Sunday, September 24, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅየገና ዋዜማ በጎዳና

የገና ዋዜማ በጎዳና

ቀን:

እሳተ ገሞራው

መለየት ቢደብብ

መራራቅ ቢያረብብ

      ትናንትና ጠፍቶ በቀደም ቢረሳ

      ዕድሜ ዕድሜው ቢረዝም ቆዳ ቢወረዛ

            የነደደ ቋያ ዘመን የሸፈነው

            የተደፈነ ፍም ጊዜ አመድ የኳለው

            ልብ ወለል ላይ ድሮ መሠረት የጣለው

            ውስጡን አመርቅዞ አይቀር መፈንዳቱ

            በቀደምን አምናን ማብሰሩ መርዳቱ

      መውደድ ኖሮ ኖሮ

      ፍቅር ኖሮ ኖሮ

      ነፍሮ ነፍሮ ግሞ

            አቂሞ ለግሞ

      አይተው የልጅነት

      አይለቅ የለጋነት

                  ይፈነዳል ከርሞ፡፡

  • ተፈሪ ዓለሙ፣ የካፊያ ምች፣ 2007
  •  

ዋጋ ስጥ

እውነተኛ ማንነትህን ማወቅ፣ እውነተኛ ፀጋህን በማወቅ መከተል አለበት፡፡ ከብቃቶች ሁሉ የላቀችዬቱ ብቃት፣ ብቃትን የማወቅ ብቃት ነች፤ ይላሉ ጠቢባን፡፡ ይህ የሌሎችን ብቃት ስለማወቅ ብቻ ሳይሆን፣ የገዛ ራስህንም ብቃት ስለማወቅ የተባለ እውነት ነው፡፡ ቀላል ላይሆን ይችላል፤ ግን፣ እውነተኛ ኃይልህና ፀጋህ እምንህ ላይ እንደሁ ለማወቅ አይሳንህም፡፡

በመሆን ጎዳና ላይ፣ ብዙ ተጓዦች፣ ነፍሳቸውን ወይም መንፈሳቸውንና ኃይሏን እውነተኛ ማንነታቸውና ኃይላቸው እንደሆኑ ያምናሉ፡፡ ነፍስ ወይም መንፈስ በምንለው የቃል ዣንጥላ ውስጥ የትየለሌ ልዩ ፀጋዎች ታምቀዋል፡፡ ይህ በሰው መንፈስ ውስጥ ብቻም አይደለም፤ በባህልና በተፈጥሮ መንፈስም ውስጥ እንጂ፡፡

አንተ ፈጣሪ በሰም ያሸገህ ህቡዕ መጽሐፍ ነህ፡፡ በነፍስህ ግምጃ ቤት ውስጥ የተቀመጡቱ ሚስጥራት ሊገለጡ የሚችሉት ባንተ ብቻ ነው፡፡ በባህልህ ካዝና ውስጥ የተቆለፈባቸው የጥበብ ዕንቁዎች ተከፍተው ሊወጡ የሚችሉት ባንተ ብቻ ነው፡፡

ሁለንተና አብዝቶ ይወድሃልና፣ ያንተን በገዛ ራስ መንቃት አብዝቶ ያፈቅራልና፣ ከቶም ሊያስገድድህ አይሻም፡፡ በፈቃድህ ጉበን ላይ እሚያሻህን እገዛ ሊሰጥህ ብቻ ይጠብቃል፡፡

ላለህና እቅርብህ ለሆነው ዕውቅናና ዋጋ ስጥ፡፡ እጓሮአቸው ፍጹም ንፁህ ሉል እያለላቸው፣ ከአድማስ ባሻገር ድብቅ ፀጋ ፍለጋ ከሚማስኑትን አትሁን፡፡ ሁዋላ፣ ለውድቀትህ የሆነን ነገር መኮነን ካለብህ፣ እጦትህን ሳይሆን፣ ማየት አለመቻልህን ኮንን፡፡ አንተ ግን፣ ከኮናኞች ወገን አይደለህም፡፡

  • ኦ’ታም ፑልቶ፣ የፈላሱ መንገድ፣ 2006
  •  

 

ያገኘውን ነገር የሚመገበው ውሻ ቀዶ ሕክምና ተደረገለት

አሜሪካ ፊላዴልፊያ ውስጥ ያገኘውን ነገር ሁሉ የሚመገበው ውሻ ቀዶ ሕክምና እንደተደረገለት አሶሺየትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡ ቀዶ ሕክምናው በተደረገበት ሲቪትታውን ማዕከል የሚገኙ የእንስሳት ሐኪሞች እንደገለጹት፣ የስድስት ወር ዕድሜ ያለው ጃስፐር፣ ሙሉ በመሉ ጤናማ ሲሆን፣ ችግሩ ያገኘውን ነገር ሁሉ የመመገብ ነው፡፡ ውሻው በተደረገለት ቀዶ ሕክምና ከሆዱ የወጣለት ሁለት ኳስ ሲሆን፣ ዶ/ር ስኮት ጃውድሪ ‹‹ውሻው ያልሆኑ ነገሮችን ይመገባል›› ብለዋል፡፡ እዚያው አካባቢ ባለፈው ዓመትም ኳሶችን ጨምሮ ሌሎች ተመሳሳይ ነገሮችን ለተመገበ ውሻ ቀዶ ሕክምና ተደርጓል፡፡ የዚህ ውሻ (ጃስፐር) አሳዳሪዎች ውሻቸው ሁለቱን ኳሶች የበላው ከሳምንትት በፊት ሳይሆን እንዳልቀረ ተናግረዋል፡፡

  •  

በፍቺ ሒደት እያለች የ2.3 ሚሊዮን ሎተሪ ያሸነፈች በፍርድ ቤት ፀደቀላት

ጥንዶቹ ለመፋታት ማቀዳቸውን ፍርድ ቤት ያሳወቁት እ.ኤ.አ. ጥቅምት 2014 ላይ ነበር፡፡ ሆኖም እስከ ሰኔ 2015 መደበኛ የሆነ ይሁንታን ከፍርድ ቤቱ አላገኙም፡፡ ሮይተርስ እንደዘገበው፣ ጥንዶቹ በፍቺ ሒደት ላይ እያሉ ሚስቲቱ ለ2015 አዲስ ዓመት የሚወጣ ሎተሪ ትገዛለች፡፡ ዕድሏም የ2.3 ሚሊዮን ዶላር ባለቤት ያደርጋታል፡፡ በፍቺ ሒደት ላይ ያለ ባል ግን፣ ከሎተሪው መካፈል አለብኝ ሲል ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ ይቀርባል፡፡

በጋብቻ በቆዩባቸው 30 ዓመታት ከሁለቱም አካውንት ገንዘብ በማውጣት ሎተሪ የመግዛት ልምድ እንደነበራትም ያክላል፡፡ ፍርድ ቤቱ ከሳምንት በፊት በዋለው ችሎት፣ ጥንዶቹ የፍቺ ደብዳቤያቸውን በ2014 ለፍርድ ቤቱ ሲያቀርቡ፣ የንብረት ክፍፍል ዝርዝር ያቀረቡ መሆናቸውን፣ በዝርዝሩ ሎተሪው አለመካተቱንና ሎተሪው የተገዛው የፍቺ ጥያቄ ካቀረቡ በኋላ መሆኑን በማየት፣ በሎተሪ ዕድል ያገኘችውን 2.3 ሚሊዮን ብር እንድትወስድ ለሴቷ ወስኖላታል፡፡

  •  

በ20 ሚሊዮን ፓውንድ በረዶ የተገነባው ህድሞ

የኤድመንተን የበረዶ ህድሞ (Castle) 20 ሚሊዮን ፓውንድ በረዶ ፈጅቷል፡፡ በኤድመንተን አልበርታ የሚገኘውና ለከተማዋ የመጀመሪያ የሆነው ከበረዶ የተሠራ መስህብ፣  ለጎብኚዎች ክፍት የሆነው ከሳምንት በፊት ነው፡፡ ዩፒአይ እንደዘገበው፣ መስህቡ በተከፈተበት የመጀመሪያው ቀን አራት ሺሕ ሰዎች ስፍራውን ለማየት ትኬት ቆርጠው ነበር፡፡

በረዶው ብርሃን በተላበሰ ሊድ የተለበጠ ሲሆን፣ ምሽት ላይ ስፍራው በብርሃን እንዲሞላ ያደርጋል፡፡ ከዚህ ቀደም ዋሻዎችንና የዋሻ አናቶችን በበረዶ የማስዋብ ጥበብ በሚኒያሶታና ኒውሃምሸር የተተገበረ ቢሆንም፣ 20 ሚሊዮን ፓውንድ በረዶ የፈጀውና ከሁለት ሔክታር መሬት በላይ የሚሸፍነውን ዓይነት ህድሞ ተሠርቶ አያውቅም፡፡ ለካናዳም በዓይነቱና በመጠኑ የመጀመሪያው ነው ተብሏል፡፡

  •  

በድመቶች እጥረት ምክንያት ለጥቂት ጊዜያት የተዘጋ ካፌ

በካናዳ የሚገኘው የድመት ካፌ (ካት ካፌ) በድመት እጥረት ምክንያት ለአንድ ሳምንት ያልህ ተዘጋ፡፡ ሲቢሲ እንደዘገበው፣ የሬስቴራንቱ ባለቤት ሜቼሌ ፈርባቸር፣ ሬስቶራንቱን ለአንድ ሳምንት ያህል ለመዝጋት የተገደዱት፣ ፍላጐቱ ላላቸው የሬስቶራንቱ ተስተናጋጆች በማደጐ የሚሰጧቸው ድመቶች ቁጥር ስለተመናመነ ነው፡፡ ድመት በማየት የሚዝናኑ ደምበኞቻቸውም የዓይን ማረፊያ ስለሌላቸው ሬስቶራንቱን ለመዝጋት ተገደዋል፡፡

ከስምንት እስከ 12 ድመቶች በካፌው መኖር አለባቸው፡፡ ቁጥሩ ማደጐ የሚወስዱና ድመት ወደ ካፌው በመጣ ቁጥር የሚለያይ ቢሆንም፣ ቁጥሩ ከስምንት ማነስ የለበትም ሲሉም የካፌው ባለቤት ተናግረዋል፡፡

  •  

የወይራ ፍሬ በመልቀም ላይ የነበሩ ወይዘሮ በአዳኝ ጥይት ተመቱ

ሴትየዋ ከወይራ እርሻቸው ገብተው፣ የወይራ ፍሬ እይለቀሙ ነው፡፡ የ65 ዓመቱ አዛውንት ደግሞ መሣሪያቸውን አንግበው ለአደን ወጥተዋል፡፡ ጥቅጥቅ ካለው የወይራ ዛፍ ውስጥ እንቅስቃሴ በመመልከታቸው አፈሙዛቸውን እንቅስቃሴ ወዳለበት አቅጣጫ ያዞራሉ፡፡ ከዚያም ቃታቸውን ስበው በሁለት ጥይት ዛፍ ላይ የተንጠለጠሉትን ወይዘሮ ያወርዷቸዋል፡፡

ዴይሊ ስታር እንደዘገበው፣ አዳኙ ሴትየዋን በጥይት የመቱት ወፍ መስሏቸው ነው፡፡ ‹‹ዛፍ ላይ ወፍ ያየሁ መስሎኝ ተኮስኩኝ፡፡ ወዲያውም የሲቃ ድምፅ ተሰማኝ›› ብለዋል፡፡ አዳኙ በቁጥጥር ሥር ሲውሉ፣ በሁለት ጥይት የተመቱት ወይዘሮ የሕክምና ዕርዳታ ተደርጐላቸው ተርፈዋል፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የቤት ባለንብረቶች የሚከፍሉትን ዓመታዊ የንብረት ታክስ የሚተምን ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ

በአዋጁ መሥፈርት መሠረት የክልልና የከተማ አስተዳደሮች የንብረት ታክስ መጠን...

እንደ ንብረት ታክስ ያሉ ወጪን የሚያስከትሉ አዋጆች ከማኅበረሰብ ጋር ምክክርን ይሻሉ!

የመንግሥትን ገቢ በማሳደግ ረገድ አስተዋጽኦ እንዳላቸው የሚታመኑት የተጨማሪ እሴት...

ለዓለምም ለኢትዮጵያም ሰላም እንታገል

በበቀለ ሹሜ ያለፉት ሁለት የዓለም ጦርነቶች በአያሌው የኃያል ነን ባይ...