Wednesday, June 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊአገልግሎት የማይሰጡ የወጣት ማዕከላት መበራከታቸው ተገለፀ

አገልግሎት የማይሰጡ የወጣት ማዕከላት መበራከታቸው ተገለፀ

ቀን:

በኢትዮጵያ ከሚገኙ ሦስት ሺሕ የወጣት ማዕከላት መካከል በተለያዩ አስተዳደራዊና መዋቅራዊ ችግሮቸ ሳቢያ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙት 998ቱ ብቻ እንደሆኑ የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በአሁኑ ወቅት 183 የወጣት ማዕከላት ሙሉ ለሙሉ አገልግሎት ያቆሙ ሲሆን፣ 10 ማዕከላት መፍረሳቸውን፣ አምስት ለሌላ አገልግሎት መዋላቸውን የማዕከላቱ አገር አቀፍ አሀዛዊ መግለጫ ያሳያል፡፡ አብዛኞቹ የፈረሱ ማዕከላት በገጠራማው የትግራይ ክፍል የሚገኙ መሆናቸውም ታውቋል፡፡

     በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በጀት ዓመት ውስጥ በአገር አቀፍ ደረጃ ያሉ የወጣት ማዕከላትን ቁጥር ከ5800 በላይ የማድረስ ግብ የተያዘ ቢሆንም፣ እስካሁን ግን ቁጥራቸው ከ3000 ሊዘል አልቻለም፡፡ ከእነዚህ ውስጥ 694 ማዕከላት በግንባታ ሂደት ላይ መሆናቸውን፣ 410 ማዕከላት ደግሞ ግንባታቸው ቢጠናቀቅም እስካሁን አገልግሎት መስጠት አለመጀመራቸውን ማወቅ ተችሏል፡፡

- Advertisement -

     በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ ከሚገኘው የወጣት ቁጥር አንፃር  የተገነቡ ማዕከላት አነስተኛ መሆናቸውን የገለጹት የሚኒስቴሩ የወጣት ማዕከላትና ልማት ዳይሬክተሯ ወይዘሪት እሌኒ ታደለ፣ ያሉትም በአግባቡ አገልግሎት መስጠት አለመቻላቸው ችግሩን እንዳባባሰውና የማዕከላቱ እጥረት በተለይም በገጠርና በአርብቶ አደር አካባቢ ከፍተኛ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ ለዚህም ‹‹በማንኛውም የከተማ ልማትና የማዘጋጃ ቤት አስተዳደር ላይ የወጣት ማዕከላትና የማዘውተሪያ ስፍራዎች ግንባታ ተደራሽ ማድረግ›› የሚለው የከተማ ልማት ፖሊሲ ማስፈፀሚያ ደንብ አለመውጣቱ የፈጠረው ክፍተቱ መሆኑ ተሰምሮበታል፡፡  

     ማዕከላቱ ወጥ የሆነ የአስተዳደርርዓት የሌላቸው መሆኑ፣ አንዳንዶቹ ለተጠያቂነት በማይመች መልኩ በቦርድ፣ በወጣት አደረጃጀትና በመሳሰሉት የሚመሩ መሆናቸውም ለተፈጠረው ክፍተት ዓይነተኛ ሚና ተጫውቷል፡፡ በአብዛኛው በማዕከላት የሚሰጡ አገልግሎቶች በመንግሥት መዋቅር ውስጥ በሚቀጠሩ ባለሙያዎች ሳይሆን በበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች የሚሰጥ መሆኑም ሌላው ችግር ነው፡፡  

     ማዕከላቱን ለተለያዩ አገልግሎቶች እንዲውሉ የሚደረግ ሲሆን፣ ወጣቶች ተገቢውን አገልግሎቶች እንዳያገኙና ከማዕከላት እንዲርቁ እየሆነ ይገኛል፡፡ ‹‹አንዳንድ የወጣት ማዕከላት ከታለመላቸው ዓላማ ውጪ እየዋሉ ነው፡፡ ድንገተኛ ጉብኝት በምናደርግበት ወቅት አንዳንዶቹ ጫት መቃሚያ፣ አልኮል መጠጦች መሸጫ ሆነው እናገኛቸዋለን፤›› ያሉት ደይሬክተሯ እንደ አጠቃላይ ሲታይ የማዕከላቱ ዓላማና እየሰጡ ያለው አገልግሎት ለየቅል መሆናቸውን ሳይጠቅሱ አላለፉም፡፡

