Monday, July 15, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትበወልዋሎ አዲግራት ክለብና መሪው ላይ የተጣለው ቅጣት ሲፀና የአራት ተጫዋቾች ቅጣት ተነሳ

በወልዋሎ አዲግራት ክለብና መሪው ላይ የተጣለው ቅጣት ሲፀና የአራት ተጫዋቾች ቅጣት ተነሳ

ቀን:

  • ተጨማሪ ቅጣትም ተላልፏል

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ፣ በወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ክለብ ላይ በዲስፕሊን ኮሚቴ ተጥሎ የነበረው ቅጣት ላይ ማሻሻያ አደረገ፡፡ የክለቡ የቡድን መሪ ቅጣት ሲፀና፣ በአንድ ተጫዋች ላይ ተጨማሪ ቅጣትን አስተላልፏል፡፡

ሚያዝያ 22 ቀን 2010 ዓ.ም. ከተደረጉ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከመካላከያ ጋር በአዲስ አበባ ስታዲየም ሳይጠናቀቅ የተቋረጠው ጨዋታ ይጠቀሳል፡፡ በወቅቱ ለጨዋታው መቋረጥ ምክንያት የነበረው ደግሞ የ84ኛው ደቂቃ መከላከያ ወልዋሎ ላይ ያስቆጠራት ግብ ‹‹ትክክለኛ ነው አይደለም›› በሚል የወልዋሎ ተጫዋቾችና የቡድን አባላት በጨዋታው ዋና ዳኛ ላይ ውክቢያና ድብደባ  በመሞከራቸውና በመፈጸማቸው መሆኑ አይዘነጋም፡፡

ጉዳዩን ሲያጣራ የቆየው የፌዴሬሽኑ ዲሲፕሊን ኮሚቴ፣ የወልዋሎ አዲግራት ክለብ የቡድን መሪ አቶ ማሩ ገብረፃዲቅ፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከሚያዘጋጃቸው ማንኛውም የእግር ኳስ እንቅስቃሴ ዕድሜ ልክ እንዲታገዱ፣ የገንዘብ ቅጣት ደግሞ 20 ሺሕ ብር እንዲከፍሉ ወስኗል፡፡ ክለቡ ደግሞ 250 ሺሕ ብር እና ስድስት ተጫዋቾች ለስድስት ወራት ከጨዋታ እንዲታገዱ፣ በተጨማሪም እያንዳንዳቸው 10 ሺሕ ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲከፍሉ፣ የክለቡ አንድ ተጫዋዋች ላይ ደግሞ ሁለት ዓመትና 15 ሺሕ ብር የገንዘብ ቅጣት ማስተላለፉን ይታወሳል፡፡

የወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ክለብ በበኩሉ፣ በፌዴሬሽኑ የዲስፕሊን ኮሚቴ የተላለፈበት የቅጣት ውሳኔ ተገቢ አለመሆኑን በመጥቀስ፣ ለፌዴሬሽኑ ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ቅሬታውን ማቅረቡ አይዘነጋም፡፡

የሕግ ባለሙያና ጠበቃ በሆኑት አቶ ጳውሎስ ተሰማ ሰብሳቢነት የሚመራው የፌዴሬሽኑ ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ በበኩሉ፣ በክለቡ ላይ የተላለፈውን የዲሲፕሊን ቅጣትና ክለቡ ያቀረበውን የይግባኝ አቤቱታ ከብሔራዊ ፌዴሬሽኑ መተዳደሪያ ደንብና የዲስፕሊን መመሪያ፣ እንዲሁም ከካፍና ፊፋ ሕጎች ጋር በማገናዘብ የውሳኔ ማሻሻያ ማድረጉን ይፋ አድርጓል፡፡

ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴው ግንቦት 14 ቀን ባስተላለፈው የቅጣት ማሻሻያ መሠረት፣ የወልዋሎ አዲግራት ክለብ የቡድን መሪ ከተጣለባቸው ኃላፊነት አንፃር በመሀል ዳኛ ኢያሱ ፈንቴ ላይ የፈፀሙት ድብደባ አግባብ ባለመሆኑ፣ ቀደም ሲል ከማናቸውም እግር ኳሳዊ እንቅስቃሴ የዕድሜ ልክ ዕገዳና የተጣለባቸው 20 ሺሕ ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲፀና ወስኗል፡፡ በክለቡ ላይ የተላለፈው 250 ሺሕ ብር በተመሳሳይ የፀና እንዲሆን መወሰኑን አስታውቋል፡፡

