Wednesday, June 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናበፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች ላይ ከብሔራዊ ደኅንነት ተገኘ የተባለው ማስረጃ እንዲቀርብ ትዕዛዝ ተሰጠ

በፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች ላይ ከብሔራዊ ደኅንነት ተገኘ የተባለው ማስረጃ እንዲቀርብ ትዕዛዝ ተሰጠ

ቀን:

በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በነፃ ከተሰናበቱ በኋላ ይግባኝ ተብሎባቸው በእስር ላይ የሚገኙት የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች ላይ፣ ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት መሥሪያ ቤት ተገኝቷል የተባለው ‹‹ኦርጂናል›› ማስረጃ እንዲቀርብ ማክሰኞ ጥር 10 ቀን 2008 ዓ.ም. ትዕዛዝ ተሰጠ፡፡

የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ የቀድሞው አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ አመራሮች አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ አቶ ዳንዴል ሺበሺ፣ የአረና ፓርቲ አመራር አቶ አብርሃ ደስታና የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አቶ የሸዋስ አሰፋ ላይ ያቀረበውን የይግባኝ አቤቱታ እየመረመረው የሚገኘው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ትዕዛዙን ያስተላለፈው፣ ዓቃቤ ሕግ በይግባኝ አቤቱታው ላይ ባቀረበው ዝርዝር መግለጫ ውስጥ የሥር ፍርድ ቤት ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት ያቀረበውን ማስረጃ ሳይመዝን (ሳይመረምር) እንዳለፈበት ካመለከተ በኋላ ነው፡፡

ፍርድ ቤቱ በዓቃቤ ሕግ የቀረበለትን አቤቱታ ‹‹ያስቀርባል›› ካለ በኋላ ሁለቱን ወገኖች አክራክሮ ስለነበር፣ ጥር 10 ቀን 2008 ዓ.ም. ብይን ይሰጣል ተብሎ ተጠብቆ ነበር፡፡

- Advertisement -

ይግባኝ ሰሚው ችሎት እንደገለጸው ግን፣ ዓቃቤ ሕግ በሥር ፍርድ ቤት እንዳልታየለት በአቤቱታው የገለጸውና ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት መሥሪያ ቤት ‹‹አገኘሁት›› ያለው ማስረጃ፣ ማስረጃ ሳይሆን የመረጃ ትንተና የተሰጠበት ሰነድ በመሆኑ ዋናው ‹‹ኦርጂናሉ›› ቀርቦ እንዲመረመር አዟል፡፡ መረጃው እንደወረደ መቅረብ እንዳለበት፣ ከፌስቡክም ይሁን ከኢሜል የተገኘው መረጃ ቃል በቃል እንዲቀርብ እንጂ፣ ትንታኔው መሆን እንደሌለበት ገልጿል፡፡ ከእነ ሀብታሙ አያሌው ጋር ይግባኝ የተባለባቸው አቶ አብርሃም ሰለሞንን ስለሚመለከትም በሥር ፍርድ ቤት ለዓቃቤ ሕግ ምስክር ሆነው የቀረቡት የሦስተኛ ምስክር ሙሉ የምስክርነት ቃል ተገልብጦ እንዲቀርብለት በማዘዝ፣ ለጥር 24 ቀን 2008 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...