     የቦርድ አባላት የማዕከሉን ሥራ ከመደገፍ፤ አገልግሎትን ጥራትና ተደራሽነትን ከማረጋገጥ አንፃር ትኩረት አድርጎ አለመሥራት፣ ቦርዱን የሚቆጣጠር አካል አለመኖር፣ በየደረጃው የሚገኙ የመንግሥት አስፈፃሚ አካላት ለማዕከላቱ ትረኩት አለመስጠት ወይም የሌላ አካል አድርጎመመልከት አዝማሚያ መኖር፣ ማዕከላቱ የተገነቡበትንላማ ለማኅበረሰቡ በማስተዋወቅ እንዲደግፋቸው አለማድረግ፣ የተቋቋሙበት ግልፅ አዋጅ አለመኖር፣ ማዕከላቱን የማስገንባት የማስተዳደር የመደገፍ ኃላፊነት በግልፅ የተሰጠው አካል አለመኖር፣ የሰው ኃይል ቅጥርና ምደባን በተመለከተ የተቀረፀ አሠራር ሥርዓት አለመኖር የማዕከላቱን የባለቤትነት ማረጋገጫ እንዲኖራቸው የሚደግፍ አሠራር አለመዘርጋቱም ትልቅ ችግር ሆኖ ተገኝቷል፡፡

     ማዕከላቱ ለሌላ አገልግሎት ሲውሉ፣ ሲፈርሱ  ሲዘጉ ይህን በሚያደርገው አካል ላይ ሕጋዊ ዕርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል ሥርዓት አለመኖሩን በዘርፉ በሚታዩ ችግሮችና መፍትሔዎቻቸው ዙሪያ ባለፈው ሳምንት መገባደጃ በአዳማ ተዘጋጅቶ በነበረው ውይይት ላይ ተገልጿል፡፡

በአገር አቀፍ ደረጃ የሚገኙ ሁሉም ማዕከላት ወጥነት ያለው የግንባታ ዲዛይን እንደማይከተሉ፣ ዲዛይኑ የወጣቱን ወቅታዊ ፍላጎት ያላገናዘቡና ሳቢ እንደማይሆኑ፤ ቦታ የለም በሚል ምክንያት ማዕከላት ከከተማ ውጪና ለወጣቶች ምቹ ባልሆኑ አካባቢዎች እንደሚገነቡ፣ ዲዛይናቸው ሴቶችንና አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ያላደረገ እንደሆኑ፣ በቂ የመሠረተ ልማት አውታሮች እንደማይሟሉ፣ የግንባታ ጥራት ችግር እንዳለባቸው፣ አገለግሎት መስጠት ከጀመሩም በኋላ ወቅቱን ጠብቆ የማደስ ችግር እንደሚታይ በዕለቱ የቀረበው ጽሑፍ ያስረዳል፡፡  

     እንዲህ ያሉ ችግሮችን ለመፍታትም ማዕከላቱን የሚገዛ የአገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርድ ይፋ ተደርጓል፡፡ ስታንዳርዱ ከወቅቱ የወጣቶች ፍላጎትና አገሪቱ ከደረሰችበት የዕድገት ደረጃና ነባራዊ ሁኔታ አንፃር ተቃኝቶ የተዘጋጀ ነው፡፡ ስታንዳርዱ የወጣቶች ሰብእና ልማት ማዕከላት በሚሰጡት የአገልግሎት ዓይነቶችና ጥራት አንፃር ሞዴል፣ ሁለገብ፣ መካከለኛና አነስተኛ በሚል በአራት ዋና ዋና ክፍሎች ከፍሎ አስቀምጧል፡፡  

     በሞዴል ማዕከላት የሚሰጠው የቤተ መጻሕፍት አገልግሎት፣ የካፍቴሪያወጣት ተኮር የጤና አገልግሎቶች፣ ሁለገብ አዳራሽ፣ የቤት ውስጥ ጨዋታዎች፣ የቤት ውጭ ጨዋታዎች፣ የመረጃ ማዕከል (አይሲቲ)፣ የገላ መታጠቢያ፣ የኪነ ጥበባት፣ የሥልጠና፣ የሥነ ልቦና ድጋፍና ምክር፣ ሁለገብጂምናዚየም፣ የበጎ ፈቃድ፣ የሚኒ ሚዲያ፣ የፈጠራናርቶ ማሳያ አገልግሎቶችና መለስተኛ ሱቅ ይሆናሉ፡፡

     ‹‹ስታንዳርዱን ብቻ መከለሳችን ያለውን ችግር ይቀርፋል ብለን አናስብም፡፡ ማዕከላቱ በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ተቀጥሮ የሚሠራ ተጠያቂ ሰው ማስቀመጥ አለባቸው፡፡ ይህ በአዲስ አበባ ተሞክሮ ውጤታማ መሆኑ ተረጋግጧል፣ ወደ ሌሎች ክልሎችም መስፋፋት አለበት፤›› ብለዋል ወይዘሪት እሌኒ፡፡
 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...