Friday, September 22, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊፋሺስት ኢጣሊያ ድል የተመታበት 75ኛ ዓመት ሊከበር ነው

ፋሺስት ኢጣሊያ ድል የተመታበት 75ኛ ዓመት ሊከበር ነው

ቀን:

የፋሺስት ኢጣሊያ ሠራዊት ድል የተመታበትና የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር የተመሠረተበት 75ኛ ዓመት የአልማዝ ኢዮቤልዩ፣ አርበኞች የከፈሉትን መስዋዕትነት በሚያትቱ ሲምፖዚየሞችና ልዩ ልዩ ዝግጅቶች እንደሚከበር ማኅበሩ አስታወቀ፡፡ ሚያዝያ 27 ቀን 2008 ዓ.ም. የሚከበረው የአልማዝ ኢዮቤልዩ ወረራው ስላደረሰው ተፅዕኖ የሚያወሱና፣ የዛሬው ትውልድ ያለበትን ኃላፊነት የሚያመላክቱ ጥናቶች የሚቀርቡበት እንደሆነ የማኅበሩ ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን ገልጸዋል፡፡

ታኅሣሥ 26 ቀን 2008 ዓ.ም. በማኅበሩ ጽሕፈት ቤት በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ፕሬዚዳንቱ እንደተናገሩት፣ በአልማዝ ኢዮቤልዩ አከባበሩ ስለ ተጋድሎና የማኅበሩ ታሪክ የሚያወሱ ጽሑፎች ተዘጋጅተዋል፡፡

ከ1928 እስከ 1933 ዓ.ም. የተካሄደውን መራር ትግል የተመረኮዙ የኪነ ጥበብ ሥራዎች የሚመዘኑባቸው የውይይት መድረኮች በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና በሌሎችም ከፍተኛ ትምህርት ተቋሞች እንደሚዘጋጁ ከገለጻቸው ለመረዳት ተችሏል፡፡ በጦርነቱ ወቅት አርበኞች የተገለገሉባቸው የጦር መሣሪያዎችና ሌሎችም ቁሳቁሶች በዓውደ ርእይ  እንደሚቀርቡም ይጠበቃል፡፡ በተጨማሪም በጦርነቱ ወቅት ከኢትዮጵያ ጎን ለቆሙ አገሮች ምስጋና የሚሰጥበት ሥነ ሥርዓት ይኖራል፡፡

የማኅበሩ ፕሬዚዳንት በዓሉን ምክንያት አድርገው ወጣቶች በአገሪቱ የተንሰራፋውን ሙስና፣ የመልካም አስተዳደር እጦትና ኪራይ ሰብሳቢነት እንዲታገሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በዓሉ እርቅ የሚሰበክበት እንደሆነም አክለዋል፡፡ ‹‹ደማችን ፈሷል፣ አጥንታችን ተከስክሷል ዛሬ ከዛ አልፈን የእርቅና ይቅር የመባባል ጊዜ ላይ ነን፤›› ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ጣልያንን ጨምሮ ከበርካታ አገሮች ጋር ትስስር እንዳላት አንስተው፣ በቀደመው ጠብ ሳይሆን በይቅር ባይነት አብሮ መሥራት የተሻለ መሆኑን ላይ አተኩረዋል፡፡ አገሪቱ እየለመነች ሳይሆን ራሷን ችላና ማንነቷን አስከብራ እንድትዘልቅ  መሥራት ደግሞ የግድ እንደሆነ አሳስበዋል፡፡

ድሉ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በፋሽስት ኢጣልያ ሥር የነበሩ ሌሎች የአፍሪካ አገሮችም ጭምር እንደሆነ የገለጹት ልጅ ዳንኤል፣ የማኅበሩ አባላት የሆኑና ወደ 45,000 የሚደርሱ አርበኞች ተጋድሎ የሚታሰብበት በዓል እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ ብዙ አርበኞች ከዕድሜ መግፋት፣ በአቅም እጦትም ፈታኝ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ ጠቁመው፤ ከመንግሥት በሚመደብላቸው በጀት እርዳታ ለማድረግ ቢጣጣሩም በቂ አለመሆኑን አመልክተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ሪፖርት ምን ይዟል?

ለአሜሪካ ድምፅ አማርኛ ዝግጅት የስልክ አስተያየት የሰጡ አንድ የደንበጫ...

መንግሥት በአማራ ክልል ለወደሙ የአበባ እርሻዎች ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት በቢዝነስ...

አምናና ዘንድሮ!

እነሆ መስከረም ጠብቶ በአዲስ መንፈስ ተሞልተን መንገድ ጀምረናል። ‹‹አዲስ...