Tuesday, March 28, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየሴት ሳይንቲስቶችን ቁጥር ለመጨመር ተግባራዊ ዕርምጃ እንዲወስድ ተጠየቀ

የሴት ሳይንቲስቶችን ቁጥር ለመጨመር ተግባራዊ ዕርምጃ እንዲወስድ ተጠየቀ

ቀን:

ከዚህ ቀደም ሴቶች እንዳይበቁ ማነቆ የነበሩ ችግሮች በጥናት በመለየታቸውና በቂ ግንዛቤ ማስጨበጥ በመቻሉ ቀጣዩ ሥራ በተግባር ላይ ያተኮረ እንዲሆን፣ የወጣው ግብም ምን ያህል ተፈጻሚ መሆኑን ለመገምገም በየዓመቱ ይህንን ያህል ሴቶች መብቃት አለባቸው ሲባል በቁጥር መለየት እንደሚገባው፣ የኢትዮጵያ የሳይንስ አካዳሚ አስታወቀ፡፡ ሥራ አስፈጻሚው ፕሮፌሰር ማስረሻ ፈጠነ ይህን የተናገሩት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ ሴት ሳይንቲስቶችን በሥራቸው እንዲበረቱ፣ ይበልጥ እንዲነሳሱ ለማድረግና ማብቃት ላይ ያተኮረው በሐርመኒ ሆቴል በተደረገው የሁለት ቀናት በተካሄደው ዓውደ ርዕይ ላይ ነበር፡፡

የመክፈቻ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴዔታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ እንዳሉት፣ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገቡ 70 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች የሳይንስ ትምህርት እንዲማሩ መደረጉ በሳይንስና ቴክኖሎጂው ዘርፍ በቂ የሰው ኃይል እንዲኖር ያስችላል፡፡ በርካታ ሴቶችም በዘርፉ ገብተው እንዲማሩ ዕድል ፈጥሯል፡፡ ነገር ግን አሁንም በኢኮኖሚና በፖለቲካው ዘርፍ የሴቶች ተሳትፎ ደካማ ነው፡፡

ይህ ችግር በተለይም በሳይንስና በፈጠራ ሥራዎች ረገድ ጐልቶ የሚታይ መሆኑን የሚናገሩት ፕሮፌሰር ማስረሻ በቂ የትምህርት ደረጃ ያላቸው ሴቶች ቁጥር አነስተኛ መሆን በሳይንሱ ረገድ በቂ ተሳትፎ እንዳይኖራቸው አስተዋጽኦ ማድረጉን ይናገራሉ፡፡ ‹‹የመጀመሪያ ዲግሪ፣ ሁለተኛ ዲግሪና ሦስተኛ ዲግሪ ያላቸው ሴቶች ቁጥር አናሳ ነው፡፡ የተሻለ ቁጥር ያላቸውም የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው ሴቶች ናቸው፡፡ ነገር ግን በሳይንስና ፈጠራ ረገድ ለመሳተፍ ሁለተኛና ሦስተኛ ዲግሪ ቢኖራቸው ይመረጣል፡፡ ይሁን እንጂ የተሻለ የትምህርት ደረጃ ያላቸው ሴቶች በጣት የሚቆጠሩ ናቸው›› በማለት በሳይንስና ፈጠራ የሚሳተፉ ሴቶችን ቁጥር ከፍ ለማድረግ ከፍተኛ የቤት ሥራ እንደሚጠበቅ ይናገራሉ፡፡

መቀመጫውን ጀርመን አገር ያደረገውና በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሳይንቲስቶች አካዳሚክ ድጋፍ የሚያደርገውና በቅርቡ በኢትዮጵያ ቢሮ የከፈተው የሁምቦልት ማኅበርና የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በጋራ ባዘጋጁት የሁለት ቀናት ዐውደ ጥናት ላይ ‹‹የሴት ሳይንቲስቶችን ቁጥር ማብዛት እንዲሁም ሴቶችን ማብቃት የሚቻለው እንዴት ነው?›› በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡ መሰል ውይይቶች በዘርፉ የሴቶችን ተሳተፎ ለማሳደግ እንደሚያስፈልጉ የተናገሩት ፕሮፌሰሩ የተለያዩ የግንዛቤና የማብቃት ሥራዎችን በመሥራት አካዳሚው የበኩሉን እንደሚወጣ ገልጸዋል፡፡  

በ2002 ዓ.ም. የተቋቋመው የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ለትርፍ ያልተቋቋመና መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ነው፡፡ በጥቂት ሳይንቲስቶች የተቋቋመው አካዳሚው በአገሪቱ ሳይንስ እንዲስፋፋ፣ የልማት አጋር እንዲሆን፣ የተሻለ የጤና አገልግሎት እንዲስፋፋ እንቅስቃሴ ማድረግን ያለመ ነው፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ...

የፓርላማ አባላት ስለሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ግልጽ መረጃ የለንም አሉ

‹‹ሕወሓትን ለፍረጃ አብቅተውት የነበሩ ጉዳዮች በአብዛኛው መልክ ይዘዋል›› ሬድዋን...