Tuesday, April 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

የጡሩሲናው ረከቦትና ሲኒዎች

ትኩስ ፅሁፎች

የጡሩሲና መስጊድ በደቡብ ወሎ በዳዋ ጨፋ ወረዳ በከሚሴና በወለዲ ከተሞች መካከል ሸከላ ተብላ በምትጠራ ትንሽ የገጠር ከተማ የሚገኝ ነው፡፡  በመስጊዱ ለኅብረተሰቡ የሚቀርበው ቡና የሚዘጋጅበት ክፍል ውስጥ ርዝመቱ ወደ 2 ሜትር የሚሆን ረከቦት፣ ከ150 የሚበልጡ ሲኒዎች ያሉ ሲሆን፤ ረከቦቱ በአንድ ጊዜ 190 ሲኒዎችን መደርደር የሚችል ነው፡፡ ጀበናዎቹ ደግሞ የእንስራ መጠን ያላቸው ከብረትና ከሸክላ የተሠሩ ናቸው፡፡ (የኢትዮጵያ ፌስቲቫል ማውጫ- ሀገሬ ሚዲያ ኮሙኒኬሽን)

**************

ንሳ ውሰድ ልቤን

ንሳ ውሰድ ልቤን አስገባው በጅህ

እጅህን አለስልስ ግን ተጠንቅቀህ

ያ የኔ ቀይ ልብ – ላንተ ሲሰጥህ፡፡

በርጋታ ይመታል፣ ፀጥታውም ደርቷል

ፍቅር ቀምሷልና ሥቃይን ያውቃታል

ዛሬማ ፀጥ አለ – ዛሬ ያንተ ሆኗል፡፡

ሊቆስል ይችላል፣ ሊጠወልግም

ወትሮም ይረሳ፤ ያውቃል ማዘንጋትም፤

ግን ያንተ መሆኑን ፈጽሞ አይረሳትም፡፡

ልቤም ጠነከረ ተሰማው ኩራት፤

ተኝቶም አለመ፤ ፈክቶ ሲጫወት

አሁንም ይችላል ሊፈነካከት – ይህን የምትችል

ግን እጅህ ብቻ ናት፡፡

ከቶቭ ዳትሊውስን /ስድ ትርጉም በከበደ ዳግማዊ

**********************

ባለሁለት እግሯ ውሻ መስህብ ሆነች

በፔሩ ቲንጋ ማሪያ በተባለ ከተማ ውስጥ አበዳሪዎች ጐዳና ላይ የጣሉት ባለ ሁለት እግር ውሻ የከተሜውን ዓይን መሳቧን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ የአንድ ዓመት ከስድስት ወር ዕድሜ ያላት ትንሿ ውሻ አስተሬላ በከተማው የእንስሳት መጠለያ በሚያስተዳድሩ ጥንዶች ተወስዳ በጥሩ ሁኔታ ላይ ትገኛለች፡፡ በጥሩ ሁኔታ መገኘትም በላይ እንደባሪያዋ ሳይሆን እንደ ካንጋሮ የምትንቀሳቀሰው አስተሬላ የጐብኚዎችን ቀልብ ስባለች፡፡ ስለዚህም ብዙ ጐብኚዎች ወደመጠለያው በመሔድ አሳዳሪዎቿ ለመሆን ፍላጐት እያሳዩ ነው፡፡ የመጠለያው አስተዳዳሪ ኢቫን ኢስካቫር ውሻዋን ሲያገኟት ገና የስድስት ወር እንደነበረች ‹‹ለመራመድ ይሞክር እንደነበር ሕፃን ነበረች›› በማለት ይገልጻሉ፡፡

**************

15 ጥንዶች በረዶ ላይ ተሞሸሩ

ከቻይና ከተሞች ቀዝቃዛማ በሆነችው ሀርቢን ከተማ ባለፈው ሳምንት 15 ጥንዶች ሙቀቱ ከ20 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች በሆነበት ሁኔታ ውስጥ ጋብቻቸውን የፈፀሙት ዓለም አቀፉ የበረዳ ፌስቲቫል እየተካሄደ ባለበት ጊዜ ነው፡፡ ጥንዶቹ ምንም እንኳ የደንብ የሙሽራ ልብሶቻቸውን ለብሰው የነበረ ቢሆንም ቅዝቃዜው ትልልቅ ካፖርቶች እንዲደርቡ የበረዶ ጫማ እንዲጫሙም የግድ ብሎ ነበር፡፡   

******

እንቆቅልሾቹ

በአንድ ወቅት አንድ ድሃ ሰው ነበረ፡፡ ሰውየውም ወንድ ልጁ የአንድ ሃብታም ሰው ሴት ልጅ እንዲያገባ ፈልጎ ጋብቻውን ይጠይቃል፡፡ ሃብታሙም ሰው የሰውየውን ድህነት አይቶ ከለከለው፡፡ እንዲህ እያለም ይፈትነው ጀመር፡፡

“እንቆቅልሾችን መፍታት ትችላለህ?” ሲለው ሰውየውም “አዎ፣ እችላለሁ፡፡” አለ፡፡

ሃብታሙም ሰው “እንግዲያው ሶስት እንቆቅልሾችን አሰጥሃለሁ፡፡ መልሶቹን እስከ ነገ ድረስ እንድታመጣ፡፡” ብሎ የሚከተሉትን ሶስት እንቆቅልሾች ጠየቀው፤

“አንድ ገበሬ ሶስት ላሞች ሲኖሩት አንደኛዋ ላም የምትታለበው በተለመደው ሁኔታ ቆማ ሲሆን ሁለተኛዋ ላም ግን ተንበርክካ ነው የምትታለበው፡፡ ሶስተኛዋ ላም ደግሞ የምትታለበው ተቀምጣ ነው፡፡ ይህ ምን ማለት ነው?”

ሰውየው ይህንን መመለስ አልቻለም፡፡

“እስኪ ሚስቴን ልጠይቃት፡፡” ሲል ሃብታሙም ሰው “እሺ ሄደህ ጠይቃት፡፡” አለው፡፡

ሆኖም ሚስቱም አልቻለችም፡፡ በዚህ ጊዜ ሃብታሙ ሰው “ሄደህ ለሶስትና ለአራት ቀናት ጠይቀህ ለመምጣት ሞክር፡፡” ብሎ በቀጠሮ ሲልከው ወዲያው አንዲት የኔቢጤ ሴት መጥታ “ስለእግዚአብሔር፣ እባካችሁ የምበላው ነገር ስጡኝ፡፡” እያለች መለመን ጀመረች፡፡

ድሃውም ሰው “ለአንቺ ምግብ የምንሰጥበት ጊዜ የለንምና እባክሽ ሂጂልን፡፡ የሃብታሙን ሰው እንቆቅልሽ ለመፍታት እየሞከርን ነውና ሂጂልን፡፡” አላት፡፡

የኔቢጢዋም ሴትዮ “እንቆቅልሹን ልትነግሩኝ ትችላላችሁ?” ስትላቸው እነርሱም “አንቺ ምስኪንና የምትበይው እንኳን የሌለሽ ድሃ የኔቢጤ ነሽና እንቆቅልሹን እንዴት ልትፈቺ ትችያለሽ?” አሏት፡፡

እርሷም “ግዴለም እመኑኝና ልስማው፡፡” ብላ ተማፀነች፡፡ ሰውየውም ነገራት፡፡

እርሷም “ይህማ ቀላል ነው፡፡ የመጀመሪያው፣ ላሟ የሃብታም ሰው ንብረት ናት፡፡ ድሃ ሰው የሃብታሙን ሰው ላም ወደ ግጦሽ፣ ወደ ውሃና ወደመሳሰሉት ነገር እየወሰደ ይጠብቃታል፡፡ ስትወልድም በማዋለድ ለሰራው ስራ የላሟን ወተት ለልጆቹ ይወስዳል፡፡ ታዲያ ይህ ሰው አንድ ቀን ሃብታሙ ሰው መጥቶ ላሟን ይወስዳታል ብሎ ሁልጊዜ ይሰጋል፡፡ ስለዚህ ነው ሃብታሙ ሰው ሳይወስዳት በችኮላ በቆመችበት የሚያልባት፡፡ ሁለተኛው ሰው ደግሞ በከፊል እምነት ያለው ነው፡፡ ሃብታሙ ሰው ላሟን ሊወስዳትም ላይወስዳትም ይችላል፡፡ ምክንያቱም ላሟ የጋራ ንብረታቸው ናት፡፡ ላሟን በጋራ ነው የገዟት፡፡ ሶስተኛው ሰው ላሟ ተቀምጣ የሚያልባት ላሟ የራሱ ንብረት ስለሆነች ማንም ሰው መጥቶ አይወስዳትምና ተረጋግቶ በሰላም ያልባታል፡፡” በማለት የእኔ ቢጤዋ ሴት ነገረችው፡፡

ሆኖም ድሃው ሰው መልሱን ራሱ የማያውቀው መሆኑን ለሃብታሙ ሰው ነግሮት ስለነበረ የእኔ ቢጤዋን ሴት ወደ ሃብታሙ ሰው ዘንድ ይዟት ሄዶ መልሱን እርሷ እንደነገረችው ነገረው፡፡ ሃብታሙም ሰው “ወንድ ልጅ አለሽ?” ብሎ ጠየቃት፡፡ እርሷም “አዎ” አለችው፡፡

እርሱም “ልጄን ለልጅሽ ነው የምሰጠው፡፡” ብሏት የእኔ ቢጤዋ ሴት የሃብታም ሰው ቤተሰብ ሆነች፡፡

  • በካፒቴን ደጀኔ ዋሻካ የተተረከ የጉራጌ ተረት

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች