Tuesday, July 16, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበኢትዮጵያ አዲስ የአየር ንብረት ለውጥ እንደሚኖር ተገለጸ

በኢትዮጵያ አዲስ የአየር ንብረት ለውጥ እንደሚኖር ተገለጸ

ቀን:

የውኃ እጥረት ያጋጥማቸዋል ከተባሉት አገሮች ኢትዮጵያ አንዷ ነች

የዓለም የሙቀት መጠን እስከ ሁለት ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ከጨመረ ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች የሚኖረው የሙቀት መጠን 2.5 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ፣ 3 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ እና 3.5 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ሊደርስ እንደሚችልና ይህም ያልተለመደና አዲስ የአየር ንብረት ለውጥ እንደሚያስከትል ተገለጸ፡፡ ክስተቱ ውርጭ እንዲጠፋ፣ አልፎ አልፎ ብቻ ይከሰቱ የነበሩት ድርቅና ጎርፍ የመሳሰሉ ክስተቶች እንዲደጋገሙና በስፋት እንዲከሰቱ እንደሚያደርግ ፕሮፌሰር ወልደአምላክ በዕውቀት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲት የማኅበራዊ ሳይንስ ኮሌጅ ዲን፣ የኢትዮጵያ ወጣት ሳይንስ አካዴሚ መሥራችና ሊቀመንበር አስታወቁ፡፡

ፕሮፌሰሩ፣ ይህንን ያስታወቁት ታኅሳስ 21 ቀን 2008 ዓ.ም. በተካሄደው ወርሃዊ ሳይንሳዊ ገለፃና ውይይት መድረክ ላይ ‹‹የአየር ንብረት ለውጥ በኢትዮጵያ ከሁለት ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ የሙቀት ጭማሪ ጋር መኖር ምን ማለት ነው?›› በሚል ርዕስ ትኩረት ያደረገ ጥናታዊ ጽሑፋቸውን ባቀረቡበትና ከታዳሚዎቹም ለተሰነዘሩት ጥያቄዎች መልስና ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው፡፡

እንደ ፕሮፌሰር ወልደአምላክ ማብራሪያ፣ የውኃ እጥረት፣ የሰብል ተባዮችና የእንስሳት በሽታ መታየትም በአዲሱ የአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ከሚመጡ ክስተቶች መካከል ተጠቃሾች ናቸው፡፡ ከዚህም ሌላ እ.ኤ.አ በ2050 ሊኖር ከሚችለው አገራዊ ምርት አሥር በመቶ ቅነሳ እንደሚያሳይ አንድ ጥናት ጠቁሟል፡፡ በዚህ ዓመት ከአሥር ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ወገኖችን ለችግር የዳረገውና በኢሊኖ ሳቢያ የተከሰተውም ድርቅ ከአየር ንብረት ለውጡ የመነጨ ነው፡፡

የአገሪቱ 70 ከመቶ ያህሉ ክፍል ለከፍተኛ ሙቀት ተጋላጭ መሆኑንና 80 ከመቶ የሚሆነው የእንስሳት ሀብት ደግሞ የሚኖረው በዚህ ክፍል መሆኑም ችግሩን እንደሚያባብሰው ተናግረዋል፡፡ ይህን ከመሰለው የአየር ንብረት ለውጥ ጋር አብሮ ለመኖር የሚያስፈልገው መላመድ ሳይሆን መለወጥ ማለትም ለተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ፣ ለውኃ ልማት፣ ለአረንጓዴ የኃይል ምንጭ ማደግና መስፋፋት በተጠናከረና ቀጣይነት ባለው መልኩ መሥራት እንደሆነ አሳስበዋል፡፡ ከዚህም ሌላ ለቦታው አዲስና ተስማሚ ቴክኖሎጂን ማስረጽ ግድ ይላል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ እ.ኤ.አ በ2025፣ 2030 እና 2050 የውኃ ችግር ያጋጥማቸዋል ተብለው ከሚገመቱ አገሮች መካከል አንዷ ኢትዮጵያ መሆኗን ገልጸዋል፡፡ ‹‹የውኃ ሀብታችን እንደምናስበው የተትረፈረፈ አይደለም፡፡ በጥንቃቄ መጠቀምና ማልማት አማራጭ የሌለው መፍትሔ ነው›› ሲሉም አስረድተዋል፡፡

በሙቀት ምክንያት የገፀ ምድር ውኃ እጥረት ይገጥማል፡፡ የከርሰ ምድርም ውኃ እጥረት መከሰቱ አይቀሬ ነው፡፡ የገፀ ምድር ውኃ እጥረት ባጋጠመ ጊዜ በከርሰ ምድር ውኃ ላይ ትኩረት ሲደረግ ይስተዋላል፡፡ ትኩረቱ በዚህ መልኩ ከቀጠለ ግን አገሪቷ የከርሰ ምድር ውኃ ሀብቷ እየተመናመነ በኋላም እያለቀ እንደሚሄድና ችግሩን የከፋ እንደሚያደርገው ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዴሚ ያዘጋጀውና በአዲስ አበባ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የስብሰባ አዳራሽ በተከናወነው በዚሁ የውይይት መድረክ፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና የኢንስቲትዩቱ ማኅበረሰብ፣ የአየር ንብረት ለውጥ ተመራማሪዎችና ሙያተኞች የመንግሥትና የግል ድርጅቶች ኃላፊዎችና ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሚዲያው በሕዝብ የህሊና ችሎት ከተዳኘ በቂ ነው!

መሰንበቻውን ድንገት ሳይታሰብ ያለ ማስጠንቀቂያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ...

የባህር በር ጉዳይ

በታምሩ ወንድም አገኘሁ ድሮ ድሮ ገና ልጅ ሆኜ ፊደል እንደቆጠርኩ...

አገሩ ፖለቲካዊ ስክነትና መደማማጥ ያስፈልገዋል

በንጉሥ ወዳጀነው    ኢትዮጵያ የሁላችንም የጋራ ቤት ነች፡፡ ‹‹ጥያቄዬ ተመለሰልኝ››፣...

የመንግሥት የሰብዓዊ መብት ተቋም ለምን የመንግሥት ሚዲያን ማስተማር አቃተው

በገነት ዓለሙ የአገራችን የ2016 የበጀት ዓመት መሰናበቻና የአዲሱ የ2017 በጀት...