Thursday, June 13, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ስፖርት​ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኑና የአቶ ዱቤ ጅሎ ውዝግብ

​ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኑና የአቶ ዱቤ ጅሎ ውዝግብ

ቀን:

– ‹‹የሥራ መልቀቂያ አስገብቻለሁ ሆኖም በጉዳዩ ከፌዴረሽኑ ጋር ተነጋግረንበት በሥራ ገበታዬ እገኛለሁ›› አቶ ዱቤ ጅሎ

– መልቀቂያውን የፌዴሬሽኑ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በዝርዝር ተወያይቶበት ተቀብሎታል›› አቶ ቢልልኝ መቆያ የፌዴሬሽኑ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በበርካታ ችግሮች ሲተችና ሲታማ ቆይቷል፡፡ በዙሪያው ለስፖርቱ እንቅፋት ተብለው የሚወሰዱ በርካታ የሥነ ምግባር ችገሮች ሲታዩበት፣ ለስፖርቱ ዝቅተኛ ውጤትና ተገቢነት ለሚጎላቸው ስፖርተኞች ምልመላና ማንነት ጭምር ቅሬታዎች ሲቀርቡበት ኖሯል፡፡ አሁንም እየቀረበበት ይገኛል፡፡

- Advertisement -

ይባስ ብሎም አትሌቲክሱ በአትሌቶች ስም፣ አትሌቶች ያልሆኑትን አትሌቶች ተብለው በክፍያ ወደ ውጭ የማሻገሪያ መሣሪያ ሆኖ መገኘቱ ሁሉ በሰፊውና በአደባባይ እየተወራበት ይገኛል፡፡ አገሪቱ በዓለም በአትሌቲክሱ መድረክ እየተወራበት ስሟ የናኘበት አትሌቲክስ በውጤት ቀውስ ውስጥ መሆኑ በሚነገርለት በአሁኑ ወቅት፣ በተለይ አትሌቶችና ስፖርቱን የሚመሩ ኃላፊዎች ለግል ጥቅማቸው መሯሯጣቸው ስፖርቱን ክፉኛ እየጎዳው ስለመሆኑም የሚናገሩ አሉ፡፡

ሰሞኑን ደግሞ የብሔራዊ ፌዴሬሽኑ የቴክኒክ ዘርፍ በዳይሬክተርነት ከ20 ዓመት በላይ አገልግሎት በመስጠት ላይ የቆዩት አቶ ዱቤ ጅሎ በሥራ ጫና ምክንያት ባለፈው ቅዳሜ ታኅሣሥ 23 ቀን 2008 ዓ.ም. ለብሔራዊ ፌዴሬሽኑ የሥራ መልቀቂያ ደብዳቤ አስገብተው ፌዴሬሽኑም የሥራ መልቀቂያቸውን አስመልክቶ በዝርዝር ተወያይቶ የተቀበለው መሆኑ ታውቋል፡፡ ሪፖርተር በስልክ ስለ ጉዳዩ ያነጋገራቸው አቶ ዱቤ ጅሎ በበኩላቸው፣ በሥራ ገበታቸው እንደሚገኙ ነው ያስረዱት፡፡ ይህም ፌዴሬሽኑን ‹‹በእንቅርት ላይ …›› እንዲሉ ወደ ሌላ ውዝግብ ውስጥ እያስገባው ስለመሆኑ ጭምር የሚናገሩ አሉ፡፡

በብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ከነበራቸው የኃላፊነት ቆይታ አንፃር በተለይም የሪዮ ኦሊምፒክ እየተቃረበ በሚገኝበት በዚህ ወቅት የሥራ መልቀቂያ ማስገባትዎ ለምን? ለሚለው የሪፖርተር ቀጣይ ጥያቄ አቶ ዱቤ፣ ‹‹የሥራ መልቀቂያውን ለማስገባት በዋናነት ያስገደደኝ በሥራ ጫና ምክንያት ነው፡፡ መልቀቂያውን ያስገባሁት ደግሞ ያለፈው ቅዳሜ ታኅሳስ 23 ቀን 2008 ዓ.ም. ነው፡፡ ሆኖም በመልቀቂያ ዝርዝር ጉዳይ ላይ ከፌዴሬሽኑ ጋር ተነጋግረንበት ከስምምነት ደርሰን በአሁኑ ወቅትም የምገኘው በሥራ ገበታዬ ላይ ነው፤›› ብለው ዝርዝሩን በሚመለከት ግን ከመናገር ተቆጥበዋል፡፡

የብሔራዊ ፌዴሬሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ቢልልኝ መቆያ በበኩላቸው፣ ‹‹አቶ ዱቤ የሥራ መልቀቂያ ማስገባታቸው እውነት ነው፡፡ ጥያቄውም ‹የድርጅት ተልዕኮ  ስላለብኝ ከጥር 1 ቀን 2008 ጀምሮ ስለምለቅ የሚረከበኝ ሰው ይመደብልኝ፤› የሚል መልዕክት የያዘ በመሆኑ የብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በመልቀቂያ ዙሪያ ባለፈው ሰኞ ታኅሣሥ 25 ቀን 2008 ዓ.ም. በዝርዝር ከተወያየበት በኋላ ጥያቄውም የድርጅት መርሕ ስለሆነ መልቀቂያቸውን ተቀብሎታል፡፡ ሆኖም ወደፊት ግን በትርፍ ጊዜያቸው ወይም በሌላ አማራጭ ፌዴሬሽኑን እንዲያግዙ ቢደረግ የተሻለ መሆኑን በማመን ማክሰኞ ጠዋት ታኅሳስ 26 ቀን 2008 ዓ.ም. የመልቀቂያ ወረቀቱን ሰጥቷቸዋል፤›› ብለዋል፡፡

አቶ ዱቤ ‹‹በሥራ ገበታዬ ላይ ነኝ፤›› ይላሉ ለሚለው ቀጣይ የሪፖርተር ጥያቄ አቶ ቢልልኝ፣ ‹‹ቀደም ሲል ከተናገርኩት ውጪ በሥራ ገበታቸው ላይ ስለመሆናቸው የማውቀው ነገር የለም፤›› ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቋሙን እንደ አዲስ ለማደራጀት የመሠረታዊ ሥራ ሒደት ለውጥ በመተግበር ላይ እንደሚገኝ የሚናገሩ አሉ፡፡ ይሁንና ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በቅርቡ የፌዴሬሽኑን ሕጋዊ ማኅተም በመጠቀም አትሌት ያልሆኑ፣ ነገር ግን ትክክለኛ አትሌት መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ተሰጥቷቸው ወደ ተለያዩ የአውሮፓ አገሮች ሊወጡ ሲሉ በኤምባሲዎች ትብብር የተደረሰባቸው መሆኑ መዘገቡ ይታወሳል፡፡ ይህንኑ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ አምኖ ለድርጊቱ ቀጥታ ተጠያቂ ናቸው ብሎ ያመነባቸው የፌዴሬሽኑ ሠራተኞች ከሥራ እንዲሰናበቱ መወሰኑም ይታወቃል፡፡

     

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...