ሱ ሼፍ ጌታዋ በሪሁን
ጥሬ እቃዎች
- 2 ፍሬ የተከተፈ ኩከምበር ( ኪያር)
- 4 ፍሬ የተከተፈ ቲማቲም
- 2 ራስ በቁመቱ የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት
- 1 የሻይ ማንኪያ የደቀቀ ነጭ ሽንኩርት
- 1 የሾርባ ማንኪያ የሾርባ ቅጠል
- 2 እግር ሰላጣ (በትንሹ የተቆራረጠ)
- ½ የሻይ ማንኪያ ጨው
- ½ የሻይ ማኪያ ቁንዶ በርበሬ
- 1 ሲኒ ዘይት
- ሩብ ሲኒ ኮምጣጤ
- 4 ዳቦ
አዘገጃጀት
- በጎርጓዳ ሳህን ውስጥ የተዘጋጀውን ኪያር፣ ቀይ ሽንኩርት፣ ነጭ ሽንኩርት፣ የሾርባ ቅጠል፣ ቲማቲም እና ሰላጣውን ባንድ ላይ ማደባለቅ
- ጨው ቁንዶ በርበሬ፣ ዘይት እና ኮምጣጤውን ባንድ ላይ በማንኪያ ( በእንቁላል መምቻ) ማደባለቅ
- በመጨረሻ የተዘጋጀውን ሶስ ከሰላጣው ጋር በመቀላቀል በተዘጋጀው ሳህን ላይ በማድረግ መመገብ