Tuesday, January 31, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልየኢትዮጵያን ሙዚቃ በ“አሪፍ ዘፈን” ድረ ገጽ

የኢትዮጵያን ሙዚቃ በ“አሪፍ ዘፈን” ድረ ገጽ

ቀን:

የኢትዮጵያን ሙዚቃዎች በድረ ገጽ በማቅረብ የሚታወቀው አሪፍ ዘፈን፣ በተንቀሳቃሽ ስልኮች ላይ በሬዲዮ መልክ ሙዚቃዎችን ማስተላለፍ መጀመሩን አስታውቋል፡፡ ከአራት ዓመታት በፊት በይፋ አገልግሎት መስጠት በጀመረው ድረ ገጽ አዲስ የሙዚቃ አልበሞች፣ ነጠላ ዜማዎች እንዲሁም ቆየት ያሉ ዘፈኖች ይገኙበታል፡፡ ነዋሪነታቸው አሜሪካ በሆነ ወጣቶች የተመሰረተው አሪፍ ዘፈን መጠሪያውን ሳይለውጥ በሬዲዮ የ24 ሰዓት አገልግሎት መስጠት የጀመረው ከሳምንታት በፊት ነው፡፡

የድረ ገጹ ዴቨሎፐር በፍቃዱ አየነው ለሪፖርተር እንደገለፀው፣ የአሪፍ ዘፈንን አፕልኬሽን ዳውንሎድ በማድረግ የሬዲዮ አገልግሎቱን ማግኘት ይቻላል፡፡ አድማጮች የሚፈልጉትን ዓይነት ሙዚቃ ከድረ ገጹ ከመረጡ በኋላ የሚያዳምጡ ሲሆን፣ 18 የጣቢያ ምርጫዎች ይሰጣል፡፡

ከቀረቡት ምርጫዎች መካከል ሬጌ፣ ሮክ፣ ሂፕኃፕ፣ በመሣሪያ የተቀነባበሩና ባህላዊ ሙዚቃዎች ጥቂቱ ናቸው፡፡ በተጨማሪም መዝሙሮች፣ ቆየት ያሉ ዘፈኖች፣ ለአውደ ዓመት ወይም ለተለያዩ ዝግጅቶች የሚሆኑ ሙዚቃዎችን ማግኘት ይቻላል፡፡ አድማጮች የሚወዱትን ሙዚቃ ላይክ ሲያደርጉ ከወደዱት የሙዚቃ ስልት ጋር ተመሳሳይ የሆኑ ሌሎች ሙዚቃዎችም ወደ ተንቀሳቃሽ ስልኮቻቸው ይላካሉ፡፡

ዲስከቨሪ የተባለው ምድብ አድማጮች የወደዷቸውን ዘፈኖች ላይክ ሲያደርጉ ይመዘግባል፡፡ ሌሎች አድማጮችም ላይክ የሚያደርጓቸውን ሙዚቃዎች ይመዘግብና ተመሳሳይ ምርጫ ያላቸው አድማጮች የሚሰሟቸውን ሙዚቃዎች የአንዳቸውን ለሌላቸው ይልክላቸዋል፡፡ ይህ አሠራር አንድ አድማጭ የማያውቃቸውን ነገር ግን ካለው የሙዚቃ ምርጫ አንጻር ሊወዳቸው እንደሚችል የታመነባቸው ሙዚቃዎችን እንዲያዳምጥ የሚደረግበት ነው፡፡

ሌላው ምድብ ቱደይስ ሒትስ፣ በየዕለቱ የተመረጡ ሙዚቃዎች የሚለቀቁበት ሲሆን፣ አድማጮች የተለያዩ ዘፈኖችን በቅደም ተከተል ያዳምጣሉ፡፡ አሪፍ ዘፈን ከሌሎች ሬዲዮዎች የሚለየው የተለያዩ አድማጮች በተመሳሳይ ሰዓት እንደየምርጫቸው የተለያየ ሙዚቃ መስማት በመቻላቸው እንደሆነ በፍቃዱ ይናገራል፡፡

ሬዲዮው ከአድማጮች ጎን ለጎን ዘፋኞችንም ተጠቃሚ እንደሚያደርግም ይገልጻል፡፡ ድምጻውያን አዳዲስ ዘፈኖች ሲለቁ ድረ ገጹን ለማስተዋወቂያነት ይጠቀማሉ፡፡ ድረ ገጹ ኮንሰርቶች ሲዘጋጁም ያስተዋውቃል፡፡ አዲስ አልበም ሲወጣ ከአልበሙ ላይ አንድ ወይም ሁለት ሙዚቃ በድረ ገጹ በመጫን አድማጮች አልበሙን እንዲገዙ ያስተዋውቃሉ፡፡ “አድማጮች አዲስ የወጣ አልበም ላይ ያሉ ሙዚቃዎችን ባጠቃላይ በድረ ገጹ ካገኙ አልበሙን አይገዙም፤ ስለዚህ ሁለት ሙዚቃ ብቻ በነጻ በመልቀቅ አልበሙን እንዲገዙ ይደረጋል፤” ይላል በፍቃዱ፡፡

በእርግጥ በአይቱንስ ወይም ሌሎች የኦንላይን ግብይት የሚካሄድባቸው ድረ ገጾች ላይ አልበማቸው የሚሸጥ የኢትዮጵያ ሙዚቀኞች ውስን ቢሆኑም፣ ኦንላይን ለሚሸጡ ሙዚቀኞች ድረ ገጹ አማራጭ ይሰጣል፡፡ አድማጮችንም ወደ ግዥ ድረ ገጹ ይመራቸዋል፡፡

የአሪፍ ዘፈንን ሬዲዮ በአይፎን በነጻ ዳውንሎድ አድርጎ መጠቀም የሚቻል ሲሆን፣ አንድሮይድ ስልኮች ላይ በቅርቡ ሥራ እንደሚጀምር ከዴቨሎፐሩ ገለጻ ለመረዳት ተችሏል፡፡ እሱ እንደሚለው፣ አሪፍ ዘፈን በኢትዮጵያ ያለው ተደራሽነት ከውጭ አገር ያነሰ ነው፡፡ ይህ በአገሪቱ ካለው ውስን የኢንተርኔት ተደራሽነት ጋር የተገናኘ ነው፡፡ ይህን ለመቅረፍም ኦፍላይን (ያለ ኢንተርኔት ድረ ገጹን ዳውንሎድ በማድረግ ብቻ የሚሰጥ አገልግሎት) የመጀመር ዕቅድ አላቸው፡፡

በብዛት በድረ ገጽ በሚተላለፉ ሙዚቃዎች ድምጻውያን የሚገባቸውን ጥቅም ሳያገኙ ይቀራሉ፡፡ በፍቃዱ እንደሚለው፣ የኢንተርኔት ላይ ስርቆትን ለመከላከል ሕጋዊ የኦንላይን አሠራሮችን መዘርጋት የግድ ነው፡፡ አሪፍ ዘፈን ከኮፒራይት ሶሳይቲ ጋር እንደሚሰራና በቅርቡ የጸደቀው የሮያሊቲ ክፍያ በተግባር የሚውልበት አሰራር ሲተገበር እንደሚጠቀሙበት ይናገራል፡፡

አሁን ከአንዳንድ ድምጻውያን ጋር በመስማማት ክፍያ የሚሠጡበት አሠራር ቢዘረጉም የተጠናከረ አይደለም፡፡ “ከድምጻውያኑ ጋር አብረን በመሥራት ከስርቆት በጸዳ መልኩ በድረ ገጹ የሚጠቀሙበት አሰራር አለ፤” ሲል ይገልጻል፡፡ ከዚህ ቀደም ድምጻውያን ከኦንላይን ሽያጭ እንዲጠቀሙ ለማስቻል ልዩ ልዩ ሥልጠናዎች  መስጠታቸውንም ያክላል፡፡

የአሪፍ ዘፈን ማርኬቲንግ ሄድ ምዕራፍ ተክሌ፣ ከዓመታት በፊት የተነሱበት ዓላማ አሜሪካ ያሉ ኢትዮጵያውያን በቀላሉ የኢትዮጵያን ዘፈን እንዲያገኙ ለማስቻል ቢሆንም፣ ዛሬ ተደራሽነታቸው በዓለም ላይ ሰፍቶ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ተጠቃሚ እንዳላቸው ትናገራለች፡፡ ድረ ገጹ ከአድማጮች በተጨማሪ ድምጻውያንንና የሙዚቃ ኢንዱስትሪውን በአጠቃላይ እንደሚጠቅምም እምነቷ ነው፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የገጠር መሬት ማሻሻያና የመሬት ባለቤትነት ጥያቄ በኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ ከቅርብ ወራት ወዲህ መሬትን በተመለከተ ጠንከር ያሉ የለውጥ...

በፖለቲከኞች እጅ ያለው ቁልፍ

ኢትዮጵያ በተለይ ካለፉት አምስት ዓመታት ወዲህ ሰላሟ መረጋጋት አቅቶታል፡፡...

የኤክሳይስ ታክስ ረቂቅ አዋጅ ፓርላማው ያፀደቀውን አዋጅ የሚጥሱ ድንጋጌዎችን በማካተቱ እንዳይፀድቅ ተጠየቀ

ሰሞኑን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የኤክሳይስ ታክስ ማሻሻያ...

በፀጥታ ችግር ሳቢያ ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው አማራ ክልል የገቡ ዜጎች ቁጥር 800 ሺሕ መድረሱ ተነገረ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 112 ሺሕ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ...