Monday, June 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊጠቅላይ ሚኒስትሩ የደረሱለት ታዳጊ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የደረሱለት ታዳጊ

ቀን:

ከደቂቃዎች በፊት ሲቦርቅ ሲጫወት የነበረ ሕፃን ከአፍታ በኋላ እንደዋዛ መናገርም ሆነ መንቀሳቀስ የማይችልበት ከእርሶ የራቀ የዝምታ ዓለም ውስጥ ሆኖ ቢያገኙት ምናልባት ቅዠት ይሆን ብለው ሊያስቡ ይችላሉ፡፡ እውነታውን አምኖ መቀበል እንኳንስ ለወላጅ ለሌላም ከባድ ይሆናል፡፡ ችግሩ የተፈጠረው ደግሞ ብዙም አስጊ ያልነበረን ነገር ግን ምቾት የነሳውን የጤና እክል አክመው ያድኑታል ብለው ባመኑባቸው ሐኪሞች ሲሆን፣ ሐዘኑም ቁጭቱም ድርብ ይሆናል፡፡

ትውልዱ በመካከለኛው ምሥራቅ በሆነው ታዳጊ መሐመድ አብዱልአዚዝ ላይ በሕክምና ስህተት የደረሰበት አደጋም ከዚህ በምንም የተለየ አይደለም፡፡ ፍልቅልቁ ታዳጊ መሐመድ አፍንጫው ላይ በነበረበት ያልታወቀ ችግር ለመተንፈስ ይቸገር ነበር፡፡ የአራት ዓመት ልጅ ሳለም እናቱ / ሐሊማ ሙዘሚል በሳዑዲ ዓረቢያ ጅዳ ከተማ ወደሚገኘው የሱሌይማን ፋኬህ ሆስፒታል በአፍንጫው ውስጥ የበቀለውና ለመተንፈስ የሚያስቸግረው ሥጋ በቀላል ቀዶ ሕክምና እንዲወጣለት ወሰዱት፡፡

በአሥር ደቂቃ ቀዶ ሕክምና የልጃቸው ጤና እንደሚመለስ በማመን መሐመድን ለሐኪሞቹ አስረክበው ይጠባበቁ ጀመር፡፡ ነገር ግን ፈፅሞ ያልጠበቁት ነገር ተፈጠረ፡፡ መሐመድ እንኳንስ አተነፋፈሱ ሊስተካከል መናገርም ሆነ መስማት፣ መላወስ የህልም ያህል የራቀው የአልጋ ቁራኛ ሆኖ ነበር ያገኙት፡፡ ለአሥር ደቂቃ ሕክምና ተብሎ ከገባበት ክፍል ሲወጣ ራሱን አያውቅም ነበር፡፡ በሆነው ነገር የሚይዙትን የሚጨብጡትን ያጡ የመሐመድ ወላጆች እውነታውን ለመቀበል ብዙ ተቸግረዋል፡፡

የመሐመድ ቀላሉ ሕክምና ወደ ዘላቂ ችግር የመራው ሲሆን፣ ወደ ፅኑ ሕሙማን ክፍል ተዛውሮ በመሣሪያ ድጋፍ እየተነፈሰ እንዲታከም ተገደደ፡፡ ወደ ሕክምና ከመግባቱ በፊት ሙሉ ምርመራ ተደርጎለት ጤናማ መሆኑ ተረጋግጦ እንደነበር የሚናገሩት እናቱ ወ/ሮ ሃሊማ እንዳይሆን ሆኖ የቀረ ልጃቸውን ነገር ክፉ አጋጣሚ ብቻ ብለው አለማለፋቸውን ይናገራሉ፡፡ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከሚገኝበት ሪያድ ድረስ ሄደው ጉዳዩን አቤት ብለዋል፡፡ እንዲሁም ጅዳ ለሚገኘው ቆንስላም ጉዳዩን በዝርዝር አቅርበዋል፡፡

ጉዳዩን ለአገሪቱ ጤና ጥበቃ አቅርበውም የመሐመድ ጤንነት አሁን ያለበት ሁኔታ ላይ የደረሰው ሙሉ በሙሉ በሕክምና ስህተት እንደሆነ አረጋግጧል። የመሐመድን ሕክምና ስህተት የመረመረው የሳዑዲ ዓረቢያ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የሐኪሞች ቦርድ 2.4 ሚሊዮን ሪያል ካሳ እንዲከፈል የወሰነ ቢሆንም ወይዘሮዋ ግን የልጄን ጤና መልሱልኝ በማለት ገንዘቡን አልቀበልም ብለው እንደነበር የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡

ከሰመመን ሳይነቃ 12 ዓመታትን ያስቆጠረው መሐመድ ጉዳይ በማኅበራዊ ሚዲያዎች አነጋጋሪ ሆኖ ነበር የሰነበተው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አሕመድ (ዶ/ር) ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ ለሥራ ባቀኑበት ወቅት በሐኪሞች ስሕተት ለተወሳሰበ የጤና ችግር የተዳረገውን ሕጻን መሐመድና እናቱን መጠየቃቸውን ተከትሎ መልካም ዜናዎች እየተሰሙ ነው።

ሳዑዲ ለዓመታት የአልጋ ቁራኛ ለሆነው ታዳጊ መሐመድ ሙሉ የካሳ ክፍያ ለመስጠት መወሰኗ ዋናው ሲሆን፣ ወደ አገር ቤት በሚመለስበት ወቅትም ለሚደረገው የሕክምና ክትትል ወጪ እንደምትሸፍንም ገልጻለች። የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍጹም አረጋ በግል የትዊተር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ የሳዑዲረቢያ መንግሥት ለሕፃኑ ቤተሰቦች ሙሉ የካሳ ክፍያ ለመስጠት መስማማቱን ገልጸዋል። ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ ለሚደረግለት እንክብካቤ ሁሉም ወጪዎች በሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥት እንደሚሸፈኑም በገፃቸው አስፍረዋል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አስጨናቂው የኑሮ ውድነት ወዴት እያመራ ነው?

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የኑሮ ውድነት እንደ አገር ከባድ ፈተና...

‹‹ወላድ ላማቸውን አርደው ከደኸዩት ወንድማማቾች›› ሁሉም ይማር

በንጉሥ ወዳጅነው   የዕለቱን ጽሑፍ በአንድ አንጋፋ አባት ወግ ልጀምር፡፡ ‹‹የአንድ...

የመጋቢቱ ለውጥና ፈተናዎቹ

በታደሰ ሻንቆ ሀ) ችኩሎችና ገታሮች፣ መፈናቀልና ሞትን ያነገሡበት ጊዜ እላይ ...

ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ሥርዓት ሳይዘረጉ አገልግሎት ለመስጠት መነሳት ስህተት ነው!

በተለያዩ የመንግሥትና የግል ተቋማት ውስጥ ተገልጋዮች በከፈሉት ልክ የሚፈልጉትን...