Monday, October 2, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የኢትዮ ጂቡቲ ኮሪደር መንገድ በመበላሸቱ የተሽከርካሪዎች ምልልስ እየተስተጓጎለ ነው

ተዛማጅ ፅሁፎች

ከሌሎች ጎረቤት አገሮች አንፃር ሲታይ ለመሀል ኢትዮጵያ ቅርብ የሆነው የጂቡቲ ወደብ ቢሆንም፣ በተለይ ከወደቡ እስከ ጋላፊ ድረስ ያለው 200 ኪሎ ሜትር መንገድ በመበላሸቱ፣ የተሽከርካሪዎችን ምልልስ ከማስተጓጎሉም በላይ፣ ለአላስፈላጊ የመለዋወጫ ዕቃዎች ወጪ እያደረጋቸው መሆኑን ባለንብረቶች አስታወቁ፡፡

ከጂቡቲ አዲስ አበባ ድረስ ያለው ርቀት 907 ኪሎ ሜትር ነው፡፡ ከቅርበትና ከሌሎች ኢኮኖሚ ማኅበራያዊ ጉዳዮች በመነሳት የኢትዮጵያ መንግሥት 85 በመቶ የገቢና ወጪ ዕቃዎችን የሚያመላልሰው በጅቡቲ ወደብ በኩል ቢሆንም፣ በተለይ ከጅቡቲ ወደብ የድንበር ከተማ እስከሆነው ጋላፊ ድረስ ያለው 200 ኪሎ ሜትር መንገድ በመበላሸቱ፣ ምልልሱን እያስተጓጎለ መሆኑን የጭነት ማመላለሻ ባለንብረቶች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ትራንስፖርት ኅብረት ሊቀመንበር አቶ ብርሃን ዘሩ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ መንግሥት የትራንስፖርት ምልልሱን ከስድስት ቀናት ወደ ሦስት ወይም አራት ቀናት ለማሳጠር ቢያቅድም ይህ ሊሆን ግን አልቻለም፡፡

‹‹ምክንያቱም በተለይ በጅቡቲ ክልል ውስጥ እስከ ጋላፊ ድረስ ያለው መንገድ እጅግ በመበላሸቱ ምልልሱ ከመስተጓጎሉ ባሻገር፣ ተሽከርካሪዎች ዕቃ እየሰበሩ ለአላስፈላጊ ወጪ እየዳረጉ ነው፤›› በማለት የችግሩን ውስብስብነት አቶ ብርሃን ተናግረዋል፡፡

ይህ መንገድ ከተበላሻ ከሁለት ዓመት በላይ ቢሆንም፣ ያለምንም ጥገና የኢትዮጵያ ገቢና ወጪ ዕቃዎች እየተመላለሱበት ነው፡፡ ይህንን መንገድ የመጠገን ኃላፊነት የጅቡቲ  መንግሥት ቢሆንም፣ መጠገን ባለመቻሉ የሚመለከታቸው ተዋናዮች ለመንግሥት ቅሬታ እየቀረቡ መሆኑ ታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ሳምሶን ወንድሙ መንገዱ መበላሸቱን ለሪፖርተር አረጋግጠው፣ ነገር ግን ጉዳዩ የእሳቸውን መሥሪያ ቤት እንደማይመለከት ገልጸዋል፡፡

ለዚህ መንገድ መፍትሔ ለመስጠት የትራንስፖርት ሚኒስቴር ከሚመለከታቸው የጂቡቲ መንግሥት መሥሪያ ቤቶች ጋር እየተነጋገረ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች