Monday, September 26, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊፀረ ሙስና ኮሚሽን በግዙፍ ፕሮጀክቶች ላይ ትኩረት አደርጋለሁ አለ

  ፀረ ሙስና ኮሚሽን በግዙፍ ፕሮጀክቶች ላይ ትኩረት አደርጋለሁ አለ

  ቀን:

  – ከመልካም አስተዳደር ችግሮች 40 በመቶ ከሙስና ጋር ይያያዛሉ ተብሏል

  መንግሥት በቢሊዮን በሚቆጠር ገንዘብ በሚያካሂዳቸው ግዙፍ ፕሮጀክቶች ላይ ሙስና ይፈጸማል የሚል ጥርጣሬ በመኖሩ፣ በፕሮጀክቶቹ ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

   ዓርብ ጥር 13 ቀን 2008 ዓ.ም. የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ከንግዱ ኅብረተሰብ ጋር በጉዳዩ ላይ መክሯል፡፡

  የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የሥነ ምግባር አውታሮች ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ዋና አማካሪ አቶ አበበ ዘውዴ በወቅቱ ባቀረቡት ጽሑፍ መንግሥት በሚያካሂዳቸው ግዙፍ ፕሮጀክቶች፣ ለአብነት የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች፣ የባቡር መስመር ግንባታዎች፣ የመንገድ ግንባታዎችና የመስኖ ፕሮጀክቶች ላይ ሙስና እንደሚፈጽም ጥርጣሬ እንዳለ ጠቁመዋል፡፡

  በቀረበው ጽሑፍ እንደተብራራው ሙስና የሚፈጸመው ከፍተኛ ሀብት ባለባቸው አካባቢዎች ነው፡፡ ከፍተኛ ገንዘብና ንብረት ባለባቸው አካባቢዎች ሙስና የሚፈጸም ከመሆኑም ባሻገር፣ የሚፈጸመው ሙስና ውስብስብ ገጽታ ያለው ነው፡፡

  በዚህ መሠረት የፀረ ሙስና ኮሚሽን ከሰነድ ዝግጅት ጀምሮ ያለውን ሒደት እንደሚከታተል፣ በተለይ ሙስና ከተፈጸመ በኋላ ሳይሆን ከመፈጸሙ በፊት በመከላከል ላይ እንደሚሠራ ተመልክቷል፡፡

  ከግዙፍ ፕሮጀክቶች በተጨማሪም በመሬት አስተዳደር፣ በግብርና ታክስ፣ በፍትሕ አሰጣጥና በግዥዎች ላይ ትኩረት እንደሚደረግ ታውቋል፡፡

  በምክክር መድረኩ ላይ ሙስና ለመልካም አስተዳደር መስፈን ትልቁ ጠንቅ ነው ተብሏል፡፡ በኢትዮጵያ ከሚፈጸሙ የመልካም አስተዳደር ችግሮች 40 በመቶው ከሙስና ጋር የተያያዙ ነው ተብሏል፡፡

  የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ምክትል ኮሚሽነር አቶ ወዶ አጦ በምክክሩ ላይ እንደገለጹት፣ ኮሚሽኑ በንግዱ ዘርፍ ያለውን ችግር ለመፍታት ይሠራል፡፡ በንግዱ ማኅበረሰብ ግብርና ታክስ መሰወር፣ ጥራታቸውን ያልጠበቁ ምርቶች ወደ አገር ማስገባት፣ ከመንግሥት ሠራተኞች ጋር በመመሳጠር ያልተገቡ ድርጊቶችን መፈጸም ከተጠቀሱት ችግሮች መካከል ይገኙበታል፡፡

  የፀረ ሙስና ኮሚሽን ከዚህ ቀደም ባሉት ጊዜያት ከመሬት፣ ከታክስና ከግዥ ጋር የሚነሱ ችግሮች ላይ ጥናት እያካሄደ ዕርምጃ ሲወስድ የቆየ ቢሆንም፣ በግዙፍ ፕሮጀክቶች ላይ እጆቹን ሳይዘረጋ ቆይቷል እየተባለ ይተቻል፡፡

  ባለፈው ዓርብ በተካሄደው ምክክር ላይ ግን በግዙፍ ፕሮጀክቶች ላይ ጥርጣሬ መኖሩን በመግለጽ፣ በቀጣይ ጊዜያት የትኩረት አቅጣጫው እንደሚያደርጋቸው አስታውቋል፡፡ 

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  በኢትዮጵያ ላይ የቀጠለው የምዕራባውያን ጣልቃ ገብነት

  ምዕራባውያን አገሮች በኢትዮጵያ ላይ ጠንካራ ጫና ማሳደራቸውን ቀጥለዋል፡፡ በዲፕሎማሲም...

  የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የድጎማ በጀት ለፖለቲካ ሥራ ማስፈጸሚያ እንደሚውል የሚያሳይ ሪፖርት ቀረበ

  ለመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የሚደረግ የበጀት ድጎማ ከመደበኛው ሥራ ይልቅ ከዋናው...

  መንግሥት የሥራ ግብር ምጣኔን እንዲቀንስ ተጠየቀ

  የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) መንግሥት የሠራተኛውን የኑሮ ጫና...

  የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የአመራሮች ምርጫና ቀጣይ ዕቅዶቹ

  የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ሲጠበቅ የነበረውን...