Wednesday, February 28, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየብረት አምራቾች ማኅበር ለዘርፉ በልዩ ሁኔታ የውጭ ምንዛሪ እንዲቀርብ ጠየቀ

የብረት አምራቾች ማኅበር ለዘርፉ በልዩ ሁኔታ የውጭ ምንዛሪ እንዲቀርብ ጠየቀ

ቀን:

በውጭ ምንዛሪ እጥረትና አመዳደብ ችግር ምክንያት አገር በቀል የብረት ፋብሪካዎች የመዘጋት አደጋ እንደተጋረጠባቸው፣ የኢትዮጵያ መሠረታዊ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪዎች ማኅበር አስታወቀ፡፡ ማኅበሩ ግንቦት 3 ቀን 2010 ዓ.ም. ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በጻፈው ደብዳቤ፣ ለአገር በቀል ብረት አምራቾች በአጭር ጊዜ ውስጥ በልዩ ሁኔታ የውጭ ምንዛሪ እንዲቀርብ ጠይቋል፡፡

‹‹አገር በቀል ብረት አምራቾች በሙሉ ወይም ከግማሽ በላይ የማምረት አቅማቸው ሊያመርቱ የሚያስችላቸውን ጥሬ ዕቃ እንዲያገኙ በልዩ ሁኔታ የውጭ ምንዛሪ እንዲቀርብ፣ ከዚህ በኋላም በቋሚነት በየወሩ የውጭ ምንዛሪ ሊቀርብ ይገባል፤›› በማለት ጥያቄውን ያቀረበው ማኅበሩ፣ ‹‹ይህ የማይደረግ ከሆነ አገር በቀል ኢንዱስትሪዎችን ከውድድር ውጪ እንደሚያደርግ፣ እነዚህ ግዙፍ ብረት አምራቾች ከጨዋታ ውጪ በሚሆኑበት ጊዜ ተያያዥ የሆነው የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪና አነስተኛና መለስተኛ ብረታ ብረት አምራቾችም አደጋ ውስጥ ይገባሉ፤›› በማለት ማኅበሩ ከወዲሁ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በጻፈው ደብዳቤ አስጠንቅቋል፡፡

በኢትዮጵያ የሚገኙ አምራቾች በአጠቃላይ የማምረት ዓመታዊ አቅማቸው ከአምስት ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን በላይ ነው፡፡ ነገር ግን በጥሬ ዕቃ አቅርቦት ችግር ምክንያት እያመረቱ የሚገኙት ከአቅማቸው በታች ከአሥር እስከ 20 በመቶ ድረስ ብቻ መሆኑ ተገልጿል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ማኅበሩ ለብረት ዘርፍ የሚቀርበው የውጭ ምንዛሪ ፍትሐዊ አይደለም ብሏል፡፡ በዚህም ሳቢያ አንዳንዶች የኢንዱስትሪዎች ጥሬ ዕቃዎችን የሚሸምቱበት የውጭ ምንዛሪ በማጣት ፋብሪካቸውን በመዝጋታቸው፣ የባንክ ዕዳ መክፈል የማይችሉበት ደረጃ እየተፈጠረ ባንኮችም ሆኑ ኢንዱስትሪዎቹ ከፍተኛ አደጋ ውስጥ መግባታቸውን ማኅበሩ በደብዳቤው አሳውቋል፡፡

‹‹የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት ፍትሐዊ ካለመሆኑም በላይ ኢንዱስትሪዎቹ ጥሬ ዕቃ አጥተው ሠራተኞቻቸውን እየበተኑ ባሉበት በዚህ ወቅት፣ ያለቀለት ብረት ከውጭ በገፍ እየገባ ነው፡፡ የኢትዮጵያ 85 በመቶ ገቢና ወጪ ንግድ በሚያስተናግደው ጂቡቲ ወደብ ተከማችቶ የሚኘው ጥሬ ዕቃ ሳይሆን ያለቀለት ብረት ነው፤›› በማለት የገለጸው ማኅበሩ፣ ‹‹በግሉ ዘርፍ ያለቀለት ብረት ለማስመጣት የሚውለው የውጭ ምንዛሪ ላይ ከፍተኛ ቁጥጥርና ክትትል በማድረግ፣ በአሥር ሺሕ የሚቆጠር የዘርፉ ተዋናዮችን ኑሮ መታደግ ያስፈልጋል፤›› በማለት ማኅበሩ ብሔራዊ ባንክን አሳስቧል፡፡

ማኅበሩ በዚሁ ደብዳቤ ላይ ጨምሮ እንደገለጸው፣ ብሔራዊ ባንክ ከወራት በፊት ዜግነትን መሠረት አድርጎ ያወጣው የአቅራቢዎች ብድር (ሰፕላየርስ ክሬዲት)፣ አገር በቀል የሆኑና በኢትዮጵያውያን ባለሀብቶች ብቻ የተመሠረቱ ኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም በማዳከም፣ ከገበያ ውድድር ውጪ የሚያደርግ በመሆኑ መመርያው ሊስተካከል ይገባል ብሏል፡፡

የኢትዮጵያ መሠረታዊ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ማኅበር ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን ሙሉጌታ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ‹‹ብሔራዊ ባንክ የውጭ አገር ዜጋ ባለሀብቶች ካልሆኑ በስተቀር ለኢትዮጵያውያን ባለሀብቶች እንዳይፈቀድ ያወጣው መመርያ፣ አገር በቀል የሆኑ ኢትዮጵያውያን ባለሀብቶችን በጣም ያሳዘነ ነው፡፡ ይህም የአገር ውስጥ ባለሀብቶች እንዳይስፋፉና በውጭ አገር ዜጎች ተፅዕኖ ሥር እንዲውሉ የሚያደርግ ስለሆነ ሊታረም ይገባዋል፡፡››

አቶ ሰለሞን ጨምረው እንደገለጹት፣ አገር በቀል አምራቾች አቅማቸው እስከቻለና የውጭ አቅርቦት እስካገኙ ድረስ፣ እንዲሁም የአገር ውስጥ ባንክ የሚከፍል መሆኑ ካልቀረ ይህ ክልከላ በአስቸኳይ ታርሞ ለአገር ውስጥ ባለሀብቶችም እንዲፈቀድላቸው፣ በተለይም ባንኩ አሠራሩን አስተካክሎ ለኢንዱስትሪዎች ጥሬ ዕቃ ማስመጫ ሊመድብ ይገባል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ግዥ አቶ ተክለ ወልድ አጥናፉ በማኅበሩ ቅሬታ ላይ አስተያየት እንዲሰጡ የተደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...