Monday, October 3, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ሥነ ፍጥረትአዲስ የአሳ ነባሪ ዝርያ ተገኘ

  አዲስ የአሳ ነባሪ ዝርያ ተገኘ

  ቀን:

  ሳይንቲስቶች በጨለማ የሚያበራ አዲስ የአሳ ነባሪ ዝርያ ማግኘታቸውን ገለጹ፡፡ ዋሽንግተን ፖስት እንደዘገበው፣ አዲስ ተገኘ የተባለው ዝርያ የሚያብረቀርቅና ባለጥቁር ቀለም ሲሆን፣ ይህም ከዚህ በፊት በግራጫነታቸው ወይም በቡናማ ቀለማቸው ከሚታወቁት የአሳ ነባሪ ዝርያዎች ለየት ያደርገዋል፡፡

  አዲስ የተገኘው አሳ ነባሪ፣ ኢትሞፒትረስ ቤንችሊ የተባለ ሳይንሳዊ ስም የተሰጠው ሲሆን በቅፅል ስሙ ኒንጃ ላንተርንሻርክ በመባል ይጠራል፡፡

  በካሊፎርኒያ የሚገኘው የፓስፊክ ሻርክ ምርምር ማዕከል ሳይንቲስቶች፣ አዲሱን አሳ ነባሪ ያገኙት የተለያዩና ዓለም ብዙም ያላወቃቸው የባህር ዝርያዎች ይገኙበታል ተብሎ በሚገመተው በመካከለኛው አሜሪካ ፓስፊክ ዳርቻ ነው፡፡

  ላይቭ ሳይንስ እንደሚለው፣ ከዚህ ቀደም በጨለማ የሚያበሩ የአሳ ነባሪ ዝርያዎች አሉ ቢባልም፣ ኒንጃ የሚል ቅፅል ስም እንደተሰጠው በጨለማ ሲያበሩ አልተስተዋሉም፡፡ ኒንጃ ግን በጨለማ የሚያበራ መሆኑ በማስረጃ ተረጋግጧል፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img