በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዴሚ ሥር የሚገኘው የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ የሥነ ጥበባት ማዕከል፣ በሠዓሊ ታምራት ሥልጣን የተዘጋጀ ‹‹መክተፏ – የሕይወት ታሪክ›› የተሰኘ የሥዕል ዐውደ ርዕይ ቅዳሜ ግንቦት 11 ቀን 2010 ዓ.ም. በ9፡00 ሰዓት ይከፍታል፡፡
ማዕከሉ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ ዐውደ ርዕዩ ኢትዮጵያዊ መክተፊያ ቅርፅ ያላቸውና የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ እንደ ኅብረተሰብ እንዲቀጥል እናቶች ያላቸውን አበርክቶት በአዲስ ዕይታ አቅርቧል፡፡ በመክፈቻው ዕለት በነጋሪት ባንድ ሙዚቃዊ ክዋኔ ጥበብ፣ በፈንድቃ የዳንስ ቡድን የዳንስ ትዕይንት ይቀርባልም ብሏል፡፡
ከቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ከፍ ብሎ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጉለሌ ቅርንጫፍ አካባቢ 500 ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘው በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዴሚ፣ የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ የሥነ ጥበባት ማዕከል የሚቀርበው ዐውደ ርዕይ ለሁለት ወራት ለሁሉም ኅብረተሰብ ለዕይታ ክፍት ይሆናል፡፡