Friday, June 9, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

በኢትዮጵያና በቱርክ መካከል የተፈረመው የዲፕሎማቶች መኖሪያ የግንባታ መሬት ልውውጥ ስምምነት ፀደቀ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

በኢትዮጵያና በቱርክ መንግሥታት መካከል ለኤምባሲ፣ ለሚሲዮን መሪዎችና ለዲፕሎማቶች መኖሪያ የግንባታ መሬት ልውውጥ የተፈረመውን ስምምነት ፓርላማው አፀደቀ፡፡

ፓርላማው ጥር 10 ቀን 2008 ዓ.ም. ባካሄደው መደበኛ ጉባዔው ረቂቅ ስምምነቱን ከገመገመው የውጭ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ የቀረበውን የውሳኔ ሐሳብ አዳምጦ ነው ስምምነቱን ያፀደቀው፡፡

የውሳኔ ሐሳቡን ያቀረቡት የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ደባ እንዳሉት፣ ስምምነቱ ሁለቱ አገሮች የሚያከናውኑዋቸውን የዲፕሎማሲ ሥራዎች ለማሳለጥ ምቹ ሁኔታዎችን የሚፈጥርና ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን መሠረት ያደረገ ነው፡፡ በማከልም ቱርክ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ስትራቴጂካዊ አጋርነት ይበልጥ የሚያጠናክር፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርና ለኢትዮጵያውያን የሥራ ዕድል ከመፍጠር አኳያ በቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንት የምትጫወተውን ሚና ለማበረታታት ጠቀሜታው ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በፀደቀው ስምምነት መሠረት የቱርክ መንግሥት 3,000 ካሬ ሜትር ከክፍያ ነፃ የሆነ በቱርክ አንካራ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ የተከለለ ቦታ፣ ለሚሲዮንና ለአምባሳደር መኖሪያ ቤት ግንባታ የሚውል መሬት ያቀርባል፡፡

በአፀፋው ደግሞ የኢትዮጵያ መንግሥት 7,192.8 ካሬ ሜትር መሬት በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ለቱርክ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ ያቀርባል፡፡ የሚቀርበው ቦታ ለሚሲዮን፣ ለአምባሳደርና ለዲፕሎማቶች መኖሪያ ግንባታ የሚውል ነው፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት ከሚያቀርበው 7,192.8 ካሬ ሜትር ውስጥ፣ 4192.8 ካሬ ሜትር የሚሆነው መሬት 3.2 ሚሊዮን ዶላር ሊዝ የሚከፈልበት መሆኑ በስምምነቱ ላይ ተገልጿል፡፡

የግንባታ ቦታው የሚሰጠው በሰጥቶ መቀበል መርህ ሆኖ፣ ሁለቱም ወገኖች መሬቱን የሚጠቀሙት የዲፕሎማቲክ ተልዕኳቸውን ለማሳካት ብቻ መሆኑን ስምምነቱ ያስረዳል፡፡    

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች