Tuesday, April 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊለብሔራዊ ባንክ ቁርጥራጭ ባሌስትራ በማቅረብ ከ95 ሚሊዮን ብር በላይ የወሰደው ተከሳሽ ይግባኙ...

ለብሔራዊ ባንክ ቁርጥራጭ ባሌስትራ በማቅረብ ከ95 ሚሊዮን ብር በላይ የወሰደው ተከሳሽ ይግባኙ ተቀባይነት አጣ

ቀን:

– የ25 ዓመት ጽኑ እስራትና 180 ሺሕ ብር ተፈርዶበታል

ከቀድሞ ማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስቴር ያገኘውን የወርቅ ጥራት ማረጋገጫ በመያዝ፣ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በውስጣቸው በቁርጥራጭ የባሌስትራ ብረቶች የተሞሉ 29 የታሸጉ ሳጥኖችን በማቅረብ ከ95 ሚሊዮን ብር በላይ መውሰዱ ተረጋግጦ ቅጣት የተወሰነበት ነጋዴ፣ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረበው የይግባኝ አቤቱታ ተቀባይነት አጣ፡፡

ከ1998 ዓ.ም. እስከ 1999 ዓ.ም. ድረስ የተለያዩ ስሞችን፣ የንግድ ሰርተፍኬቶችንና መታወቂያዎችን በመጠቀም የማጭበርበር ድርጊቱን ፈጽሟል ተብሎ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት የ25 ዓመታት ጽኑ እስራትና የ180 ሺሕ ብር የገንዘብ ቅጣት የጣለበት ነጋዴ፣ አቶ አስማረ አያሌው ደስታ (በብዛት የሚታወቅበት ስሙ ከፍያለው ኡመታ) ይባላል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በድምሩ ከ150 ሚሊዮን ብር በላይ መጭበርበሩ ይታወሳል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የአንድ ዲፓርትመንት ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ሰይፈ ደስታና የሥራ ባልደረቦቻቸው፣ በማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ዋና ጂኦሎጂስት አመንቴ አብርሃና የሥራ ባልደረቦቻቸውና በተለያዩ የንግድ መስኮች የተሰማሩ ነጋዴዎች በቁጥጥር ሥር ሲውሉ፣ አቶ አስማረ ከአገር መውጣቱ መገለጹ አይዘነጋም፡፡

የሁሉም ተከሳሾች የክስ ሒደት ሲጠናቀቅ በወቅቱ ያልተያዘውና በጋዜጣ ተጠርቶ ያልቀረበው አቶ አስማረ፣ በሌለበት 25 ዓመታት ጽኑ እስራትና 180 ሺሕ ብር ተቀጥቶ ፖሊስ ግለሰቡን ይዞ ቅጣቱን እንዲያስፈጽም ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር፡፡

በመሆኑም አቶ አስማረ ለዓመታት ይኖር ከነበረበት የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ፣ በኢንተርፖል አማካይነት ተይዞ ወደ ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. መስከረም 30 ቀን 2014 መጥቶ በእስር ላይ ይገኛል፡፡ አቶ አስማረ ወደ ኢትዮጵያ ተላልፎ ከተሰጠ በኋላ፣ ‹‹ቅጣት የተወሰነብኝ መከሰሴ ተገልጾ ፍርድ ቤት እንድቀርብ መጥሪያ ሳይላክልኝ፣ ጥፋቴን ሳላውቀውና ባልተከራከርኩበት ጉዳይ ነው፡፡ በመሆኑም ቅጣቱ ቀሪ ሆኖ የተከሰስኩበት ወንጀል ተነግሮኝ የመከራከር መብቴ እንዲጠበቅልኝ፤›› በማለት የሥር ፍርድ ቤትን የቅጣት ውሳኔ በመቃወም ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የይግባኝ አቤቱታ አቅርቦ ነበር፡፡

ፍርድ ቤቱ አቶ አስማረ ያቀረበውን የይግባኝ አቤቱታ ተመልክቶ በሥር ፍርድ ቤት ክስ ያቀረበው የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ዓቃቤ ሕግ ምላሽ እንዲሰጥበት አድርጓል፡፡

የኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ በሰጠው ምላሽ እንዳስረዳው፣ ፍርደኛው መከሰሱን ያውቃል፡፡ በወቅቱ ሊገኝ ባለመቻሉ በጋዜጣም ጥሪ ተደርጐለታል፡፡ በተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ መኖሩ ሲታወቅ፣ ግለሰቡ አደገኛ ስለሆነ በኢንተርፖል በኩል መጥሪያ ተሰጥቶት ተይዞ እንዲመጣ ተደርጓል፡፡ በመሆኑም ሕጉ በሚፈቅደው መሠረት የተጣለበት ቅጣት ተገቢ በመሆኑ ያቀረበው የይግባኝ አቤቱታ ውድቅ እንዲደረግና ቅጣቱ ተግባራዊ እንዲሆን መጠየቁን ፍርድ ቤቱ ገልጿል፡፡

ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የሁለቱን ወገኖች ክርክር ካዳመጠ በኋላ፣ ‹‹ይግባኝ ባዩ ላይ የተጣለበት ቅጣት ባለበት መቀጠሉ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም?›› የሚል ጭብጥ ይዞ መዝገቡን መመርመሩን አስታውቋል፡፡ አንድ ተከሳሽ ወደ ዳኝነት እንዲቀርብ ሲጠየቅ ከሸሸ ጉዳዩ በሌለበት የሚታይበት የሕግ አግባብ መኖሩን ፍርድ ቤቱ አስታውሶ፣ አቶ አስማረም መከሰሱን አውቆ ሊቀርብ ይገባ እንደነበር ገልጿል፡፡ ዓቃቤ ሕግ በአግባቡ መጥሪያና ክስ የማድረስ ግዴታ እንዳለበት የጠቆመው ፍርድ ቤቱ፣ በወቅቱ ተከሳሹ ሊገኝ አለመቻሉን ገልጾ በመከራከሩ፣ ክሱ እንደ አዲስ እንዲቀጥል ማድረጉ ተገቢ አለመሆኑን ገልጾ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ አቶ አስማረ በቅጣቱ ላይ ይግባኝ የማለት መብት እንዳለው ማለትም በወቅቱ የቅጣት ማቅለያ ሐሳብ ባለማቅረቡ፣ የቅጣት ማቅለያ ሐሳብ እንዲያቀርብ ለታኅሳስ 27 ቀን 2008 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

   

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰው መሆን ምንድን ነው? ቅርስና ማኅበራዊ ፍትሕ

በሱራፌል ወንድሙ (ዶ/ር) ዳራ ከጎራዎች፣ ከመፈራረጅ፣ ነገሮችን ከማቅለልና ከጊዜያዊ ማለባበስ ወጥተን...

ኢኮኖሚው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሳት ያሠጋል

በጌታቸው አስፋው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሱ የሚያሠጉኝ አንድ ሁለት ብዬ ልቆጥራቸው የምችላቸው...

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ትግል በሕግ አምላክ ይላል

በገነት ዓለሙ የአገራችንን ሰላም፣ የመላውን ዓለም ሰላም ጭምር የሚፈታተነውና አደጋ...

በሽግግር ፍትሕ እንዲታዩ የታሰቡ የወንጀል ጉዳዮች በልዩ ፍርድ ቤት ሳይሆን በልዩ ችሎት እንዲታዩ ተወሰነ

የኤርትራ ወታደሮች በሌሉበትም ቢሆን ይዳኛሉ ተብሏል በፅዮን ታደሰ የሽግግር ፍትሕ የባለሙያዎች...