Thursday, June 13, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ንግድ ባንክ አስተዳደራዊ የመዋቅር ለውጥ አደረገ

spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እስካሁን ሲሠራበት የነበረው አስተዳደራዊ መዋቅር ላይ ለውጥ አደረገ፡፡ በዚህም መሠረት የባንኩ ፕሬዚዳንትና ምክትል ፕሬዚዳንት መዋቅሮች ላይ ማሻሻያ አድርጓል፡፡

በማሻሻያውም የባንኩን ፕሬዚዳንት አቶ በቃሉን ዘለቀ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብሎ የሰየመ ሲሆን፣ በሥራቸውም ስምንት ሥራ አስፈጻሚዎችን አስቀምጧል፡፡ በተመሳሳይ ከዚህ ቀደም ምክትል ፕሬዚዳንት የነበሩት አምስት ኃላፊዎችን በብድር፣ በሰው ኃይል፣ በፋይናንስና በኦፕሬሽን ምክትል ሥራ አስፈጻሚ ሆነው በሁለተኛው የሥልጣን ዕርከን የተሾሙ ሲሆን፣ በሥራቸውም 11 ምክትል ፕሬዚዳንቶች  ተሰይመዋል፡፡

ከተሾሙት 11 ምክትል ፕሬዚዳንቶችም ሦስቱ ከዚህ ቀደም በተለያዩ የሥራ ኃላፊነቶች በምክትል ፕሬዚዳንት ደረጃ የሠሩ ሲሆን፣ ሰባቱ ደግሞ በዋና መሥሪያ ቤትና በዲስትሪክቶች የሠሩ ናቸው፡፡ ሌላኛው ምክትል ፕሬዚዳንት በቀድሞ አደረጃጀት ከሥራ አስፈጻሚነት አድገው የመጡ ናቸው፡፡

ከአዲሱ ሹመት ጋር በተያያዘም ከሰባቱ ምክትል ፕሬዚዳንት ውስጥ አምስቱ በዳይሬክተር ደረጃ በዋና መሥሪያ ቤት የሠሩ ሲሆን፣ ሁለቱ ደግሞ የዲስትሪክት ሥራ አስኪያጅ የነበሩ ናቸው፡፡ ይህ አዲስ መዋቅር የባንኩ የአምስት ዓመት ስትራቴጂካዊ ዕቅድ አካል ነው ሲሉ የባንኩ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ በልሁ ታከለ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም ንግድ ባንክ እ.ኤ.አ. በ2025  ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ባንክ የመሆን ራዕዩን ዕውን ለማድግ እየሠራቸው ያሉትን ሥራዎች ያግዛል ተብሏል፡፡

የመዋቅር ለውጡ ከላይኛው የሥልጣን ዕርከን በተጨማሪ ወደ ታች ወርዶ ተፈጻሚ እየሆነ እንደሚገኝ አቶ በልሁ የገለጹ ሲሆን፣ በቀጣይም ሌሎች ሥራዎችም ይከተላሉ ተብሏል፡፡

በ1930ዎቹ እንደተመሠረተ የሚነገርለትና 75ኛ ዓመቱን እያከበረ የሚገኘው ንግድ ባንክ፣ በአሁን ወቅት ላይ በሥሩ 33 ሺሕ ቋሚ ሠራተኞችን ቀጥሮ ይዟል፡፡

የባንኩ ጠቅላላ ተቀማጭ ገንዘብ ከዘጠኝ ዓመት በፊት ከነበረው 56 ቢሊዮን ብር ወደ 436 ቢሊዮን ብር ያደገ ሲሆን፣ በተመሳሳይ የባንኩ አጠቃላይ ሀብት ወደ 540 ቢሊዮን ብር ይጠጋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ባንኩ የቅርንጫፎቹን ብዛት 1,260 ማድረስ ችሏል፡፡     

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች