Friday, September 22, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበድርቁ ምክንያት የሰብል ምርቶች ኤክስፖርት ታገደ

በድርቁ ምክንያት የሰብል ምርቶች ኤክስፖርት ታገደ

ቀን:

ኢትዮጵያ ውስጥ በተፈጠረው ድርቅ ምክንያት ተጎጂ ለሆኑ ከአሥር ሚሊዮን በላይ ወገኖች የምግብ አቅርቦት ሲባል፣ የሰብል ምርቶች ኤክስፖርት እንዲቆም የሚኒስትሮች ምክር ቤት መወሰኑን የንግድ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የንግድ ሚኒስትሩ አቶ ያዕቆብ ያላ ረቡዕ ታኅሳስ 20 ቀን 2008 ዓ.ም. የሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸማቸውንና አጠቃላይ የበጀት ዓመቱ ዕቅድን ባቀረቡበት ወቅት ነው ይህንን የገለጹት፡፡

እስካሁን ድረስ የታገዱ የምርት ዓይነቶች በቆሎና ማሽላ መሆናቸውን የገለጹት ሚኒስትሩ፣ ‹‹ቦሎቄን ኤክስፖርት እንዳይደረግ ባናግድም በትንሹ ብቻ እንዲወጣ እያደረግን የቀረውን ከላኪዎች እየወሰድን ለአደጋ መከላከል ኮሚቴ እያቀረብን ነው፤›› ብለዋል፡፡

ይህንን በማድረግም ኤክስፖርት ደረጃ ያለው የቦለቄ ምርት ለአገር ውስጥ አልሚ ምግብ አምራቾች እየቀረበ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡

በድርቁ ሳቢያ የግብርና ምርት ኤክስፖርት ገቢ ጉዳት እንደሚደርስበትም ከወዲሁ መገመቱን ገልጸዋል፡፡ የቡና ምርት በድርቁ ምክንያት ፍሬው የቀጨጨ ቢሆንም፣ ምርቱን ሙሉ በሙሉ በማውጣት በተገኘው ዋጋ የመሸጥ ዕቅድ መያዙን ተናግረዋል፡፡

በሩብ ዓመት ውስጥ ከግብርና ምርቶች 528 ሚሊዮን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ የተገኘው 439 ሚሊዮን ዶላር መሆኑን ሪፖርቱ ይጠቁማል፡፡

በአጠቃላይ በሩብ ዓመት ውስጥ ከኤክስፖርት ገቢ 869.6 ሚሊዮን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ የተገኘው 681.7 ሚሊዮን ዶላር መሆኑን፣ ይኼም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ከተገኘው 733.4 ሚሊዮን በእጅጉ እንደሚያንስ በቋሚ ኮሚቴውም በሚኒስቴሩም ተገምግሟል፡፡

ይህ ዝቅተኛ አፈጻጸም በአገሪቱ የውጭ ምንዛሪ ፍላጎት ላይ ተፅዕኖ እንዳያሳድር የታሰበውን መፍትሔ የተጠየቁት ሚኒስትሩ፣ የስኳር ምርትን በቀጣዮቹ ወራት ኤክስፖርት የማድረግና የበልግ ዝናብ በወቅቱ ከመጣ ከተጨማሪ የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ለማካካስ መታሰቡን ጠቁመዋል፡፡

በዚህ የተነሳ የዚህ ዓመት የኤክስፖርት ገቢ ዕቅድ ሊካካስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ሪፖርት ምን ይዟል?

ለአሜሪካ ድምፅ አማርኛ ዝግጅት የስልክ አስተያየት የሰጡ አንድ የደንበጫ...

መንግሥት በአማራ ክልል ለወደሙ የአበባ እርሻዎች ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት በቢዝነስ...

አምናና ዘንድሮ!

እነሆ መስከረም ጠብቶ በአዲስ መንፈስ ተሞልተን መንገድ ጀምረናል። ‹‹አዲስ...