በክለቡ ተጨዋቾች ላይ የተላለፈውን ውሳኔ አስመልክቶ፣ በተለይም የክለቡ ግብ ጠባቂ የሆነው በረከት አማረ፣ የተቆጠረበትን ትክክለኛ ጎል በፀጋ ከመቀበል ይልቅ ኳስ ይዞ ወደ መሀል ዳኛው ሮጦ ለተፈጠረው ውዝግብ መንስኤ በመሆኑ፣ ቀደም ሲል የተጣለበት ስድስት ጨዋታና 10 ሺሕ ብር የገንዘብ ቅጣት ፀንቶበታል፡፡

ተጨማሪ የጨዋታና የገንዘብ ቅጣት የተላለፈበት የክለቡ ተጫዋች አሰር ማሃዲ ሲሆን፣ ተጫዋቹ ቀደም ሲል የተላለፈበትን የጨዋታና የገንዘብ ቅጣት፣ ከፈጸመው ጥፋት አንፃር ያነሰ በመሆኑ በፌዴሬሽኑ የዲስፕሊን መመሪያ አንቀጽ 66 ንዑስ አንቀጽ ሁለት መሠረት፣ ከጨዋታ ስደስት ወራት የሚለው ወደ አንድ ዓመት፣ እንዲሁም በገንዘብ 10 ሺሕ ብር የሚለው ደግሞ ወደ 20 ሺሕ ብር ከፍ እንዲል ወስኗል፡፡

በዳኞችና በጨዋታ ታዛቢ ዳኛ በቀረበበት ሪፖርት መሠረት፣ ከማንኛውም ጨዋታ ሁለት ዓመትና በገንዘብ 15ሺሕ ብር ቅጣት ተላልፎበት የነበረው ዋለልኝ ገብሬ፣ ሪፖርቱ ከጨዋታው የቪዲዮ ምስል ጋር የሚጣረስ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በመሆኑም ቅጣቱ አግባብነት የሌለው ስለሆነ፣ በፌዴሬሽኑ የዲሲፕሊን መመሪያ አንቀጽ 52(2)(ሀ) መሠረት፣ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያና 5 ሺሕ ብር የገንዘብ ቅጣት ተላልፎበታል፡፡ ቀሪዎቹ ዓለምነህ ግርማ፣ ማናዬ ፋንቱ፣ በረከት ተሰማና አፈወርቅ ኃይሉ የተባሉት የክለቡ ተጫዋቾች፣ ቀደም ሲል የተላለፈባቸው የጨዋታና የገንዘብ ቅጣት እንዲነሳላቸው ወስኗል፡፡ ነገር ግን ተጫዋቾቹ ዳግም እንዲህ ከመሰለ ድርጊት መታቀብ ይችሉ ዘንድ፣ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል ብሏል፡፡ ሌላው ክለቡ ላይ የተላለፈው በፎርፌ ተሸናፊ እንዲሆን የሚለው ውሳኔ የፀና እንዲሆን ስለመደረጉም  የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴው ውሳኔ አመልክቷል፡፡   

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሚዲያው በሕዝብ የህሊና ችሎት ከተዳኘ በቂ ነው!

መሰንበቻውን ድንገት ሳይታሰብ ያለ ማስጠንቀቂያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ...

የባህር በር ጉዳይ

በታምሩ ወንድም አገኘሁ ድሮ ድሮ ገና ልጅ ሆኜ ፊደል እንደቆጠርኩ...

አገሩ ፖለቲካዊ ስክነትና መደማማጥ ያስፈልገዋል

በንጉሥ ወዳጀነው    ኢትዮጵያ የሁላችንም የጋራ ቤት ነች፡፡ ‹‹ጥያቄዬ ተመለሰልኝ››፣...

የመንግሥት የሰብዓዊ መብት ተቋም ለምን የመንግሥት ሚዲያን ማስተማር አቃተው

በገነት ዓለሙ የአገራችን የ2016 የበጀት ዓመት መሰናበቻና የአዲሱ የ2017 በጀት...