Monday, February 26, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየህዳሴው ግድብ በግብፅ ላይ ጉልህ ጉዳት እንደማያደርስ የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪ ገለጹ

የህዳሴው ግድብ በግብፅ ላይ ጉልህ ጉዳት እንደማያደርስ የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪ ገለጹ

ቀን:

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በግብፅም ሆነ በሱዳን ላይ ጉልህ ጉዳት እንደማያደርስ፣ በግድቡ ላይ ጥናት ያደረጉ የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪ ኬቨን ዊል (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

በግድቡ የውኃ ሙሌት ሞዴል ላይ ያደረጉትን ጥናታዊ ምርምር ባለፈው ሳምንት በግብፅ አሌክሳንድርያ ከተማ ለተገኙ የተፋሰሱ የምሥራቅ አፍሪካ ጋዜጠኞች ባረቀቡበት ወቅት ነው፣ ኢትዮጵያ የምትገነባው የህዳሴ ግድብ ጉልህ ጉዳት እንደማያደርስ ተመራማሪው የተናገሩት፡፡

ኢትዮጵያ ግድቡን መሙላት ስትጀምር የታችኛው የዓባይ ተፋሰስ አገር ወደሆነችው ግብፅ የሚፈሰው የውኃ መጠን በከፍተኛ ደረጃ ይቀንሳል የሚለውን የግብፅ ሥጋት የማይቀበሉት የግድቡን የውኃ አሞላል በተመለከተ የራሳቸውን ምርምር ያደረጉት ተመራማሪው ኬቨን ዊል፣ ‹‹ወደ ግብፅ የሚፈሰው የውኃ መጠን መቀነሱ አይቀሬ ነው፡፡ ነገር ግን የተቀናጀ ትብብር በአገሮቹ መካከል ከተፈጠረ ሥጋቱ መቶ በመቶ መቀረፍ የሚችል ነው፤›› ብለዋል፡፡ እርሳቸው እንደሚሉት ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን የግድቡን የውኃ ሙሌት በተመለከተ ሁለት ዓይነት የአሞላል ሥልቶችን መከተል ይችላሉ፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

አንደኛው በሦስቱ አገሮች ስምምነት ተግባራዊ የሚደረግ ዓመታዊ የውኃ አለቃቀቅ ሲሆን፣ ይህም ዝናባማና ደረቅ ወቅቶችን መሠረት ያደረገ ነው፡፡ ሁለተኛው አማራጭ ደግሞ በስምምነት የተወሰነ የውኃ መጠን በየዓመቱ ግድቡን እንዲሞላ ማድረግ (Fixed Yearly Increase) ናቸው፡፡

የመጀመርያው የሙሌት ሥልት ተመራጭ እንደሆነ የሚናገሩት ተመራማሪው በዚህ ሥልት በዝናባማ ወቅት ግድቡን በፍጥነት መሙላት፣ እንዲሁም በደረቅ ወቅት የሙሌት መጠኑን መቀነስ የሚያስችል በመሆኑ አስተማማኝ የውኃ ፍሰት እንደሚኖር ለግብፅ ያረጋግጣል ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ የመጀመርያውን ዙር የውኃ ሙሌት በዚህ ዓመት እንደምትጀምር ግምት እንዳላቸው፣ ይህ የመጀመርያ ዓመት የውኃ ሙሌት የግድቡን የታችኛው አካል ሁለት ተርባይኖች ኃይል ለማመንጨት ለመሞከር የሚያስችል እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ሁለቱን ተርባይኖች ለመሞከር የሚደረገው የመጀመርያ ዓመት ሙሌት በግድቡ ውስጥ 15 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውኃ ማቆር የሚያስችል ቢሆንም፣ በግብፅ ላይ ምንም ዓይነት ተፅዕኖ እንደማያመጣ ያስረዳሉ፡፡ የሚሰጡትም ምክንያት የተጠቀሰውን ያህል መጠን የውኃ መዋዠቅ በግብፅ የአስዋን ግድብ ላይ የተለመደ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የሁለተኛው ዓመት የውኃ ሙሌት የህዳሴውን ግድብ የቀሩ 14 ተርባይኖች ወደ ኃይል ማመንጨት ሙከራ እንዲገባ የሚያደርግ ከፍተኛ የውኃ ሙሌት በመሆኑ ግብፅን ሊሰማት እንደሚችል፣ ነገር ግን ግብፅ የድርቅ ወቅት የውኃ አስተዳደር ሥልቷን በመጠቀም የውኃ መጠን ቅናሹን ያለ ምንም ጉዳት ማለፍ እንደምትችል ያስረዳሉ፡፡

በዚህ መንገድ ኢትዮጵያ ግድቧን በአምስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ሞልታ ማጠናቀቅ እንደምትችል በጥናታቸው ማረጋገጣቸውን ጠቁመው፣ ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ግድቡን ለመሙላት ይፋ ያደረገችው የጊዜ ርዝማኔ አለመኖሩንና በጉዳዩ ላይም ሦስቱ አገሮች በተራዘመ ድርድር ላይ እንደሚገኙም አስታውቀዋል፡፡

‹‹የህዳሴው ግድብ በታችኛው ተፋሰስ አገሮች ላይ ጉልህ ጉዳት አያደርስም፤›› የሚል ከጥናት የመነጨ የጠነከረ አቋም የያዙት ተመራማሪው ኬቨን፣ በተለይ ሱዳን ከምንጊዜውም የተሻለ የውኃ መጠን ልታገኝ እንደምትችል ይናገራሉ፡፡

ይሁንና በግድቡ ምክንያት ሱዳን ልታገኝ የምትችለውን ተጨማሪ የውኃ መጠን መጠቀም ትችላለች ወይ የሚለው ጥያቄ፣ ሱዳን እ.ኤ.አ. በ1959 ከግብፅ ጋር የፈረመችው የውኃ ድርሻ ውል አካል ሊሆን እንደሚችል ጠቆም አድርገው አልፈዋል፡፡

በግብፅ አስዋን ግድብ ያለው ዓመታዊ የትነት መጠን 10.9 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ሲሆን፣ የህዳሴው ግድብ የውኃ ሙሌት ይኼንን የትነት መጠን በከፍተኛ ደረጃ በመቀነስ ለሙሌቱ እንዲውል እንደሚያደርግ፣ በተጨማሪም ግድቡ በመገንባቱ ወደ ግብፅና ሱዳን ተጠርጎ የሚሄደውን የደለል መጠን 86 በመቶ እንደሚያስቀር ተመራማሪው አስረድተዋል፡፡

በመሆኑም አገሮቹ በድርድር ጊዜ ከሚፈጁ እንዲተባበሩና እንዲተማመኑ፣ መተማመን የሚመነጨው ደግሞ እውነተኛ መረጃን በመለዋወጥ መሆኑን በመጥቀስ መክረዋል፡፡ ኬቨን ዊል በውኃ ሀብት አስተዳደርና የውኃ ኢንጂነሪንግ ዘርፍ የ15 ዓመታት ልምድ ያካበቱና በአሜሪካ የኮሎራዶ ወንዝ ውዝግብን ለመፍታት፣ አሜሪካና ሜክሲኮን ወደ ድርድር በማምጣት ውጤታማ የሆኑ ምሁር መሆናቸው ይነገራል፡፡

ተመራማሪው ይህንን ቢያሳስቡም ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን የግድቡን ሙሌት በተመለከተ የሚደረገውን ጥናት ለማስጀመር አሁንም እልህ አስጨራሽ ውዝግብ ውስጥ ናቸው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...