Wednesday, February 28, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበዲላ ዩኒቨርሲቲ ጉዳት ካደረሰው የቦምብ ፍንዳታ በኋላ ትምህርት ቆመ

በዲላ ዩኒቨርሲቲ ጉዳት ካደረሰው የቦምብ ፍንዳታ በኋላ ትምህርት ቆመ

ቀን:

– አንድ የተማሪዎች መኖሪያ ሕንፃ ወድሟል

በዲላ ዩኒቨርሲቲ ታኅሳስ 21 ቀን 2008 ዓ.ም. ባልታወቁ ሰዎች ተወርውረዋል በተባሉት ሦስት የእጅ ቦምቦች ሁለት ተማሪዎች ለሞት ሲዳረጉ፣ ሦስት ተማሪዎች መቁሰላቸው ተገለጸ፡፡ በተፈጠረው አለመረጋጋገት ትምህርት መቋረጡንና ተማሪዎች ወደየመጡበት አካባቢዎች በመጓጓዝ ላይ መሆናቸውም ታውቋል፡፡

ከቦምብ ፍንዳታው ክስተት ማግስት ደግሞ በጊቢ ውስጥ መፀዳጃ ቤት አካባቢ ሁለት ተማሪዎች ታርደው ተገኝተዋል የሚል መረጃ እየተናፈሰ በመምጣቱ፣ ተማሪዎች ተረጋግተው መማር እንዳይችሉ እንዳደረጋቸው የሪፖርተር ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ነገር ግን የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ፍስሃ አሰፋ ተማሪዎች ታርደው ተገኝተዋል ተብሎ የሚናፈሰውን ወሬ ላይ ምርመራ የተደረገ ቢሆንም፣ ምንም ታርዶ የተገኘ ተማሪ አለመኖሩን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ኮሚሽነር ፍስሃ በቦምብ ፍንዳታው ሁለቱ ተማሪዎች መሞታቸውንና ሌሎች ሦስት ተማሪዎች ደግሞ መቁሰላቸውን ያረጋገጡ ሲሆን፣ የቦምብ ጥቃቱን ግን ማን እንዳደረሰው የክልሉና የፌዴራል ፖሊሶች በጋራ እየመረመሩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በተያያዘ ዜና በዩኒቨርሲቲው 280 ተማሪዎች የሚኖሩበት የጋራ መኖሪያ ቤት በእሳት ሙሉ በሙሉ መጋየቱን ኮሚሽነሩ ያረጋገጡ ሲሆን፣ ጉዳቱ በደረሰበት ቀን (ታኅሳስ 25 ቀን 2008 ዓ.ም.) ተማሪዎች በጋራ መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ያልነበሩ በመሆኑ በሰው ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት እንዳልደረሰ አመልክተዋል፡፡ ኮሚሽነሩ ‹‹የቃጠሎው መንስዔም እስካሁን ያልታወቀ በመሆኑ ምርመራ እየተካሄደ ነው፤›› ብለዋል፡፡ የቦምብ ፍንዳታው ካለፈው ወር ጀምሮ እየተቀጣጠለ ከመጣው የኦሮሚያ ተቃውሞ ጋር ግንኙነት ይኑረው ወይም አይኑረው በመንግሥት ባይገለጽም፣ የተለያዩ ወገኖች የየራሳቸውን መላ ምቶች እየሰጡ ይገኛል፡፡

ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ አንድ የዲላ ዩኒቨርሲቲ መምህር የቦምብ ጥቃቱ ከኦሮሚያ ክልል ከተነሳው ተቃውሞ ጋር ስለመያያዙ እርግጠኛ ባይሆኑም፣ ፍንዳታው የተከሰተው ግን ባለፈው ወር ተቃውሞ አነሳስታችኋል ተብለው ከታሰሩና በኋላም ከዩኒቨርሲቲው የስንብት ደብዳቤ ለተማሪዎቹ በተሰጣቸው ማግስት መሆኑን ለሪፖርተር ጠቁመዋል፡፡

የክልሉም ፖሊስ ኮሚሽነሩም ሆኑ ምንጮች እንዳረጋገጡት፣ ከታኅሳስ 26 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ ተማሪዎች ግቢውን በመልቀቅ ወደየትውልድ ቦታቸው በመሄድ ላይ ናቸው፡፡ ሪፖርተር ማረጋገጥ እንደቻለው ተማሪዎች የአንደኛ ዓመት ፈተና ለመውሰድ ሁለት ሳምንት ብቻ ሲቀራቸው ነው ከዩኒቨርሲቲው የወጡት፡፡ ነገር ግን የተማሪዎች መውጣት ጊዜያዊ ይሁን አይሁን ከዲላ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ለማወቅ ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡

የተማሪዎቹን መልቀቅ ተከትሎ በዲላ ከተማ ከፍተኛ የትራንስፖርት እጥረት መከሰቱንና በተማሪዎቹና በመምህራኖች ላይ ከፍተኛ መጉላላት መከሰቱን ከምንጮች ለማወቅ ተችሏል፡፡ አንዳንድ ምንጮች እንደገለጹልን፣ ወትሮ ከዲላ እስከ ሐዋሳ ከተማ 40 ብር የነበረው የትራንስፖርት ታሪፍ እስከ 320 ብር ድረስ ተጠይቆበታል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...