ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል የመሀል ዳኛ ባምላክ ተሰማ፣ በቻን 2016 ኒጀር ከቱኒዚያ ጋር ጥር 17 ቀን 2008 ዓ.ም. ያደረጉትን የምድብ ሦስት ጨዋታ በመሀል ዳኝነት መርተዋል፡፡ ባምላክ ከዚህ ቀደም አይቮሪኮስት ከሞሮኮ በምድብ አንድ ያደረጉትን ጨዋታ በመሀል ዳኝነት የመሩ ሲሆን፣ አንድ የፍጹም ቅጣት ምትም ለዝሆኖቹ ሰጥተዋል፡፡ በምድብ አራት ዩጋንዳ ከማሊ ባደረጉት ጨዋታ ደግሞ አራተኛ ዳኛ ነበሩ፡፡