Friday, September 22, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናለኔዘርላንድ ኩባንያ የተሰጠውን የጤፍ የባለቤትነት መብት ለማሰረዝ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ክስ እንዲመሠርት...

ለኔዘርላንድ ኩባንያ የተሰጠውን የጤፍ የባለቤትነት መብት ለማሰረዝ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ክስ እንዲመሠርት ተወሰነ

ቀን:

የኢትዮጵያን የባለቤትነት መብት በመጣስ ለኔዘርላንድ ኩባንያ የተሰጠውን የጤፍ አዘገጃጀት ፓተንት (መብት) ለማሰረዝ ሲደረግ የቆየው ድርድርና ውይይት ባለመሳካቱ፣ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ መደበኛ ክስ እንዲመሠረት መወሰኑን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር ኢንጂነር) ግንቦት 7 ቀን 2010 ዓ.ም. ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዘጠኝ ወራት ሪፖርት ሲያቀርቡ፣ በአምስት የአውሮፓ አገሮች ለኔዘርላንድ ኩባንያ በጤፍ ዱቄት አዘገጃጀት የተሰጠውን የባለቤትነት መብት ለማሰረዝ ብዙ ጥረትና አድካሚ ውይይቶች ቢደረጉም ምንም ውጤት ሊገኝ አለመቻሉን ገልጸዋል፡፡

‹‹በተለይም ባለፉት ዘጠኝ ወራት ሰፊ ሥራዎች ከተሠሩ በኋላ አገራችን በጤፍ መስክ ያጣችውን መብት ለማስመለስ፣ ወደ ፍትሕ አካላት መሄድ ብቸኛው መፍትሔ መሆኑን ታምኖበታል፤›› ሲሉ ለምክር ቤቱ አስረድተዋል፡፡

‹‹ወደ ፍትሕ አካላት መሄድን ሚኒስቴር መሥሪያ ቤታችን በፅኑ በማመኑ ክስ እንዲመሠረት ለጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ጥያቄና ሰነዶችን ያቀረበ መሆኑን ምክር ቤቱ እንዲያውቅልን እወዳለሁ፤›› ሲሉ ሚኒስትሩ  አስረድተዋል፡፡

ከጤፍ ዝርያና አዘገጃጀት ጋር በተለይም ለሚኒስትሩ ተጠሪ በሆነው የኢትዮጵያ አዕምሮአዊ ንብረት ጽሕፈት ቤት አማካይነት፣ ሄልዝ ኤንድ ፕርፎርማንስ ኢንተርናሽናል ከተባለው ኩባንያ ጋር ሲወዛገብ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በጣሊያን፣ በእንግሊዝ፣ በጀርመን፣ በኦስትሪያና በኔዘርላንድ የተሰጠውን የባለቤትነት መብት ለማሰረዝ በቀጥታ ድርድርና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ጥረት ሲደረግ መቆየቱን፣ የአዕምሮአዊ ንብረት ጽሕፈት ቤት ሲገልጽ ነበር፡፡

ይህ ጉዳይም በፓርላማም በተደጋጋሚ ጥያቄ ሲያስነሳ እንደነበር፣ መንግሥት የባለቤትነት መብቱን እንዲያስመልስ ግፊት ሲደረግ መቆየቱ በመደበኛ ስብሰባው ወቅት ተጠቅሷል፡፡

ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የተባለውን ክስ መቼ እንደሚጀምርና በየትኛው ዓለም አቀፍ የፍትሕ ተቋም የክስ መዝገብ እንደሚከፍት ባይገለጽም፣ ክሱ በአጭር ጊዜ እንደሚጀመር ተጠቁሟል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ሪፖርት ምን ይዟል?

ለአሜሪካ ድምፅ አማርኛ ዝግጅት የስልክ አስተያየት የሰጡ አንድ የደንበጫ...

መንግሥት በአማራ ክልል ለወደሙ የአበባ እርሻዎች ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት በቢዝነስ...

አምናና ዘንድሮ!

እነሆ መስከረም ጠብቶ በአዲስ መንፈስ ተሞልተን መንገድ ጀምረናል። ‹‹አዲስ...