Wednesday, July 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየፌዴሬሽኑ ዕጩ ፕሬዚዳንታዊና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዝርዝር ይፋ ሆነ

የፌዴሬሽኑ ዕጩ ፕሬዚዳንታዊና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዝርዝር ይፋ ሆነ

ቀን:

  • አዲስ አበባን ጨምሮ ሦስት ክልሎች ለፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ያቀረቧቸው ዕጩዎች ውድቅ ተደርገዋል

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሚያዝያ 27 ቀን 2010 ዓ.ም. በካፒታል ሆቴል በጠራው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ የተሰየመው የፌዴሬሽኑ አስመራጭ ኮሚቴ ግንቦት 26 ቀን በአፋር ሰመራ ለሚደረገው ፕሬዚዳንታዊና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ምርጫ የሚቀርቡ ዕጩዎችን ይፋ አድርጓል፡፡

አስመራጭ ኮሚቴው ግንቦት 14 ቀን ይፋ ባደረገው ዝርዝር መሠረት ከፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የአዲስ አበባ፣ የትግራይና የጋምቤላ እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች የወከሏቸው ኢንጂነር ፀደቀ ይሁኔ፣ አቶ ተስፋዬ ካህሳይና ኢንጂነር ቶል ቤል በተደረገው ማጣራት መሠረት ከዕጩነት ዝርዝር ውጪ ተደርገዋል፡፡

ግንቦት 14 ቀን ይፋ በተደረገው ዝርዝር መሠረት፣ ከድሬዳዋ አቶ ጁነዲን ባሻ፣ ከአማራ አቶ ተካ አስፋውና ከኦሮሚያ አቶ ኢሳያስ ጅራ ለዕጩ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫው ቀርበዋል፡፡ ለሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ምርጫ የታጩት አቶ አበበ ገላጋይ ከድሬዳዋ፣ አቶ ዮሴፍ ተስፋዬ ከአዲስ አበባ፣ አቶ አሊሚራህ መሐመድ ከአፋር፣ አቶ ዘሪሁን ቀቀቦ ከደቡብ፣ አቶ ሰውነት ቢሻው ከአማራ፣ አቶ አብድራዛቅ ሐሰን ከሶማሌ፣ አቶ ከማል ሁሴን ከኦሮሚያ፣ አቶ አሥራት ኃይሌ ከአዲስ አበባ፣ ኮሎኔል አወል አብዱራሂም ከትግራይ፣ ዶ/ር ሲራክ ሀብተማርያም ከአማራ፣ አቶ ወንድአወክ አበዜ ከድሬዳዋ፣ አቶ ኡቻላ ኡጅሉ ከጋምቤላ፣ ወ/ሮ ሶፍያ አልማውን ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ አቶ ኢብራሂም መሐመድ ከሐረሪ፣ አቶ ወልደ ገብርኤል መዝገቡ ከትግራይ፣ ኢንጂነር ኃይለየሱስ ፍሥሐ ከአዲስ አበባ፣ አቶ ሙራድ አብዲ ከሐረሪ፣ አቶ ተስፋዬ ኦሜጋ ከአዲስ አበባ፣ ዶ/ር ቻን ጋትኮት ከጋምቤላ፣ ዶ/ር ወገኔ ዋልተንጉሥ ከድሬዳዋ፣ አቶ ዳግም መላሼ ከጋምቤላ፣ ዶ/ር ኃይሌ ኢቲቻ ከኦሮሚያ ናቸው፡፡

ለፕሬዚዳንታዊ ምርጫው ከዕጩነት ውጪ የሆኑት ሦስቱ ተወዳዳሪዎች፣ የትግራይ ክልል ያቀረባቸው አቶ ተስፋዬ ካሕሳይ ክልሉ ውክልናቸውን በማንሳቱ ከዝርዝሩ ውጪ ሆነዋል፡፡ ከአዲስ አበባ የተወከሉት ኢንጂነር ፀደቀ ይሁኔ ደግሞ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ቼዝ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሆነው እየመሩ በመሆናቸው፣ የፌዴሬሽኑን ኃላፊነት ደርበው ለመሥራት የፌዴሬሽኑ ደንብ አንቀጽ 21 ተራ ቁጥር አንድ መሠረት እንዲሁም የስፖርት ማኅበራት ስለሚያቋቁሙት ለመወሰን በወጣው መመሪያ አንቀጽ 35 ተራ ቁጥር ሁለት መሠረት አንድ ሰው በአንድ የአገልግሎት ዘመን በአባልነት የሚያገለግለው በአንድ የስፖርት ማኅበር ውስጥ ብቻ በሚለው ሕግ ከዕጩነታቸው እንዲሰረዙ መደረጉ ተገልጿል፡፡ የጋምቤላው ተወካይ ኢንጂነር ቾል ቢል ማስረጃቸው የቀረበው ቀነ ገደቡ ከተጠናቀቀ በኋላ በመሆኑ ተቀባይነት እንዳላገኘ ተነግሯል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ።...

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...

ግለሰብ ነጋዴዎችን በአስገዳጅነት የንግድ ምክር ቤት አባል ለማድረግ ያለመው ረቂቅ አዋጅ ተከለሰ

በምትኩ የንግድ ተቋማት በአስገዳጅነት የንግድ ምክር ቤት አባል ይሆናሉ...

አሳርና ተስፋ!

ከቱሉ ዲምቱ ወደ ቦሌ ጉዞ ልንጀምር ነው፡፡ ገና ከመንጋቱ...