድረግ አዳዲስ ሹመቶች ሰጡ፡፡

ከተሰጡት ሹመቶች መካከል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ጌታቸው ረዳን በማንሳት በኡጋንዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩትን ደግፌ ቡላ (አምባሳደር) በሚኒስትር ማዕረግ የፌዴራል የፍትሕና የሕግ ምርምርና ሥልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አድርገው ሾመዋቸዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ከኢሕአዴግ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ኃላፊነት ጋር ደርበው ይዘውት የነበረውን የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከልን ለአቶ ፈቃዱ ተሰማ ሰጥተዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የኦሮሚያ ክልል ካቢኔ አባል የሆኑት አቶ ፈቃዱ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በፌዴራልና በኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ የሥልጣን ዕርከኖች ላይ ሲሠሩ የቆዩ ሲሆን፣ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ፈቃዱን ወደፊት በማምጣት ማዕከሉን በሚኒስትር ማዕረግ እንዲያስተባብሩ ሾመዋቸዋል፡፡

ለዚህ ማዕከል ከአቶ ፈቃዱ በተጨማሪ አቶ ሳዳት ናሻ፣ አቶ ዛዲግ አብርሃና ተመሥገን ቡርቃ (ዶ/ር) ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ተሹመዋል፡፡

ሌላው ያልተለመደ የተባለው ለፈቃዱ በየነ (ፕሮፌሰር) እና ለእያሱ አብርሃ (ዶ/ር) የተሰጠው ‹‹ሹመት›› ነው፡፡ አቶ ፈቃዱ ቀደም ሲል የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ሚኒስትር፣ አቶ እያሱ ደግሞ የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስትር ሆነው ሲሠሩ ነበር፡፡

ሁለቱ ምሁራን ይመሯቸው የነበሩ መሥሪያ ቤቶች ታጥፈው አቶ ሽፈራው ሽጉጤ የግብርና እና የዓሳ ሀብት ሚኒስትር ሆነው በመሾማቸው፣ እነዚህ ሚኒስትሮች ይመሩዋቸው በነበሩ መሥሪያ ቤቶች ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው እንዲሠሩ ‹‹መሾማቸው›› ነው፡፡

ሌላኛው ሹመት በአብዛኛው ፕወዛ ሲሆን የንግድ ሚኒስትር ዴኤታ የነበሩት አቶ አያነ ዘውዴ፣ አሁን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ የነበሩት መብራቱ መለስ (ዶ/ር) የንግድ ሚኒስትር ዴኤታ፣ የማዕድን፣ ነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስትር ዴኤታ የነበሩት አቶ ቴዎድሮስ ገብረ እግዚአብሔር፣ አሁን ለገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ ምክትል ዳይሬክተር ሆነው ተሹመዋል፡፡

ቀደም ሲል የንግድ ሚኒስትር ዴኤታ፣ ከዚያም የኢትዮጵያ ባህርና ትራንስፖርት ባለሥልጣን አገልግሎት ድርጀት ዋና ዳይሬክተር፣ በኋላም የኦሮሚያ ገቢዎች ባለሥልጣን ኃላፊ የነበሩት አቶ አህመድ ቱሳ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር ዴኤታ ተደርገዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ የነበሩት አፈወርቅ ካሱ (ፕሮፌሰር) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ፣ የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስትር ዴኤታ የነበሩት አቶ ጌታቸው ኃይለ ማርያም የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ተሹመዋል፡፡ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር ዴኤታ የነበሩት ወ/ሮ ሌላዓለም ገብረ ዮሐንስ (አምባሳደር) የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ተደርገዋል፡፡

የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሚኒስትር ዴኤታዎች የነበሩት አቶ በየነ ገብረ መስቀልና አቶ ጌታቸው መንግሥቴ ለረዥም ዓመት ሲያገለግሉ ቢቆዩም፣ በአዲሱ ሹመት በምትካቸው ወ/ሮ ስመኝ ውቤና ወ/ሮ ምሥራቅ ማሞ ተሹመዋል፡፡

ወ/ሮ ስመኝ ቀደም ሲል የቀድሞው ፍትሕ ሚኒስትር ዴኤታ፣ እንዲሁም የአዲስ አበባ ሊዝና ኅብረተሰብ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ነበሩ፡፡ ወ/ሮ ምሥራቅም የስትራቴጂካዊው የመጠባበቂያ ምግብ ክምችት ኤጀንሲ ኃላፊ ነበሩ፡፡

በአጠቃላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ የሰጡት ሹመት ትምህርትንና የፖለቲካ አመራር ብቃት ከግምት በማስገባት ነው ሲል፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡

የተሿሚዎቹ ዝርዝር

 1. አምባሳደር ደግፌ ቡላ – በሚኒስትር ማዕረግ የፌዴራል የፍትሕና የሕግ ምርምርና ሥልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር
 2. አቶ ፍቃዱ ተሰማ – በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል አስተባባሪ
 3. አቶ ሳዳት ናሻ – በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል
 4. አቶ ዛዲግ አብርሃ – በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል
 5. ተመስገን ቡርቃ (ዶ/ር) – በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል
 6. ወ/ሮ ለሃርሳ አብዱላሂ – የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዴኤታ
 7. አቶ ብርሃኑ ፈይሳ – የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዴኤታ
 8. ፍቃዱ በየነ (ፕሮፌሰር) – የግብርና እና እንስሳት ሀብት ሚኒስትር ዴኤታ
 9. ኢያሱ አብርሃ (ዶ/ር) – የግብርና እና እንሰሳት ሀብት ሚኒስትር ዴኤታ
 10.  አቶ ሲሳይ ቶላ – የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ሚኒስትር ዴኤታ
 11.  መብራቱ ገብረማርያም (ዶ/ር)  – የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ሚኒስትር ዴኤታ
 12.  አቶ እሸቴ አስፋው – የትራንስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ
 13.  ወ/ሮ ሕይወት ሞሲሳ – የትራንስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ
 14.  ነጋሽ ዋቅሻው (ዶ/ር)  – የውኃ፣ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስትር ዴኤታ
 15.  አብርሃ አዱኛ (ዶ/ር) – የውኃ፣ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስትር ዴኤታ
 16.  አቶ ዮሐንስ ድንቃየሁ – የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ
 17.  አቶ አያና ዘውዴ – የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ
 18.  አቶ ቴዎድሮስ ገብረ እግዚአብሔር – በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር
 19.  አቶ ከፍያለው ተፈራ – የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስትር ዴኤታ
 20.  አቶ ካሳሁን ጎፌ – የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር ዴኤታ
 21.  አቶ ተመስገን ጥላሁን – የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር ዴኤታ
 22.  መብራህቱ መለስ (ዶ/ር) – የንግድ ሚኒስትር ዴኤታ
 23.  አቶ ሀብታሙ ሲሳይ – የንግድ ሚኒስትር ዴኤታ
 24.  ወ/ሮ ሌላዓለም ገብረ ዮሐንስ (አምባሳደር) – የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ
 25.  አቶ ጌታቸው ኃይለ ማርያም – የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ
 26.  አቶ አድማሱ አንጎ – የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ሚኒስትር ዴኤታ
 27.  አቶ ገለታ ሥዩም – የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ሚኒስትር ዴኤታ
 28.  አቶ አህመድ ቱሳ – የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር ዴኤታ
 29.  አቶ ምሥጋኑ አረጋ (አምባሳደር) – የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ
 30.  አቶ አሰፋ ኩምሳ – የማዕድን፣ ነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስትር ዴኤታ
 31.  ወ/ሮ ብዙነሽ መሠረት – የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ
 32.  ወ/ሮ ቡዜና አልከድር – የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ
 33.  አፈወርቅ ካሱ (ፕሮፌሰር) – የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ
 34.  ወ/ሮ ብርቱካን አያኖ (አምባሳደር) – የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ
 35.  ወ/ሮ አስቴር ዳዊት – የሴቶችና ሕፃናት ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ
 36.  ወ/ሮ ፍሬሕይወት አያሌው – የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ
 37.  ወ/ሮ ፈርሂያ መሐመድ – የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ
 38.  ወ/ሮ ምሥራቅ ማሞ – የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሚኒስትር ዴኤታ
 39.  ወ/ሮ ስመኝ ውቤ – የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሚኒስትር ዴኤታ
 40.  አቶ ጌታቸው ባልቻ – የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሚኒስትር ዴኤታ
 41.  ኮሎኔል ታዜር ገብረ እግዚአብሔር – የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስትር ዴኤታ
 42.  ወ/ሮ ኢፍራን ዓሊ – የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ
 43.  አቶ ወርቁ ጓንጉል – በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የጽሕፈት ቤት አገልግሎትና መልካም አስተዳደር ክትትል ሚኒስትር ዴኤታ በመሆን ከግንቦት 2 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ተሹመዋል፡፡
spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የካቲት አብዮት – ጥያቄዎችሽ ዛሬም እየወዘወዙን ነው!

በበቀለ ሹሜ አጭር መግቢያ የዚህ ጽሑፍ አቅራቢ ከ1960ዎች ወጣቶች ርዝራዦች አንዱ...

የሰሞኑ የ“መኖሪያ ቤቶች” የጨረታ ሽያጭ ምን ዓይነት ሕጋዊ መሠረት አለው?   

በዳዊት ዮሐንስ ሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተማ አየር ላይ ከሚንሸረሸሩ ዜናዎች...

ሁለቱ ወጎች፡ ከሰማየ ሰማያት አድርሶ መላሹ ቋንቋ! እስከ በዓሉ ቤርሙዳ

በተክለ ጻድቅ በላቸው ሰማየ ሰማያት አድርሶ መላሹ ቋንቋ! ከሁለት ሦስት ዓመት...

ለትግራይ ክልል ድርቅ ተፈናቃዮች አፋጣኝና ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እንዲደረግ ተጠየቀ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዩች ቋሚ...