Monday, April 15, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና እንባ ጠባቂ ተቋም በመልካም አስተዳደር ችግሮች ላይ መንግሥትን ሊያግዙ...

ሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና እንባ ጠባቂ ተቋም በመልካም አስተዳደር ችግሮች ላይ መንግሥትን ሊያግዙ ነው

ቀን:

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን አስመልክቶ ያሉ ችግሮችን በመለየትና የመፍትሔ አቅጣጫዎችን በማቅረብ መንግሥትን ሊያግዙ እንደሆነ ተነገረ፡፡

ይህ የተገለጸው ዓርብ ታኅሳስ 22 ቀን 2008 ዓ.ም. የሁለቱ ተቋማት የመልካም አስተዳደር ንቅናቄ ዕቅድ ላይ ከተለያዩ የባለድርሻ አካላት ጋር በሒልተን ሆቴል በተካሄደ የምክክር መድረክ ላይ ነው፡፡

በዕለቱ የመልካም አስተዳደር የንቅናቄ ዕቅድን ከማስፈጸም አንፃር የመልካም አስተዳደር ሁኔታዎች ግምገማ፣ የዕቅዱ መነሻዎች፣ የዕቅዱ ዓላማ ላይ፣ እንዲሁም የዕቅዱ ግቦችን በተመለከተ በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽነር ኮሚሽን ዶ/ር አዲሱ ገብረ እግዚአብሔርና በሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ዋና እንባ ጠባቂ ወይዘሮ ፎዝያ አሚን አማካይነት ገለጻ ተደርጓል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የምክክር መድረኩን ጠቀሜታና ዓላማ በተመለከተ፣ ‹‹ምንም እንኳን የዕቅዱ መነሻ ሐሳብ በተቋማቱ አማካይነት የቀረበ ቢሆንም፣ ይህ ዕቅድ የሕዝብን ፍላጎት ሊያረካ በሚችል ሁኔታ መታቀድ ስላለበት ግብዓት ለማሰባሰብ የተዘጋጀ ነው፤›› በማለት ዶ/ር አዲሱ ለሪፖርተር አስረድተዋል፡፡

የሁለቱን ተቋማት በጋራ መሥራትን አስመልክቶ የጋራ ጉዳዮችን በጋራ የመሥራት ባህል ሊዳብር ስለሚገባ እንደሆነ የገለጹት ዶ/ር አዲሱ፣ ተቋማቱ በየራሳቸው የሚሠሩት ሥራ አለ፡፡ በጋራ የሚሠሩት ሥራም እንዲሁ አለ ብለዋል፡፡ በተለይ ተመጋጋቢ የሆኑ ጉዳዮች ላይ በጋራ የመሥራት ባህልን ለማዳበርና በስህተት ወደ እንባ ጠባቂ ተቋም የሄደ ጉዳይ ካለ ወደ ኮሚሽኑ መላክ፣ ለኮሚሽኑ ያልሆነ ነገር ግን ጉዳዩ የአስተዳደር በደል ከሆነ ደግሞ ወደ እንባ ጠባቂ ተቋም የሚላክበትን አሠራር መዘርጋትና የመረጃ ፍሰቱን የተሟላ ማድረግ እንደሆነ፣ ዶ/ር አዲሱ አክለው አስረድተዋል፡፡

በ2007 በጀት ዓመት የውስጥ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመለየት ራሱን የቻለ ዕቅድ በማዘጋጀት ችግሮችን ለመቅረፍ ሲንቀሳቀስ መቆየቱን ያስታወሱት ወይዘሮ ፎዝያ ሲሆኑ፣ በአፈጻጸም ረገድም ያጋጠሙ ውስንነቶችን አቅርበዋል፡፡

በዚህም መሠረት ከታዩ ውስንነቶች መካከል የተቋሙ የምርመራ ሥራ ጥራት ዝቅተኛ መሆን፣ የውሳኔ መዘግየት፣ ፍትሐዊ ያልሆኑ ውሳኔዎችና መፍትሔዎች፣ አልፎ አልፎ የአስፈጻሚ አካላት ለተቋሙ ተባባሪ ያለመሆን፣ የመንግሥት ተቋማት መረጃን በፍጥነት ከመስጠት አንፃር መጓተትና መረጃን ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆን፣ የአዋጅ 590/2000 ማሟያ ደንቦች አለመውጣት፣ ጥራት ያለው የጥናት ውጤቶች ለመንግሥት አለማቅረብና የቁጥጥር ሥራዎች በሚፈለገው ጥራት ደረጃ ያለመሆን የሚሉት የተጠቀሱ ነጥቦች ነበሩ፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የንቅናቄውን ዕቅድ መነሻዎች የገለጹት ወይዘሮ ፎዚያ፣ ሕዝብ የሚያነሳቸው የመልካም አስተዳደር ጉድለቶች በአፋጣኝ የመፍታት አስፈላጊነት፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት በምቹ ሁኔታ ላይ መገኘት፣ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን በሕግ የተደነገጉ የዜጎች መብቶችና ጥቅሞች እንዲከበሩ ማድረግና የመልካም አስተዳደር ጉድለቶችን ለመፍታት የለውጥ መሣሪያዎችን ተግባራዊ የማድረግ አስፈላጊነት የሚሉት እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

በተካሄደው የምክክር መድረክ ላይ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔና ምክትል አፈ ጉባዔ ከአቶ አባዱላ ገመዳና ከወይዘሮ ሽታዬ ምናለ በተጨማሪ የሕዝብ ተወካዮች፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ የሙያ ማኅበራት ተጠሪዎችና የሲቪክ ማኅበረሰብ አባላት ተገኝተዋል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ያልተቃናው የልጆች የንባብ ክህሎት

አንብቦና አዳምጦ መረዳት፣ የተረዱትን ከሕይወት ጋር አዋህዶ የተቃና ሕይወት...

እንስተካከል!

ሰላም! ሰላም! ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንዲሁም የሰው ዘር በሙሉ፣...

የሙዚቃ ምልክቱ ሙሉቀን መለሰ ስንብት

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ በ1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ በኪነ ጥበባትም ሆነ...

‹‹ደስታ›› የተባለችው አማርኛ ተናጋሪ ሮቦት በሳይንስ ሙዚየም

‹‹እንደ ሮቦት ዋነኛው አገልግሎቴ ውስብስብ የሆኑ የቴክኖሎጂ ውጤቶችንና አሠራሮችን...