Thursday, February 13, 2025
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርት‹‹አረንጓዴው ጎርፍ›› በዱባይ ማራቶን

‹‹አረንጓዴው ጎርፍ›› በዱባይ ማራቶን

ቀን:

spot_img

‹‹ዓለምሽ ዛሬ ነው ዛሬ

ዓለምሽ ዛሬ ነው ዛሬ

ኦሆሆ ኢትዮጵያ ሀገሬ›› የሚለው ኅብረ ዝማሬ በዱባይ አውራ ጎዳና ላይ የተሰማው ዓርብ ማለዳ ነበር፡፡ የዋሊያዎቹን መለያ ሹራብ የለበሱ፣ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማን ያነገቡ ወጣት ኢትዮጵያውያን ጡሩምባ እየነፉ፣ ፊኛ እየለቀቁ የጭፈራ ድምፅ ያስተጋቡት በዓመታዊው የዱባይ ማራቶን ውድድር በሁለቱም ጾታዎች ድሉ የኢትዮጵያውያን መሆኑን ተከትሎ ነበር፡፡ ገልፍ ኒውስ፣ በድረ ገጹ በቪዲዮ ጭምር ባሰራጨው ዘገባው በወንዶችም በሴቶችም ኢትዮጵያውያኑ አንድም ጣልቃ ሳያስገቡ የመጀመሪያዎቹን አምስት ቦታዎች ለመጨበጥ ችለዋል፡፡

የስታንዳርድ ቻርተርድ ዱባይ ማራቶን አዲሱ አሸናፊ ለመሆን የበቃው ተስፋዬ አበራ የገባበት ጊዜ 2 ሰዓት 04 ደቂቃ 24 ሰከንድ ነበር፡፡ በሁለተኛነት ያስከተለው የአምናውን አሸናፊ ብርሃኑ ለሚን (02:04:33) ነበር፡፡

ጥር 13 ቀን 2008 ዓ.ም. 100 ሺሕ ግድም (30 ሺሕ ሯጮች በተመዘገቡበት) በተሳተፉበት የዘንድሮው የዱባይ ማራቶን፣ በርካታ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ በአውራ ጎዳናው ተመልካቾች ድጋፍ ይሰጡ ነበር፡፡ ማለዳ 12 ሰዓት 30 በቀዝቃዛው የዱባይ ንጋት ላይ ተወዳድሮ ድል የመታው ተስፋዬ አምና በጥር ወር በሙምባይ ማራቶን ድል ሲያደርግ ያስመዘገበውን 02፡09፡46፡14 ጊዜን ሰብሮበታል፡፡

ፀጋዬ መኰንን በሦስተኛነት (02፡04፡46) አጠናቋል፡፡ በሴቶች ሩጫ ኢትዮጵያዊቷ ትርፊ ፀጋዬ በ02፡19፡41 በሆነ ጊዜ የአምና ድሏን ስትደግም፣ ያገሯ ልጅ አማኔ በሪሶ በ02፡20፡48 ሁለተኛ፣ መሰለች መልካሙ በ02፡22፡29 ሦስተኛ ሆነው ውድድራቸውን አጠናቀዋል፡፡

በወንዶች ምድብ ኢትዮጵያውያኑ ሲሳይ ለማ፣ ሙላ ዋሲሁንና ዓባይነህ አየለ ከአራተኛነት እስከ ስድስተኛነት ያለውን ቦታ አላስደፈሩም፡፡ ታዋቂው ኬንያዊ ሳሙኤል ኮስጌይ ከሰባተኛነት ማለፍ አልቻለም፡፡

በሴቶች ሩጫም አራተኛና አምስተኛ ሆነው ውድድራቸውን የፈጸሙት ኢትዮጵያውያቱ ሱቱሜ አሰፋና ሙሉ ሰቦቃ ሲሆኑ፣ ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ የባሕሬን ሯጭዋ ሽታዬ እሸቴ ስድስተኛነቱን አስከብራለች፡፡ የውድድሩ ቀዳሚ አሸናፊዎች የ200 ሺሕ ዶላር ተሸላሚ መሆናቸው ታውቋል፡፡

በሁለቱም ጾታዎች ከአሥሩ መጀመሪያ ፈጻሚዎች ከሴቶች ዘጠኙ፣ ከወንዶች ስምንቱ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን የተመለከቱ ‹‹አረንጓዴው ጎርፍ›› በዱባይ ብለውታል፡፡

በዱባይ ማራቶን የ16 ዓመት ታሪክ በወንዶች ምድብ ኢትዮጵያ ዘጠኙን ስታሸንፍ፣ ቅርብ ተፎካካሪዋ ኬንያ በሰባቱ ድልን ተቀዳጅታለች፡፡ በሴቶች የመጀመሪያዎቹን አራት ውድድሮች ሩሲያ፣ ሰባተኛውን ኬንያ ከማሸነፋቸው በስተቀር ኢትዮጵያ 11ዱን በማሸነፍ ሪከርዱን ይዛለች፡፡ በሁለቱም ጾታ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያ ድል የተቀዳጀችው በአምስተኛው ውድድር በ1966 ዓ.ም. በጋሻው አስፋውና በላይላ አማን ነበር፡፡ ኃይሌ ገብረሥላሴ (2000፣ 2001፣ 2002 ዓ.ም.) እና አሰለፈች መርጊያ (2003፣ 2004ና 2007 ዓ.ም.) ሦስት ሦስት ጊዜ ማሸነፋቸው ይታወሳል፡፡   

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአየር መንገዱን አሠራር ጥሰዋል በተባሉ የአዲስ አበባ ሽያጭ ቢሮ ሠራተኞች ላይ ዕርምጃ መወሰዱ ተገለጸ

- የሕግ ክፍሉ ክስ መመሥረት የሚቻልባቸውን ሁኔታዎች እየተመለከተ ነው...

የጋዛ ውዝግብ በአፍሪካ ቀንድ ላይ የደቀነው ሥጋት

የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አማችና የቀድሞ የመካከለኛው ምሥራቅ የፖሊሲ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በውክልና ለግሉ ዘርፍ ለማስተላለፍ ያቀዳቸው አገልግሎቶች

የከተማው አስተዳደር ካቢኔ ሰሞኑን ባሳለፈው ውሳኔ የተመረጡ መንግሥታዊ አገልግሎቶችን...